PODCAST · news
ሳምንታዊ ዝግጅቶች - የአሜሪካ ድምፅ
by VOA
የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
Episodes
-
በኢትዮጵያ ላይ የተሰናዳው የአሜሪካ ሴኔት ረቂቅ ህግ - ማርች 31, 2022
የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ 'በኢትዮጵያ ሰላምና ዲሞክራሲን ለማበረታታት' በሚል ርዕስ የቀረበውን S-3199 የተሰኘ ረቂቅ ተመልክቶ ማሻሻያዎች ካደረገ በኃላ አሳልፏል። ለመሆኑ ይህ ኮሚቴው ያሳለፈው ውሳኔ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምን አንድምታ አለው? ረቂቅ ህጉ በቀጣይ የሚያልፍባቸው ሂደቶች ምን ይመስላሉ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ በአሜሪካን ሀገር ሆነው ጉዳዩን የሚከታተሉ ተንታኞችን አነጋግረናል።
-
በጉጂ በ30 የምርጫ ጣብያዎች ተቋርጦ የነበረዉ ምርጫ ዛሬ ተካሂዷል - ጁላይ 09, 2021
በአንድ የግል ተወዳዳሪ አቤቱታ ምክንያት ምርጫ ቦርድ ያቋረጠዉ የነጌሌ ምርጫ ዛሬ ተከናውኗአል። አቶ አማኑኤል ብርሃኑ የነገሌ የምርጫ ክልል አስተባባሪ የምርጫው ሂደት በ30 የምርጫ ጣብያዎች መከናወኑን ለአሜርካ ድምጽ ገልጸዋል። በምርጫዉ ከ150 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ተሳትፈዋል ብለዋል፣ ገልሞ ዳዊት ተጨማሪ አለዉ።
-
ሕወሓት ለድርድር ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች - ጁላይ 07, 2021
በሕወሐት የሚመራው የትግራይ ክልል መንግሥት፣ የተኩስ ማቆም ስምምነት ለማድረግ፣ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ። የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ፣ የኤርትራና የአመራ ክልል ሃይሎች ከክልሉ እንዲወጡ፣ ከክልሉ አለም አቀፍ በረራ ማካሄድን ጨምሮ፣ ሁሉም መገናኛ እንዲከፈቱ፣ ወደ ትግራይ ማንኛውም የፌደራል መንግስት፣ የጸጥታ አካል እንዳይገባ የሚሉ ቅድመ ሁኔታዎች ይገኙባቸዋል።(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
-
ኢትዮጵያ ያስመረቀችው የሳተላይት መቀበያ ፋይዳው ምንድነው? - ሜይ 17, 2021
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ የብዝሃ ሳተላይት መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ቅዳሜ ግንቦት 7፣ 2013 ዓ.ም አስመርቋል። የሳተላይት መረጃ መቀበያው በመስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን በቀጣይ ለሚደረጉ የሕዋ ሳይንስ ስራዎች ትልቅ መንደርደሪያ እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ በዚህ ዙሪያ ከኢትዮጵያ የስፔስ ማኅብረሰብ ስራአስኪያጅ ቤዛ ተስፋዬ ጋር አጠር ያለቆይታ አድርገናል፡፡
-
በተቋሟ የሚሰሩ ሴቶችን የምታበቃው የተፈጥሮ የውበት መጠበቂያ አምራቿ ወጣት - ሜይ 08, 2021
ዮርዳኖስ ጉሽ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት የተማረች ሲሆን በተለያዩ የብሮድካስት እና የህትመት ሚዲያዎች ላይም ሰርታለች፡፡ በአሁን ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያን ስኪን ቢውቲ ሲክሪትስ የተሰኘ የተፈጥሮ የቁንጅና ግብዓቶች የሚያመርት ተቋም ከፍታለች፡፡ ዮርዳኖስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አብረዋት የሚሰሩ 12 ሰራተኞቿ የራሳቸውን ሱቅ ከፍተው እንዲወጡ በማድረግም ሴቶችን ማብቃት ላይ የራሷን ሚና እየተጫወተች ትገኛለች፡፡
-
ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021
ወ/ሮ ዮዲት አምሃ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ በአሜሪካ ሃገር በሴቶች እና ብቸኛ ስደተኛ ህጻናት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በጾታ እኩልነት ዙሪያም ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡ ኮቪድ 19 በከፍተኛ ሁኔታ የአገልግሎት ዘርፉን ማጥቃቱና በዚህም የተነሳ በዘርፉ ውስጥ ያሉ እጅግ ብዙ ሴቶች መቸገራቸውን አንስተው የመፍትሄ አማራጮችን እና የተለያዩ ሴቶችን ያበቃሉ ያሏቸውን እድሎች ጠቁመዋል፡፡
