EPISODE · Jan 29, 2026 · 1H
የሰው ልጅ ታሪክ አዲስ መልክ፦ በኢትዮጵያ የተገኘው 2.6 ሚሊዮን ዓመት የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ስለማንነታችን ምን ይነግረናል ?
from Drum of Changes
“ ከቆዳችን በታች ሁላችንም አንድ አይነት መሆናችንን እናያለን … ፖለቲከኞች ለራሳቸው ዓለማ ከዚህ የተለየ ኃቅ ሊያሳዩን የመቻል አቅማቸዉን አሳንሼ ግን ማየት አልፈልግም … ነገር ግን አሜሪካ፣ አፍሪካ፣ ሩሲያ ወይት ሌላ ቦታ ብንኖር ሰዎች ሁሉ አንድ ዘር ነን” ሲሉ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ፣ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ ተመራማሪ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ልዩ የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን እጅግ የተሟላ እና ጥንታዊ የሆነችውንና ከ3.3 ሚሊየን በላይ እድሜ ያላት የሰላምን (አውስትረሎፒቲከስ አፋረንሲስን) እና በቅርቡ የተገኘውን የ 2.6 ሚሊየን እድሜ ባለቤት ፓራንትሮፐስ ጨምሮ የብዙ ግኝቶች እና ምርምሮች ባለቤት፣'ምድረ ቀደምት (ላንድ ኦቭ ኦሪጅን)' የሚለውን መጠሪያ ያስተዋወቁ እና በቺካጎ ዩኒቨርሲቲ የቀደምት ሰው ዘር መነሻ እና አመጣጥ (ፓሊዪአንትሮፖሎጂስት) ተመራማሪ መምህር፣ ፕሮፌሰር ዘረሰናይ ዓለምሰገድን በእንግድነት ጋብዟቸዋል።በቅርቡ ያገኙትን ቅሪተአካል (ፓራንትሮፐስ) መነሻ በማድረግ ስለሰው ዘር አመጣጥ ፣ኢትዮጵያ ስላላት ማዕከላዊ ስፍራም እናወጋለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የሰው ልጅ ታሪክ አዲስ መልክ፦ በኢትዮጵያ የተገኘው 2.6 ሚሊዮን ዓመት የሰው ልጅ ቅሪተ አካል ስለማንነታችን ምን ይነግረናል ?
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.