EPISODE · Feb 22, 2026 · 1H 12M
''በማይመች ዘመን'' ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ || ''bemayimechi zemeni'' Dr. Mamusha Fenta
from Evangelist Elsabet Tasisa
'1በሠላሳኛው ዓመት፣#1፥1 ወይም ዓመቴ በአራተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን፣ በኮቦር ወንዝ አጠገብ በምርኮኞች መካከል ሳለሁ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ። 2ንጉሡ ዮአኪን በተማረከ በዐምስተኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ቀን፣ 3በባቢሎናውያን#1፥3 ወይም በከለዳውያን ምድር በኮቦር ወንዝ አጠገብ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቡዝ ልጅ፣#1፥3 ወይም ወደ ካህኑ ቡዝ ልጅ ወደ ሕዝቅኤል ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ በዚያ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ነበረች። 4እኔም አየሁ፤ ስመለከትም፣ እነሆ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል መጣ፤ ይኸውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ፣ መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበረ፤ የእሳቱም መኻል የጋለ ብረት ይመስል ነበር። 'ሕዝቅኤል 1:1-'26ከራሳቸው በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ የሰንፔር#1፥26 ወይም ላፒስ ላዙሊ ዙፋን የሚመስል ነገር ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የሰው መልክ የሚመስል ነበር። 27ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ በእሳት መካከል እንዳለ የጋለ ብረት፣ ከወገቡም በታች እሳት ይመስል እንደ ነበር አየሁ፤ ደማቅ ብርሃንም በዙሪያው ነበር። 28በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታየው ቀስተ ደመና በዙሪያው ያለው ጸዳል እንዲሁ ነበር። ይህም የእግዚአብሔር ክብር መልክ አምሳያ ነበረ። ባየሁትም ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ የአንድ ተናጋሪን ድምፅ ሰማሁ።'ሕዝቅኤል 1:26-28'1እርሱም፣ “የሰው ልጅ#2፥1 በዕብራይስጥ ቤን አዳም ማለት የሰው ልጅ ማለት ነው። የሰው ልጅ የሚለው ይህ ቃል በአዲስ ኪዳን ላይ ካለው የሰው ልጅ ከሚለው ጋራ ግንኙነት ስላለው በትንቢተ ሕዝቅኤል ላይ በዚህ መልኩ ተቀምጧል። ሆይ፤ ተነሥተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም እናገርሃለሁ” አለኝ። 2እርሱም ሲናገር፣ መንፈስ ወደ ውስጤ ገብቶ በእግሬ አቆመኝ፤ ሲናገረኝም ሰማሁት። 3እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእኔ ላይ ወደ ዐመፀው፣ ወደ ዐመፀኞቹ የእስራኤል ልጆች እልክሃለሁ፤ እነርሱና አባቶቻቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐምፀውብኛል። 4ሕዝቡም እልኸኛና ዐንገተ ደንዳና ነው፤ እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፤ አንተም ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ በላቸው። 'ሕዝቅኤል 2:1-'1እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በፊትህ ያለውን ብላ፤ ይህን ጥቅልል መጽሐፍ ብላና ሄደህ ለእስራኤል ቤት ተናገር” አለኝ። 2ስለዚህ አፌን ከፈትሁ፤ እርሱም መጽሐፉን አጐረሠኝ። 3እርሱም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ እኔ የምሰጥህን ይህን ጥቅልል መጽሐፍ ብላ፤ ሆድህንም ሙላ” አለኝ። እኔም በላሁት፤ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠኝ። 'ሕዝቅኤል 3:1-
Embed this episode
NOW PLAYING
''በማይመች ዘመን'' ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ || ''bemayimechi zemeni'' Dr. Mamusha Fenta
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.