-
ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021
የነገ ተስፋ ሕጻናት ለአዲስ አበባ፤ የተሰኘው መርሃግብር በአ.አ አስተዳደር የህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት መርሃግብር በኩል በ 10 ክፍለከተማዎች ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት እድሜ ላሉ ሕጻናት የሚያገለግል የመጽሃፍት ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ቢሮው በጎፍቃደኞች በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ሕጻናት የሚያገለግሉ መጽሃፍትን እንዲለግሱም ጥሪ አድርጓል፡፡ የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገብረመድህን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡
-
በየጊዜው የሚደረጉ የጽዋ፣ ጀማ እና የጸሎት መርሃግብሮች ሴቶችን ለማብቃት ምን ሚና አላቸው? - ማርች 20, 2021
ከ160 ዓመት በፊት በጉራጌ ዞን እንደኖረች እና ለሴቶች መብት መከበር ትታገል እንደነበር በሚነገርላት በቃቄ ውርድወት ስም የተሰየመው መብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) የሚያዘጋጀው 'ውርድወት የምርምር መርሃግብር' ወይም ፌሎውሺፕ የመጀመሪያ ምርምር ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በየጊዜው በሴቶች የሚደረጉ የጽዋ ፣ ጀማ እና የጸሎት ቡድኖች በሴቷ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያ ሕይወት ዙሪያ ያላቸውን ሚና ላይ ያተኮረ ነው፡፡
-
ግጭት በሕይወታቸው ላይ ያሳደረውን ስቃይ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይናገራሉ - ማርች 13, 2021
በሳምንቱ መግቢያ ላይ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከብሯል፡፡ በኢትዮጵያም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ግጭቶች ለሴቶች እና ህጻናት መፈናቀል፣ ለአካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት እንዳጋለጧቸው ይታወቃል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዎች ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት ኮቪድ 19 እና ግጭት በሴቶች ላይ ያሳደረውን ጫና ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል አሰባስበው የላኩትን ዘገባ ቆንጂት ታዬ እና ኤደን ገረመው እንደሚከተለው አጠናቅረውታል፡፡
-
ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021
በአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ተቋማት የቤተሰብ ምጣኔ 2020(ሃያ ሃያ) የዓለም አቀፍ የትብብር እና ተነሳሽነት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 67 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሃገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ምንም እንኳን በድሃ ሃገራት ውስጥ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚነት ቢጨምርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን የቤተሰብ ምጣኔ እቅዱን በተገቢው መንገድ ለማስኬድ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ አመላክቷል፡፡
-
ከግብርና ተረፈምርቶች የሚሰራ የወረቀት ጥቅል ፋብሪካ በማቆም ላይ ያለችው ወጣት - ማርች 09, 2021
