EPISODE · Feb 24, 2026 · 22 MIN
እንቁዬን በሌሊት አልጥልም / Gloria Aman
from Evangelist Elsabet Tasisa
16በዚህ ጊዜ ሁለት ዝሙት ዐዳሪዎች ወደ ንጉሡ መጥተው ከፊቱ ቆሙ። 17ከእነርሱም አንዲቱ እንዲህ አለች፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት ዐብረን እንኖራለን፤ ዐብራኝ እያለችም እኔ ልጅ ወለድሁ፤ 18እኔ ከወለድሁ ከሦስት ቀን በኋላም፣ ይህች ሴት ወለደች፤ የነበርነው እኛ ብቻ ነን፤ ከሁለታችን በቀር በዚያ ቤት ማንም አልነበረም።19“የዚህች ሴት ሕፃን ልጅ ስለ ተኛችበት ሌሊት ሞተ። 20ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፣ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወሰደችው፤ ከዚያም የእኔን ልጅ ራሷ ታቅፋ፣ የሞተ ልጇን አምጥታ በዕቅፌ አደረገችው። 21በማግስቱም ልጄን ላጠባ ስነሣ እነሆ ሞቷል፤ ነገር ግን በማለዳ ብርሃን ትክ ብዬ ስመለከተው እኔ የወለድሁት ልጅ አለመሆኑን ተገነዘብሁ።”22ሌላዪቱም ሴት፣ “ነገሩ አንቺ እንደምትዪው አይደለም፤ የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለውም የእኔ ነው” አለች።የመጀመሪያዋ ሴት ግን አጠንክራ፣ “አይደለም! የሞተው የአንቺ፣ በሕይወት ያለው ግን የእኔ ልጅ ነው” አለች፤ በዚህ ሁኔታም በንጉሡ ፊት ተከራከሩ።23ንጉሡም፣ “ይህችኛዪቱ፣ ‘የእኔ ልጅ በሕይወት ያለው ነው፣ የአንቺ የሞተው ነው’ ትላለች፤ ያችኛዪቱ ደግሞ፣ ‘አይደለም የአንቺ ልጅ ሞቷል፣ በሕይወት ያለው የእኔ ነው’ ትላለች” አለ።24ከዚያም ንጉሡ፣ “እንግዲያውስ ሰይፍ አምጡልኝ” አለ፤ ለንጉሡም ሰይፍ አመጡለት። 25በዚህ ጊዜ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ልጅ ከሁለት ክፈሉና ለአንዷ ግማሹን፣ ለሌላዪቱም ግማሹን ስጡ” ብሎ አዘዘ።26በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች።ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች።27ከዚህ በኋላ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለመጀመሪያዪቱ ሴት ስጧት፤ አትግደሉት፤ እናቱ እርሷ ናት” አለ።28እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ የሰጠውን ፍርድ ሲሰሙ ፈሩት፤ ፍትሕ ለመስጠት የአምላክን ጥበብ የታደለ መሆኑን አይተዋልና።'1 ነገሥት 3:16-28
Embed this episode
NOW PLAYING
እንቁዬን በሌሊት አልጥልም / Gloria Aman
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.