1ኛ ዮሐንስ መልእክት በማሙሻ ፈንታ - ምዕራፍ 3 ክፍል 2 (1 John Chapter 3 Part 2 by Mamusha Fenta) episode artwork

EPISODE · Feb 13, 2026 · 29 MIN

1ኛ ዮሐንስ መልእክት በማሙሻ ፈንታ - ምዕራፍ 3 ክፍል 2 (1 John Chapter 3 Part 2 by Mamusha Fenta)

from Evangelist Elsabet Tasisa

1የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን። ዓለም እኛን የማያውቀንም እርሱን ስላላወቀው ነው። 2ወዳጆች ሆይ፤ እኛ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደ ፊት ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ እናየዋለን፤ እርሱን እንደምንመስልም እናውቃለን። 3በርሱ ይህን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ፣ እርሱ ንጹሕ እንደ ሆነ ራሱን ያነጻል።4ኀጢአት የሚያደርግ ሁሉ ዐመፅን ያደርጋል፤ ኀጢአትም ዐመፅ ነው። 5እርሱ ኀጢአትን ሊያስወግድ እንደ ተገለጠ ታውቃላችሁ፤ በርሱም ኀጢአት የለም። 6በርሱም የሚኖር ኀጢአትን አያደርግም፤ ኀጢአት የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም።7ልጆች ሆይ፤ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው። 8ኀጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፤ ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ አንሥቶ ኀጢአትን የሚያደርግ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው። 9ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኀጢአትን በመለማመድ አይቀጥልም፤ የርሱ ዘር በውስጡ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደም ኀጢአትን ሊያደርግ አይችልም። 10የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፤ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ11ከመጀመሪያ የሰማችኋት፣ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል የምትለዋ መልእክት ይህች ናትና፤ 12የክፉው ወገን ሆኖ ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየን አትሁኑ፤ ለምን ገደለው? ምክንያቱም የርሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው። 13ወንድሞች ሆይ፤ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ። 14ወንድሞቻችንን ስለምንወድድ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ፍቅር የሌለው ሁሉ በሞት ይኖራል። 15ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳይም የዘላለም ሕይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ።16ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ ስለ ሰጠ፣ ፍቅር ምን እንደ ሆነ በዚህ እናውቃለን፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን ልንሰጥ ይገባናል። 17ማንም የዚህ ዓለም ሀብት እያለው፣ ወንድሙ ሲቸገር አይቶ ልቡ ባይራራለት፣ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዴት በርሱ ይኖራል? 18ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።19እኛ ከእውነቱ መሆናችንን በዚህ እናውቃለን፤ ልባችንንም በፊቱ እናሳርፋለን፤ 20ይህም ልባችን በእኛ ላይ በሚፈርድብን ነገር ሁሉ ነው። እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉን ነገር ያውቃል። 21ወዳጆች ሆይ፤ ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን፤ 22ትእዛዞቹንም ስለምንጠብቅና በፊቱም ደስ የሚያሠኘውን ስለምናደርግ የምንለምነውን ሁሉ ከርሱ እንቀበላለን። 23ትእዛዙም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና እርሱ እንዳዘዘንም እርስ በርሳችን እንድንዋደድ ነው። 24ትእዛዞቹንም የሚጠብቁ ሁሉ በርሱ ይኖራሉ፤ እርሱም በእነርሱ ይኖራል። በእኛ መኖሩን በዚህ፣ ይኸውም እርሱ በሰጠን መንፈስ እናውቃለን።

Episode metadata supplied by the publisher feed · Published Feb 13, 2026

Embed this episode

Ready to play

1ኛ ዮሐንስ መልእክት በማሙሻ ፈንታ - ምዕራፍ 3 ክፍል 2 (1 John Chapter 3 Part 2 by Mamusha Fenta)

0:00 29:57

No transcript for this episode yet

We transcribe on demand. Request one and we'll notify you when it's ready — usually under 10 minutes.

No similar episodes found.

Love Evangelist Love Going Higher, Deeper, and Further. It's all about Love, Liberty, and Truth. If I can't be honest, well, what's the whole point? Greg Laurie: A New Beginning Greg Laurie Greg Laurie delivers clear, Bible-based teaching on topics all Christians face—from marriage and family to evangelism and purpose—while emphasizing the saving power of the gospel. With humor and cultural insight, he shows how to apply God’s Word in everyday life and strengthen your walk with Christ.He is the senior pastor of Harvest Church, with campuses located in California and Hawaii, a renowned evangelist, bestselling author, and inspiration for the 2023 “Jesus Revolution” film. He is also the founder and leader of Harvest Crusades, large-scale evangelistic events that share the gospel with thousands in stadiums worldwide. Learn more about Pastor Greg’s and Harvest Ministries’ mission to know God and make Him known at harvest.org. Dag Heward-Mills Video Podcast Dag Heward-Mills Welcome to Dag Heward-Mills Podcast. Here you can watch videos on all messages preached by Evangelist Dag Heward-Mills. These valuable teachings will change your life and ministry forever. Revival Lifestyle with Isaiah Saldivar Charisma Podcast Network Revival Lifestyle is a weekly podcast hosted by traveling preacher and evangelist, Isaiah Saldivar. Each week, Isaiah hosts revivalists from around the country to discuss our call to living every day in revival. If you are hungry to know more about miracles, deliverance, and the supernatural power of God, this is the podcast for you.

Frequently Asked Questions

How long is this episode of Evangelist Elsabet Tasisa?

This episode is 29 minutes long.

When was this Evangelist Elsabet Tasisa episode published?

This episode was published on February 13, 2026.

Can I download this Evangelist Elsabet Tasisa episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.
URL copied to clipboard!