ቤተልሄም ደጀኔ ለወረቀት አምራች ድርጅቶች የሚያገለግል ጥቅል ወይም ፐልፕ ሙሉ ለሙሉ ከግብርና ተረፈ ምርቶች የሚያመርት ዛፍሪ የተሰኘ ተቋም መስራች እና ስራአስኪያጅ ናት፡፡ ከ5 ዓመታት በፊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የተመረቀችው ይቺ ወጣት በዋናነት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረቷን ያደረገች ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ከዛፍ ምርት ነጻ የሆነ እና በተጨማሪም ለአነስተኛ ገበሬዎች ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ሊሆን የሚችል ምርት ለማቅረብ ዝግጅቷን ጨርሳለች፡፡
-
ደራሽ እርዳታ እየተሰጠ ካለበት የሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል የተጠናቀረ ዘገባ - ዲሴምበር 18, 2020
ደራሽ እርዳታ እየተሰጠ ያለበትን ጨምሮ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የተጓዘው አካባቢዎቹ ዘጋቢያችን የተመለከተው ከተከታዩ ዘገባ ያዳምጡ።
-
ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በተፈሪ ዓለሙ አንደበት - ዲሴምበር 17, 2020
እውቁ ተዋናይ እና ጸሐፌ ተውኔት ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሰሰ በ84 ዓመታቸው አረፉ። ተስፋዬ ገሰሰ በኢዮጵያ ዘመናዊ የመድረክ ትወናን ካስተዋወቁት ቀዳሚ ተጠሪዎች መካከል እንደነበሩ ይታወቃል። መለስካቸው አመሐ ዘገባ አለው።
-
የአምነስቲ ሪፖርት በማይካድራ ጭፍጨፋ - ኖቬምበር 13, 2020
ማይካድራ ውስጥ በመቶዎች ሲቪሎች ላይ ጭፍጨፋ ለመካሄዱ ማስረጃ እንዳለው አምነስቲ አስታወቀ።ድርጊቱ በትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ስለመፈፀሙ መረጃዎች ያመለክታሉ ሲል ያነጋገራቸውን እማኞች ቃል ጠቅሶ በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።የትግራይ ክልል በትግራይ ሕዝብ ላይ የተጀመረው ከባድ የዘር ማጥፋት ወረራን ለመቀጠል ሆን ተብሎ የተሰራጨ የሐሰት ዜና ነው ብሎታል። በአካባቢው የነበረ የህወሃት ልዩ ሃይልና ሚሊሻ የፈጸመው ጅምላ ጭፍጨፋ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል:
-
ለድሬደዋ ተማሪዎች አራት አማራጮች ቀረቡ - ኦክቶበር 03, 2020
ድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአስተዳደሩ ትምህርት ለማስጀመር አራት ዓይነት አማራጮችን ሊጠቀም ማሰቡን አስታወቀ። የአስተዳደሩ ትምሕርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የህጻናትን ደህንነት ባስጠበቀ መልኩ ትምህርት እናስጀምራለን ብለዋል። መግለጫውን የተከታተለው አዲስ ቸኮል ዝርዝር ዘገባ አለው።
-
ከለላ ለልጆች ህጻናት ከጾታዊ ጥቃት ለመታደግ የሚውል ነጻ መርጃ - ኦገስት 19, 2020
በኢትዮጵያ በሕጻናት እና በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል እና በወላጆች ፣ በአሳዳጊዎች ፣ በመምህራን እንዲሁም በአጠቃላይ በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለውን ንቃት ለመጨመር የሚያስችል ከለላ የተሰኘ መምሪያ በበጎ ፈቃደኞች ተዘጋጅቶ ለህዝብ ቀርቧል፡፡ ኤደን ገረመው የከለላ ለልጆች መስራች እና አዘጋጅ የተግባቦት ባለሞያ እና አማካሪ የሆነችውን ሰላም ሙሴን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡
-
በቤኒሻንጉል ጉምዝና በጋምቤላ ክልሎች ኮቪድ-19 እየበዛ መምጣቱን የጤና ቢሮዎቹ አስታውቀዋል - ኦገስት 15, 2020
ቤኒሻንጉል ጉምዝ ውስጥ 378 ሰዎች፤ ጋምቤላ ውስጥ ደግሞ 645 ሰዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን የክልሎቹ የጤና ቢሮዎች ኃላፊዎች ገልፀዋል።ጋምቤላ ውስጥ ሰባት ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት መሞታቸው ተነግሯል።
-
