PODCAST · news
ፍልሰት ወደ አውሮፓ ሞት ወይም ሽረት - የአሜሪካ ድምፅ
by VOA
የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
Episodes
-
የአፍሪካ የፍልሰተኞች ፍሰት ገፅታ በትክክል እንደማይገለጽ ተጠቆመ - ኦክቶበር 17, 2020
የአፍሪካ የፍልሰተኞች ፍሰት ገፅታ ብዙውን ጊዜ በትክክል እንደማይገለጽ የአፍሪካ ህብረትና ዓለማቀፍ የፍልሰት ድርጅት ያወጡት አብይ ዘገባ ያመለክታል። አብዛኞቹ አፍሪካውያን ፍልሰተኞች ባህሮቻችንና ውቅያኖሶችን በብልሹ ጀልባዎች ለማቋረጥ የሚሞክሩ ሳይሆኑ የአፍሪካን ድንበሮች በየብስ የሚሻገሩ ናቸው ይላል ዘገባው። የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ሳይመን ማርክስ ከአዲስ አባባ የላከው ዘገባ ዘርዝሩን ይዟል።
-
ኢትዮጵያውያን ከሊባኖስ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ - ሜይ 28, 2020
ሊባኖስ ውስጥ የነበሩ 337 ኢትዮጵያዊያን የሚያስፈልጋቸው የጉዞ ሰነድና ማስረጃዎች ተመቻችተውላቸው ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።
-
በሞዛንቢክ ከተቆለፈባቸው ኮንቴነር ውስጥ የተረፉ ኢትዮጵያውያን - ሜይ 23, 2020
ሞዛንቢክ ላይ የጭነት መኪና ጀርባ ባለ ኮንቴይነር ውስጥ ተቆልፎባቸው ለሞት ከተዳረጉት 64 ኢትዮጵያውያን መካከል በህይወት የተርፉት 11 ሰዎች ባለፈው አርብ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሲሞን ማርክስ ከአዲስ አበባ ያደረሰንን ሪፖርት ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።
-
"ለስድስት ወራት ድጋፍ ስላላገኘን ለችግር ተጋልጠናል" - ተፈናቃዮች - ኤፕሪል 24, 2020
ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በሎ ጀገንፎይ የተመለሱ አንዳንድ ተፈናቃዮች ለስድስት ወራት ድጋፍ ስላላገኘን ለችግር ተጋልጠናል ሲሉ ተናገሩ።
-
"ከቀናት በኋላ ቤተሰቦቼን የምመግበው ነገር የለኝም" - ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች - ኤፕሪል 03, 2020
በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሀገሩ መንግሥት የኮሮና ቫይረስን ለመቆጣጠር ባሳለፈዉ ውሳኔ ምክንያት የዕለት ጉርስ ለማግኘት እየተቸገሩ መሆቸውን ተናግረዋል። መንግሥት ማንም ከቤቱ እንዳይወጣ ባሳለፈው ውሳኔ ከእጅ ወደ አፍ ኑሮን የሚገፉ ስደተኞች ቤተሰቦቻቸውን የሚመግቡት አጥተው ለረሃብ መጋለጣቸውን ለአሜርካ ድምፅ ገልፀዋል። የመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም በትውልደ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ እገታ መብዛቱን ይናገራሉ።
-
ቤቲ ጂ የተመድ የስደተኞች ጉዳይ የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሆና ተሾመች - ማርች 10, 2020
ቤቲ ጂ በተለያዩ የሙዚቃ ስራዎቿ ትታወቃለች፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜም ዓለም አቀፍ እውቅና እያተረፈች የምትገኝ ወጣት ሙዚቀኛም ናት፡፡ በባለፈው ሳምንት ታዲያ፤ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞቸ ጉዳይ ኮሚሽን የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟታል፡፡ ኤደን ገረመው ከቤቲ ጂ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጋለች፡፡
-
ፍልሰት ወደ አረብ ሀገራት - ዲሴምበር 18, 2019
በደቡብ ወሎ በኩል ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገሮች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሊሸጋገሩ የነበሩ ቁጥራቸው ወደ አንድ ሺህ የሚሆን ሰዎች ተይዘው ወደ የተነሱባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ መደረጉን የዞኑ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ አስታውቋል። ወደ አረብ ሃገሮች ለመሸጋገር ሲሞክሩ የተያዙት ከኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ወጣቶች መሆናቸውን መምሪያው ያለፉ አምስት ወራት እንቅስቃሴውን አጣቅሶ በሰጠው መግለጫ ላይ አመልክቷል።
-
40 የሚሆኑ ሜዲቴራኒያን ባሕርን ሊያቋርጡ ሲሞክሩ ሰመጡ - ኦገስት 28, 2019
