EPISODE · Jan 27, 2026 · 1H
የጋራ ሀብቶች እና የጋራ ዕጣ ፈንታዎች፦ ሉዓላዊነትን እና ትብብርን እንደገና ማጤን በአፍሪካ
from Drum of Changes
"አፍሪካውያን ሉዓላዊነትን የምንገልፅበት እና የምንረዳበት መንገድ ምዕራባውያን በ'ዌስታፋሊያ' ሰምምነት መሰረት ከሚነግሩን የሉዓላዊነት እሳቤ የተለየ ነው።[...] አፍሪካውያን የወረስነውን የምዕራቡን ዓለም ሉዓላዊነት መንገድ በመተዉ [...] ወደውስጥ መመልከት፣ የጋራ ሀብቶቻችንን በጋራ ስለመጠቀም ማሰብ አለብን።" ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ዛሬ በድረም ኦቭ ቼንጅስ ቀዳሚ ጥንቅራችን 'አፍሪካ ሀብቶቿን በጋራ ለመጠቀም ትችል ዘንድ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ያለውን ምዕራብ ተኮር እሳቤ መተው ስትችል ነው' የሚል መከራከሪያ ከሚያቀርቡት እና በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና የአፍሪካ ጥናት ማዕከል ዳይሬክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ ያደርጋል። በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደውን የከንቲባዎች ምክክር መነሻ በማድርግ የአፍሪካ ከተሞችን እና የእድገት ጉዟቸዉን ይዳስሳል። ለዚህም ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የመጡ እንግዶች ጋር ቆይታውን ያደርጋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የጋራ ሀብቶች እና የጋራ ዕጣ ፈንታዎች፦ ሉዓላዊነትን እና ትብብርን እንደገና ማጤን በአፍሪካ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.