የየመን ሁቲ አማጺያን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሀገራቸው አባረሩ፣ በርካታዎችን ገደሉ - ኦገስት 15, 2020
የየመን ሁቲ አማጺያን በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ከሀገራቸው ለማስወጣት በከፈቱት ተኩስ በርካታ ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው ሂውማን ራይትስ ዎች ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የተኩስ ጥቃቱን ለማምለጥ ወደ ሳውዲ ድምበር ለመግባት የሞከሩ በርካታ ስደተኞች ላይ የሳውዲ ድምበር ጠባቂ ወታደሮች ተኩስ በመክፈታቸው ተጨማሪ ኢትዮጵያኖች መሞታቸውንም መግለጫው አካቷል።
-
የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤና ሌሎች ተከሳሾች በዋስ ተለቀቁ - ኦገስት 15, 2020
የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ እና በርሳቸው መዝገብ የተከሰሱ ሃያ ሰዎች በ2 ሚሊዮን ብር ዋስ ተለቅቀዋል። በዋስ መለቀቃቸውን ተከትሎ ዞኑ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ መሆኑን የዞኑ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
-
እስራኤል እና የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ግንኙነታ ለመቀጠል መስማማታቸውን ፕሬዚዳንት አሳሰቡ - ኦገስት 14, 2020
እስራኤል እና የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ግንኙነታ ለመቀጠል መስማማታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት አስታወቁ።ይህ ስምምነት የአብራሃም ውል የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል እስራኤል እ ኤ አ በ 1948 ነጻ ሃገር ሆና ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ከዚህኛው በፊት ከአረቦች ጋር የሰላም ስምምነት ያደረገችው ሁለት ጊዜ ብቻ ነው።
-
የትግራይ ክልል መንግስትለ1568 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወስነ - ኦገስት 14, 2020
የክልሉ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ እንዳስታወቀው የኮረናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ተብሎ የይቅርታ መምርያ የሚያሟሉ የህግ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተወስኗል::
-
በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ከዐስር በላይ ኢትዮጵያውያን በኮቪድ-19 ሞቱ - ኦገስት 14, 2020
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መስፋፋት ከጀመረ አንስቶ እስካሁን ባለው ጊዜ እዚያ በስደተኛነት ይኖሩ የነበሩ ከአሥር በላይ ኢትዮጵያዊያን በበሽታው ምክንያት መሞታቸው ተነግሯል።
-
በኮሮናቫይረስ ምክንያት ደም ባንክ አደጋ ውስጥ ውድቋል - ሜይ 08, 2020
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በህብረተሰቡ ውስጥ በፈጠረው ፍራቻ ምክንያት የደም ለጋሾች ቁጥር እጅጉን ቀንሷል።ይህም በጤና ተቇማት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቇል። በተለይ ብስፋት የደምልገሳ ይካሄድባቸው የነበሩት ትምህርት ቤቶች መዘጋትና ከቫይረሱ ጋር ተያይዘው የወጡ መመሪያዎች ለደም ለጋሾችመመናመን አስተዋፅኦ አድርገዋል።
-
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠው ይሆናል በሚል ከተጠረጠሩ ሰዎች የሚወሰደው ናሙና እንዴት ይመረመራል? - ማርች 19, 2020
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠው ይሆናል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎች የሚወሰደው ናሙና እንዴት ይመረመራል? ውጤቱን ለማወቅስ ስንት ቀን ይወስዳል?
