EPISODE · Mar 11, 2026 · 1H
የኩባ ውለታና የአፍሪካ ምላሽ ? ጊዜ ያነሳው ጥያቄ
from Drum of Changes
ኩባ ለአፍሪካ የነፃነት እና የሉዓላዊነት ትግል የከፈለችው መስዕዋትነት የአህጉሪቱ የማይረሳ የታሪክ አንዱ ገጽ ነው። “ኩባ [...] የህልውና ፈተና በገጠመን ወቅት መስዋዕትነት በመክፈል ከጎናችን ቆማለች፤ አፍሪካውያን ግን በተዋለልን ልክ ለኩባ ደርሰንላታል ወይ?” ሲሉ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ይጠይቃሉ። ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5/2018 ዓ.ም. “ህብረት ከግላኮማ ነፃ ለሆነች ዓለም” በሚል ጭብጥ የዓለም የግላኮማ ሳምንት ይከበራል። “ግላኮማ ታማሚዎች ሳያውቁት የማይቀለበስ የዓይነ ስውርነት የሚያስከትል በሽታ ቢሆንም፣ የግንዛቤ እጥረት ሁኔታውን አክብዶታል” ሲሉ የግላኮማ ስፔሻሊስቷ ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል። በዛሬው የ ድሪም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፣ ስለ ግላኮማ በሽታ ከስፔሻሊስትና ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር አበባ ተክለጊዮርጊስ ጋር እንመክራለን። በሁለተኛው ክፍላችን ደግሞ፣ ስለ ኩባ የታሪክ መስዋዕትነት ከኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አስተባባሪ አቶ አበበ አያሌው ጋር እንቆያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የኩባ ውለታና የአፍሪካ ምላሽ ? ጊዜ ያነሳው ጥያቄ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.