EPISODE · Mar 14, 2026 · 1H 11M
ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ / ድንቅ ስብከት / {የጳውሎስ ሰንሰለት} prophet Tilahun Tsegaye
from Evangelist Elsabet Tasisa
'1የክርስቶስ ኢየሱስ ባሮች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፤ ከቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትና#1፥1 ወይም ተመልካች ጠባቂዎች ከዲያቆናት#1፥1 ዲያቆን የሚለው ቃል ኤጲስ ቆጶሳትን ወይም ሽማግሌዎችን በአገልግሎት የሚያግዙ ሰዎችን የሚያመላክት ሲሆን በተለያየ መልኩ በሮሜ 16፥1ና በ1ጢሞ 3፥8-12 ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። ጋራ በፊልጵስዩስ ላሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፤ 2ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። 3እናንተን ባስታወስሁ ቍጥር አምላኬን አመሰግናለሁ። 4ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁ ስጸልይ፣ በደስታ እጸልያለሁ፤ 5ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስካሁን ድረስ በወንጌል አገልግሎት ተካፋይ ሆናችኋልና። 6በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ። 7በልቤ ስላላችሁ እና በእስራቴም ሆነ ለወንጌል ስመክትና ሳጸናው ሁላችሁም ከእኔ ጋራ የእግዚአብሔር ጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፣ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰቤ ተገቢ ነው። 8በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር ሁላችሁንም ምን ያህል እንደምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው። 9ጸሎቴ ይህ ነው፤ ፍቅራችሁ በጥልቅ ዕውቀትና በማስተዋል ሁሉ በዝቶ እንዲትረፈረፍ፣ 10ይኸውም ከሁሉ የሚሻለውን ለይታችሁ እንድታውቁ፣ እስከ ክርስቶስም ቀን ድረስ ንጹሓንና ነቀፋ የሌለባችሁ እንድትሆኑ፣ 11ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ እንድትሞሉ ነው። 'ፊልጵስዩስ 1:1-11
Embed this episode
NOW PLAYING
ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ / ድንቅ ስብከት / {የጳውሎስ ሰንሰለት} prophet Tilahun Tsegaye
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.