-
በኢትዮጵያ የነጥሎ ማቆያ ጣቢያዎች ይዘት ምን ይመስላል? - ማርች 18, 2020
ለኮረና ቫይረስ ተጋልጠዋል በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ነጥሎ ማቆያ ጣቢያዎች ይዘት ምን ይመስላል? ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለሞያ ጠይቀን ያጠናቀርነውን ዘገባ ተከታተሉ።
-
ኦፌኮ ቀነ ገደብ ያለው ሁለተኛ ማስጠንቀቂያ ከምርጫ ቦርድ ተላከለት - ጃንዩወሪ 31, 2020
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአቶ ጃዋር መሐመድን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሁኔታን እንዲያረጋግጥ ቀነ ገደብ የተቀመጠለት ሁለተኛ ደብዳቤ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ጻፈ። ኦፌኮ በበኩሉ ጉዳዩ በሕጉ መሠረት እልባት እንዲያገኝ እናደርጋለን ብሏል። (ዝርዝሩን ያዳምጡ)
-
የምዕራብ ወለጋ የፀጥታ ስጋት እና የአምነስቲ መግለጫ - ጃንዩወሪ 31, 2020
“ሰብዓዊ መብትትን የሚጥሱ ሰዎች ላይ ለምን እርምጃ ተወሰደ? የሚል ተቃውሞ ማሰማት እጅግ አሳዛኝ ነው” - አቶ ታዬ ደንዳአ
-
በድሬዳዋ ከተማ አዲስ የተቃዋሚ ፓርቲ ተመሰረተ - ኦክቶበር 16, 2019
ለሶማሌ ሕዝብ ነጻነትና ዴሞክራሲ እንደሚታገል ያስታወቀው አዲሱ ፓርቲ ቅንጅት ለዴሞክራሲና ለነጻነት ይሰኛል። የፓርቲው መስራች ጉባዔ እስከስኞ ድረስ ይቀጥላል ተብሏል። ፓርቲው ዋና መቀመጫውን በጅግጅጋ እንደሚያደርግና በድሬዳዋና አዲሰበባም ቅርንጫፎች እንደሚኖሩት ገልጿል።
-
የኦነግ ሸማቂዎች በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች መግደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ - ኦክቶበር 16, 2019
ባለፈው ቅዳሜ በቦረናና በምስራቅ ጉጂ ስድስት ሰዎች በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሸማቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ከመካከላቸው የፀጥታ ጠባቂ ሚሊሺያዎችና ነዋሪዎች እንዳሉባቸው የአካባቢው አስተዳደር ገልጿል።
-
የስደተኞችን መብት ለማስከበር በአዲስ አበባ ምክክር ተደረገ - ኦክቶበር 16, 2019
ኢትዮጵያ ለስደተኞች መጠለያ ከመሆን ጎን ለጎን ስደተኞቹ እንደ ማንኛውም ዜጋ መብታቸው ተከብሮ በሀገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ እና ሠርተው መኖር እንዲችሉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው ሲል የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ገልጿል። ኤጀንሲው ዛሬ በአዲስ አበባ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል።
-
ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ - ኦክቶበር 16, 2019
ከፈረሰው የሰገን አከባቢ ሕዝቦች ዞንና ከመዋቅር ጥያቄ ጋር በተገናኘ በደቡብ ክልል ቡርጂ ልዩ ወረዳ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች መገደላቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተፈጠረው በወረዳ በነያ በተሰኘ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ሲሆን መንስኤው የመዋቅር ጥያቄ መሆኑን ነዋሪዎች ለቪኦኤ በስልክ ተናግረዋል። የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ሪፖርት ልኮልናል።
-
ከ30 በላይ የሶማሌ ተወላጆች በአፋር ታጣቂዎች እንደተገደሉበት የሶማሌ ክልል ገለፀ - ኦክቶበር 15, 2019
የሶማሌ ክልል መንግሥት ከአፋር ክልል በሚነሱ ታጣቂዎች ጥቃት ካለፈው ታኅሣሥ ጀምሮ ከ270 በላይ ንጹሀን ዜጎች ተገድለዋል አለ። ባለፈው ቅዳሜ ተከስቶ በነበረው ግጭትም ከ30በላይ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በሦሥት ቦታዎች መገደላቸውን ገልጿል። የሲቲ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዑመር አብዲ የመገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ ዘገባ እያቀረቡ አይደለም ሲሉ ወቅሰዋል። በተያያዘ በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ልዩ ልዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።
-
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የረሃብ አድማውን ቀን አራዘሙ - ኦክቶበር 15, 2019
አዲሱን የምርጫና የፓርቲዎች ሕግ የተቃወሙ ፓርቲዎች ነገና ከነገ በስቲያ እናደርጋለን ብለው የነበረውን የረሃብ አድማ ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል።
-
በእስር ላይ የሚገኙት የአብን አመራሮች ጉዳይ - ኦክቶበር 15, 2019
በእስር ላይ የሚገኙት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)አመራሮችና አባላት ለአራት ቀናት ያህል በርሃብ አድማ ላይ ቆይተው ዛሬ ምግብ መጀመራቸው ተገለፀ። በፖሊስ አባላት ማስፈራሪያና እየደረሰባቸውና የፍርድ ሂደቱም በአግባቡ እየታየ አለመሆኑ እንደሆነ የፓርቲው ሊቀ መንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ተናግረዋል። ከአመራሮቹ መካከል የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ በለጠ ካሳና የምክር ቤት አባል አቶ ሲሳይ አልታሰብ ይገኙበታል።
