EPISODE · Dec 31, 2025 · 1H
የእስራኤል እውቅና ለሶማሊላንድ ፦ የሶማሊያ ተቃዉሞ እና የቀጣናው እጣፈንታ
from Drum of Changes
ሶማሌላንድ ከእስራኤል ያገኘችው የሀገርነት እውቅና በተወሰነ ደረጃ ህጋዊነትን እንድታገኝ ቢያስችላትም፣ ከሶማሊያ፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሌሎች ሀገራት እየተሰጠው ያሉ ምላሾች በመጭው ጊዜያት የግዛት አንድነት ጥያቄዎች ማዕከላዊ ሆነው እንደሚቆዩ ያሳያል። "እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችው እውቅና ከዓለም አቀፍ ሕግ ይልቅ፣ ፖለቲካዊ አንድምታው ጎልቶ ይታያል … በቀጣናው ሶማሊላንድ አዲስ ተዋናይ ሆና ብቅ ልትል ትችላለች፣ አዲስ ዓይነት የኃይል አሰላለፍም ሊፈጠር ይችላል" ሲሉ ጠበቃ፣ የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ሦስት ጉዳዮችን እንመለከታለን። በቀዳሚው ጥንቅራችን ከሰሞኑ እስራኤል ለሶማሊላንድ የሰጠችዉን የሀገርነት እውቅና እንስተን አንድምታዎቹን እንመለከታለን። ለዚህም ኢትዮጵያዊውን ጠበቃ እና የዓለም አቀፍ ሕግ ባለሞያ አንዷለም በእውቀቱን አነጋግረናል። በሁለተኛው ጥንቅራችን ደግሞ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን በማንሳት በኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባ የሚኖረዉን ሚና እንቃኛለን። ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ተቋም ዋና ዳይሬክተር፣ የሺዓለም ገዛኸኝ (ዶ/ር) በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የኮምፒዉተር ሳይንስ ትመህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር፣ እና አቶ አበበ ፀጋዬ በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሰቲ የአይሲቲ ዋና ዳይሬክተርን አነጋግረናል። በመጨረሻው ጥንቅራችን ደግሞ የኢትዮጵያ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበር ዝግጅትን መነሻ አድርገን ብርጋዴር ጄኔራል መሰረት ጌታቸው፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የመጀመሪያ ዲቪዚዮን የከባድ ጥገና ማዕከል ምክትል አዛዥ ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡትን ገለፃ ወደእናንተ እናደርሳለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
Embed this episode
Ready to play
የእስራኤል እውቅና ለሶማሊላንድ ፦ የሶማሊያ ተቃዉሞ እና የቀጣናው እጣፈንታ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.