EPISODE · Dec 24, 2025 · 1H
የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር
from Drum of Changes
“ፕሬዝዳንት ፑቲን አሁን ኢኮኖሚውን በማረጋጋት እና ተጨባጭ እድገት ወደሚታይበት ደረጃ ማድረስ ችለዋል … ዛሬ በሩሲያ እያየን ያለነው የኢኮኖሚ ለውጥ ብቻ ሳይሆን፣ የፑቲንን አመራር ተጽእኖ ፈጣሪነት ነው” ሲሉ ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪው ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አዉሮፓዉያን ዛሬም በከሸፈ የቁማር መንገዳቸው ቢቀጥሉም የሩስያ ገናና ድል ግን ቀጥሏል። ”አውሮፓውያን በውጭ አገራት የተቀመጡ የሩሲያን ንብረት እና ገንዘብ በመውሰድ ለዩክሬን ለመስጠት ማሰባቸው የደቡቡ ዓለም ከአውሮፓውያን ጋር የሚኖረውን አሰራር እንዲያጤን ቀጥተኛ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ አንዳለ ንጉሴ ናቸው። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዓመቱ ማጠቃለያ መግለጫ ወቅት ያነሷቸዉን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ ከዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ እና ከደቡብ ለደቡብ ትብብር አንፃር የሚኖራቸዉን አንድምታዎች እንቃኛለን። ለዚህም ዓለም አቀፍ የፖሊሲ አማካሪዉን ቆስጠንጢኖስ በርሁተስፋን (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩን አንዳለ ንጉሴን አነጋግረናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የአውሮፓ የከሸፈው ቁማር እና የሩሲያ ድል ፡- በፑቲን ወሳኙ ዓመታዊ ንግግር
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.