EPISODE · Mar 2, 2026 · 1H
ዓድዋ:- የሉዓላዊነት መሠረትና የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አቀጣጣይ
from Continental Drift
የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የተመዘገበው የዓድዋ ድል ጣሊያንን በጦር ሜዳ የማሸነፍ ጉዳይ ብቻ አይደለም።አፍሪካውያን በራሳቸው መደራጀት እና ማሸነፍ እንደሚችሉ ለዓለም ያሳዩበት የታሪክ ምዕራፍ ጭምር እንጂ። ዛሬም ግን የሉዓላዊነት ጥያቈ መልኩ ብዙ ሆኖ እያየነው ነው። "አፍሪካ ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳትጠይቅ በጠንካራ አቋም ወደ ድርድር ጠረጴዛው መምጣት አለባት። እነዚህን ሐሳቦች ስላስተዋወቅን ብቻ ‘ባህላዊ’ ጉዳዮች ሊባሉ አይገባም፤ ምክንያቱም ይህ ማንነታችን በመሆኑ ወሳኝ ነው።[...]‘ጭራው ውሻውን እንዲያወዛውዝ’ መፍቀድ የለብንም።" ሲሉ ፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ለስፑቲክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የዓድዋን ድል ከወቅታዊው የአፍሪካ ሉዓላዊነት ትግል ጋር በማገናኘት ከፓን-አፍሪካዊትና የሕግ ባለሙያ ደስታ መጉዎ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
Embed this episode
NOW PLAYING
ዓድዋ:- የሉዓላዊነት መሠረትና የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ አቀጣጣይ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.