EPISODE · Jun 22, 2026 · 1H
የህዳሴው ግድብ በቡድን 7 አባል አገራት ስብሰባ፡- የትራምፕ ቃል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት
from Continental Drift
የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የሉዓላዊነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተምሳሌት ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የግድቡ ግንባታ በግብፅ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ አሜሪካ በድጋሚ የመደራደር ፍላጎት እንዳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡"ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ለመደራደር ሞክረው ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚገፍ እና ተቀባይነት የሌለው ስምምነት ተረቅቆ ነበር፤ ይሄ ስምምነት በኋላ በባይደን አስተዳደር እንዲነሳ ተደርጓል። አሁን ደግሞ ለፕሬዝዳንት ሲሲ ይህን ሂደት እንደሚጀምሩ ቃል እየገቡ ነው፤ ምንም የተለየ አዲስ ነገር ይዘው እንደሚመጡ አልጠብቅም።" ሲሉ ፈቃአህመድ ነጋሽ፣ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የህዳሴ ግድብን ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ ውስብስብነት እንዲሁም የኢትዮጵያን አዳዲስ የኦዲት ማሻሻያዎች በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ፈቃአህመድ ነጋሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የገንዘብ ዘርፍ ሀላፊ ተመስገን ጌታዬ ጋር ቆይታ አድርገናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
What this episode covers
የኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ ከመሆኑ ባለፈ፣ የሉዓላዊነት እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ተምሳሌት ሆኗል። በቅርቡ ደግሞ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 (G7) አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የግድቡ ግንባታ በግብፅ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን በመጥቀስ አሜሪካ በድጋሚ የመደራደር ፍላጎት እንዳላት ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡"ትራምፕ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ለመደራደር ሞክረው ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚገፍ እና ተቀባይነት የሌለው ስምምነት ተረቅቆ ነበር፤ ይሄ ስምምነት በኋላ በባይደን አስተዳደር እንዲነሳ ተደርጓል። አሁን ደግሞ ለፕሬዝዳንት ሲሲ ይህን ሂደት እንደሚጀምሩ ቃል እየገቡ ነው፤ ምንም የተለየ አዲስ ነገር ይዘው እንደሚመጡ አልጠብቅም።" ሲሉ ፈቃአህመድ ነጋሽ፣ የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የህዳሴ ግድብን ዲፕሎማሲያዊ እና ህጋዊ ውስብስብነት እንዲሁም የኢትዮጵያን አዳዲስ የኦዲት ማሻሻያዎች በሁለት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም የድንበር ተሻጋሪ የውሃ አስተዳደር እና የሃይድሮ-ፖለቲካ አማካሪ ፈቃአህመድ ነጋሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የገንዘብ ዘርፍ ሀላፊ ተመስገን ጌታዬ ጋር ቆይታ አድርገናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
NOW PLAYING
የህዳሴው ግድብ በቡድን 7 አባል አገራት ስብሰባ፡- የትራምፕ ቃል እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ መብት
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.