EPISODE · Aug 9, 2025 · 25 MIN
1ኛ ዮሐንስ መልእክት በማሙሻ ፈንታ - መግቢያ 1John Introduction by Mamusha Fenta
from Evangelist Elsabet Tasisa
የሕይወት ቃል1ከመጀመሪያው ስለ ነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፤ ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይኖቻችን ያየነው፥ የተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው ነው። 2ይህ ሕይወት ተገልጦአል፤ እኛም አይተነዋል፤ እንመሰክራለንም። በአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛም የተገለጠውን የዘለዓለም ሕይወት እንነግራችኋለን። 3ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን። አንድነታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው። 4ደስታችን ሙሉ እንዲሆን ይህን እንጽፍላችኋለን።እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑ5ከእርሱ የሰማነውና ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት “እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም” የሚል ነው። 6ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት አለን” እያልን በጨለማ የምንኖር ከሆንን እንዋሻለን፤ በቃላችንም ሆነ በሥራችን እውነት የለም ማለት ነው። 7ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንኖር እርስ በርሳችን አንድነት ይኖረናል። ደግሞም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።8ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናታልላለን። እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። 9ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር ብንናዘዝ እርሱ ታማኝና ጻድቅ ስለ ሆነ ኃጢአታችንን ሁሉ ይቅር ይልልናል፤ ከበደላችንም ሁሉ ያነጻናል። 10ኃጢአት አልሠራንም ብንል እግዚአብሔርን ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።
Embed this episode
NOW PLAYING
1ኛ ዮሐንስ መልእክት በማሙሻ ፈንታ - መግቢያ 1John Introduction by Mamusha Fenta
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.