EPISODE · Feb 25, 2026 · 1H
በፈተና ፅኑ // በነብይ ጥላሁን ፀጋዬ // PROPHET TILAHUN TSEGAYE
from Evangelist Elsabet Tasisa
'1የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የሆነው ያዕቆብ፤ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ነገዶች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን። 2ወንድሞቼ#1፥2 ወንድሞቼ ወንድሞች የሚለው የግሪኩ ቃል ወንዶችን ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አካል በመሆናቸው ያመኑትን ወንዶችንና ሴቶችንም ያመለክታል፤ ከዚህ ቍጥር ውጪ በ16፣ 19፤ እና በ2፥1፣5፣14፤ 3፥10፣12፤ 4፥11፤ 5፥7፣9፣10፣12፣19 ላይ እናገኘዋለን። ሆይ፤ ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤ 3ምክንያቱም የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ። 4ምንም የማይጐድላችሁ ፍጹማንና ምሉኣን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን ይፈጽም። 5ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጐድለው፣ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉም የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለርሱም ይሰጠዋል። 6ዳሩ ግን ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፤ ምክንያቱም የሚጠራጠር ሰው በነፋስ እንደሚገፋና እንደሚናወጥ የባሕር ማዕበል ነው። 7ያ ሰው፣ ከጌታ አንዳች ነገር አገኛለሁ ብሎ አያስብ፤ 8እርሱ በሁለት ሐሳብ የተያዘና በመንገዱ ሁሉ የሚወላውል ነው። 9ዝቅ ያለው ወንድም ከፍ በማለቱ ይመካ። 10ባለጠጋውም ዝቅ በማለቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ይረግፋልና። 11ፀሓይ በነዲድ ሙቀቷ ወጥታ ሣሩን ታጠወልጋለችና፤ አበባው ይረግፋል፤ ውበቱም ይጠፋል፤ እንዲሁም ባለጠጋ ሰው፣ በዕለት ተግባሩ ሲዋትት ሳለ ይጠፋል። 12በፈተና የሚጸና ሰው ብፁዕ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወድዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል። 'ያዕቆብ 1:1-12
Embed this episode
NOW PLAYING
በፈተና ፅኑ // በነብይ ጥላሁን ፀጋዬ // PROPHET TILAHUN TSEGAYE
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.