-
የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች አስተያየት በጠ/ሚ አብይ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ - ኦክቶበር 15, 2019
የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዲዮስ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
-
የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች አስተያየት በጠ/ሚ አብይ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ - ኦክቶበር 15, 2019
የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የአምቦ ከተማ ዘጋቢያችን ናኮር መልካ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
-
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች አስተያየት በጠ/ሚ አብይ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ - ኦክቶበር 15, 2019
የደሴ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የወሎው ዘጋቢያችን መስፍን አራጌ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
-
የድሬደዋና የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች አስተያየት - ኦክቶበር 15, 2019
ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የተሰጠው የኖቤል ሽልማቱን ለመደገፍ እሁድ ዕለት በተለያዩ ቦታዎች ከተደረጉት ሰልፎች መካከል በድሬደዋ እና በአምቦ ከተማ የተሳተፉ ሰዎች የሰጡት አስተያየት።
-
የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አስተያየት - ኦክቶበር 15, 2019
በኢትዮጵያ የሚገኙ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ የሰጡት አስተያየት።
-
የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች አስተያየት በጠ/ሚ አብይ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ - ኦክቶበር 15, 2019
የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የባህርዳሯ ዘጋቢያችን አስቴር ምስጋናው በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
-
የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች አስተያየት በጠ/ሚ አብይ የኖቤል ሽልማት ዙሪያ - ኦክቶበር 15, 2019
የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በተመለከተ የሰጡት አስተያየት። የመቐሌው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አፅብሃ በዕለፍ ተቀደም አግኝቶ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች የሰጡትን አስተያየት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
-
በዋግ ኽምራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ - ኦክቶበር 14, 2019
ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሁለት ቀናት ልዩነት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
-
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቱርክ ላይ ማዕቀብ ሊጣልባት ይችላል እያሉ ነው - ኦክቶበር 14, 2019
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ሰሜን ሶሪያ ውስጥ የሚዋጉትን ኩርዶች ሲረዱ የነበሩትን አሜሪካውያን ወታደሮች በማስወጣታቸው ሲነቀፉ ሰንብተዋል ። አሁን ደግሞ በአካባቢው ወታደራዊ ዘመቻዋን እያፋፋመች ባለችው በቱርክ ላይ ማዕቀብ ሊጣልባት ይችላል ለዚያም ዝግጅት ተደርጉዋል እያሉ ናቸው።
-
በአፋር 17 ሰዎች መገደላቸውን የአፋምቦ ወረዳ አስተዳዳሪ ገለፁ - ኦክቶበር 14, 2019
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳይታ ዱብቲ አካባቢ የውጭ አገር መታወቂያና ተሽከርካሪ ይዘዋል የተባሉ ታጣቂዎች ከትላንት በስቲያ ሰነዘሩት በተባለው ጥቃት በርካታ ሰዎች መሞታቸውንና መቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
-
ባልደራስ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ - ኦክቶበር 11, 2019
የአዲስ አበባ ባለደራ ምክር ቤት መሆኑን የሚናገረው ቡድን በስድስት ነጥቦች ዙሪያ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ።
-
አዲሀን ከአዴፓ ጎን እንደሚቆም አስታወቀ - ኦክቶበር 11, 2019
የአማራ ክልል ገዢ ፓርቲ (አዴፓ) የህዝቡን ህልውና ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ከጎኑ እንደሚቆም ተፎካካሪው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ (አዲሀን) አስታወቀ።
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
Loading similar podcasts...