ሜዲቴራኒያን ባሕርን ሊያቋርጡ የነበሩ አርባ የሚሆኑ ሰዎች ትናንት /ማክሰኞ/ መስጠማቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታወቀ። ሰዎቹ የተነሱት ከሊብያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በስተምሥራቅ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኝ አል-ኾምስ ከተማ ነበር።
-
ቀይ ባሕርን ሲያቋርጡ የሰጠሙ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ቤተሰቦች ተረዱ - ኤፕሪል 16, 2019
ከትግራይና ከሌሎችም አካባቢዎች ተሰድደው ቀይ ባሕር በማቋረጥ ላይ ከነበሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች የተሣፈሩባት ጀልባ ባለፈው ሣምንት በመገልበጧ ከአርባ በላይ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ሰጥመው መሞታቸውና ቤተሰቦቻቸውም መርዶው እንደተነገራቸው ተገለፀ።
-
ከጠረፍ አደጋ ተርፎ - ማረፊያ ፍለጋ - ኤፕሪል 10, 2019
ሲ- አይ (Sea-Eye) የተባለው የጀርመን የሰብዓዊ ደርጅት ቡድን በሊብያ ጠርፍ ከአደጋ ያተረፋቸውን 64 ፍልሰተኞች ለስድስት ቀናት ያህል ማረፍያ ወደብ ፍለጋ ሲዘዋወር በቆየው የመድህን መርክብ ውስጥ ሰንብተዋል።
-
የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች በስደት ዙሪያ ተወያዩ - ፌብሩወሪ 12, 2019
የአፍሪካ ኅብረት 32ኛ የመሪዎች ጉባዔ ስደትን ከምንጩ ለማድረቅ መስማማቱን አስታውቋል። ስደትና መፈናቀል ከአፍሪካ ሃገሮች ግንባር ቀደም ፈተናዎችም አንዱ ነው ተብሏል።
-
በቱኒሲያ የባህር ወደብ አቅራቢያ ስደተኞችን የጫነ አነስተኛ ጀልባ ሰመጠ - ጁን 04, 2018
ትላንት ማምሻውን ከቱኒሲያ የባህር ወደብ አምስት ማይል ርቀት እንደተጓዘ ነው 180 ፍልሰተኞችን የጫነው ጀልባ የሰመጠው። እስከአሁን በጀልባዋ ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ 68ቱ ከሞት ተርፈዋል። 60 ፍልሰተኞች አስክሬን ተገኝቷል። የተቀሩት 52 ስደተኞችን ማፈላለጉ ቀጥሏል።
-
የእስራኤል ውሳኔ በኤርትራውያን እና ሱዳናውያን ስደተኞች ላይ - ጃንዩወሪ 25, 2018
ተከስተ የማነ ከሰባት ዓመት በፊት ሀገሩን ኤርትራን ለቆ የሊቢያ በረሃን አቋርጦ እስራኤል የገባው በፖለቲካ ስደት እንደሆነ ይናገራል።
-
"የስደተኛ አባት"..አባ ሙሴ ዘርዓይ በበጎ ምግባራቸው ለሽልማት ታጩ - ጃንዩወሪ 09, 2018
የአባ ሙሴ ዘርዓይ ስም የሊቢያን በረሃና የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን ለሚገቡ ስደተኞች በተለይም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስደተኞች ትልቅ ዋጋ አለው። በዓለማችን አፍሪካውያንን ከችግር ለመታደግ የሚጥሩ በጎ አድራጊ ግለሰቦችን በመሸለም የሚታወቀውና ስፔን ማድሪድ በየአመቱ በሚካሄደው የሙኖ ኔግሮ (MUNDO NEGRO) ሽልማት አባ ሙሴ ለመሸለም ታጭተዋል።
-
ስማቸው "የስደተኛ አባት"..አባ ሙሴ ዘርዓይ በበጎ ምግባራቸው ለሽልማት ታጩ - ጃንዩወሪ 09, 2018
የአባ ሙሴ ዘርዓይ ስም የሊቢያን በረሃና የሜዲትራኒያንን ባህር አቋርጠው ወደ ጣልያን ለሚገቡ ስደተኞች በተለይም ለኢትዮጵያውያንና ለኤርትራውያን ስደተኞች ትልቅ ዋጋ አለው። በዓለማችን አፍሪካውያንን ከችግር ለመታደግ የሚጥሩ በጎ አድራጊ ግለሰቦችን በመሸለም የሚታወቀውና ስፔን ማድሪድ በየአመቱ በሚካሄደው የሙኖ ኔግሮ (MUNDO NEGRO) ሽልማት አባ ሙሴ ለመሸለም ታጭተዋል።
-
የዓለም የስደተኞችና የተፈናቃዮች ቀን - ዲሴምበር 18, 2017
ዛሬ ዕለቱ ከቀያቸው ተፈናቅለው፤ በዓለም ዙሪያ የተበተኑ ሚሊዮኖች የሚታሰቡበት ነው።
-
አፍሪካ በጋዜጦች - ኦገስት 11, 2017
ሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች ሁለት መቶ ሰማኒያ ፍልሰተኞችን በየመን ባህር ውስጥ ገፍትረው መጣላቸው ታወቀ።
-
በደቡባዊ ሶማሊያ የኮሌራ ወረርሽኝና ርሃብ - ሜይ 17, 2017
በአንድ የሶማሊያ ክልል በድርቅ የተነሣ ግማሽ ሚሊዩን ሕዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል፣ ሀገሪቱ የችጋር አፋፍ ላይ ነች - ተብሏል፡፡
-
በአፍሪካ ቀንድ፣ የመን፣ ናይጄሪያና ደቡብ ሱዳን የረሃብ አደጋ መባባሱ ተገለፀ - ኤፕሪል 12, 2017
በአፍሪካ ቀንድ የመን ናይጄሪያና ደቡብ ሱዳን ብዛት ያለው ሰው ረሃብ የሚያልቅበት አደጋ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ መጥቷል ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ዓለምቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች እያስጠነቀቁ ነው።
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
HOSTED BY
VOA
CATEGORIES
Loading similar podcasts...