EPISODE · Mar 17, 2025 · 8 MIN
የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ
from Evangelist Elsabet Tasisa
ኤፌሶን 6:10-18[10] በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ። [11] የዲያብሎስን የተንኰል ሥራ መቋቋም ትችሉ ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ። [12] ምክንያቱም ተጋድሏችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦች፣ ከሥልጣናትና ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው። [13] ክፉው ቀን ሲመጣ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ዕቃ ልበሱ፤ ሁሉን ከፈጸማችሁ በኋላ ጸንታችሁ መቆም ትችላላችሁና። [14] እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ዝናር ታጥቃችሁ፣ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣ [15] በሰላም ወንጌል ዝግጁነት እግሮቻችሁ ተጫምተው ቁሙ። [16] ከእነዚህም ሁሉ ጋር፣ የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነትን ጋሻ አንሡ፤ [17] የመዳንን ራስ ቍር አድርጉ፤ የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው። [18] በሁሉ ዐይነት ጸሎትና ልመና፣ በማንኛውም ሁኔታ በመንፈስ ጸልዩ፤ ይህንም በማሰብ ንቁ፤ ስለ ቅዱሳንም ሁሉ በትጋት ልመና አቅርቡ።
Embed this episode
NOW PLAYING
የእግዚአብሔርን እቃ ጦር ሁሉ ልበሱ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.