Skip to content
ጤና - የአሜሪካ ድምፅ podcast artwork

PODCAST · news

ጤና - የአሜሪካ ድምፅ

by VOA

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

Publisher-supplied feed metadata · PodParley refreshed Apr 15, 2026 · Source feed

Episodes

  1. ራስን ማጥፋት የአይምሮ ጤና ቀውስ ውጤት ነው - ጃንዩወሪ 18, 2023

    ከቅርብ ግዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ራሳቸውን ስለማጥፋታቸው በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በተደጋጋሚ ይሰማል። ማህበራዊ ሚዲያው ከቀደመው ጊዜ የበለጠ መረጃዎችን እንድንሰማ ማድረጉ እንዳለ ሆኖ፣ ራስን ማጥፋትን በተመለከተ ጥናት ያጠናው የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በየእለቱ 30 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉና በዚህም ምክንያት ቢያንስ 150 ሰዎች ቀሪ ህይወታቸውን የሚወዱት ሰው ራሱን በማጥፋቱ በሚያስከትለው መዘዝ ጥላ ስር እንደሚያሳልፉ አመልክቷል።

  2. አፍሪካ ሲዲሲ በአፍሪካ አራተኛው ዙር የኮቪድ ግርሻ አሳስቦኛል አለ - ዲሴምበር 24, 2021

    የአፍሪካ በሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠሪያ ተቋም አፍሪካ ሲዲሲ አመት በዓል እየደረሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት በአህጉሪቱ እየተመዘገበ ያለው አዲሱ የኮቪድ 19 ስርጭት አሳስቦኛል አለ፡፡ የማዕከሉ ዳይሬክተር ጆን ንኬንጋሶንግ የአፍሪካ ሃገራት ክትባትን ላይ አስገዳጅ ደንብ እንዲያወጡ እየገፋን እንገኛለን ብለዋል፡፡

  3. አዲሱ የኮቪድ ዝርያ እና የዩናይትድ ስቴትስ ጥብቅ መመሪያ - ዲሴምበር 04, 2021

    ዩናይትድ ስቴትስ አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ኦሚኮርን በሃገሪቱ መገኘቱ ካረጋገጠች ከ24 ሰዓት በኋላ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ዓለም አቀፍ ተጓዦችን በተመለከተ ጥብቅ መመሪያዎችን ያወጡ ሲሆን በሃመላው ሃገሪቱ በመጓጓዣዎች ላይ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መመሪያዎችም ለተራዘመ ጊዜ እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ ፕሬዘዳንቱ በተጨማሪም 200 ሚሊየን የኮቪድ 19 ክትባቶች በቀጣይ ወር ለሌሎች ሃገራት እንደሚለገሱም ቃል ገብተዋል፡፡

  4. የጽንስ ማቋረጥ እሰጥ አገባ በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት - ዲሴምበር 02, 2021

    በትላንትናው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጽንስ ማቋረጥን በሚደግፍ የግዛት ሕግ ዙሪያ ክርክሮችን የሰማ ሲሆን፤ በጽንስ ማቋረጥ ዙሪያ ለብዙ አስርት ዓመታት የዘለቀውን ክርክር ተከትሎ የተቃውሞ ድምጾች ሲስተጋቡ ውለዋል፡፡

  5. የ2021 የዓለም አቀፍ የፊጎ አዋርድ ተሸላሚ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማናቸው? - ኖቬምበር 01, 2021

    ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር መቅደስ ዳባ በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህጸን እና የጽንስ ህክምና ሃኪም እንዲሁም በኢትዮጵያ የጽንስ እና የማሕጸን ሃኪሞች ማህበር ፕሬዘዳንት ናቸው፡፡ በቅርቡም ዓለም አቀፍ የጽንስ እና የማህጸን ፌደሬሽን በአለም ዙሪያ በዘርፉ በምርመር አስተዋጽኦ አድርገዋል በሚል የጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ዓ.ም ከመረጣቸው ባለሞያዎች መሃከል አንዷ በመሆን የፊጎ አዋርድ/ሽልማት ወስደዋል፡፡

  6. የህፃናትን ስነ-ባህሪና እድገት የሚያጠናው የመጀመሪያው ተቋም - ኦክቶበር 07, 2021

    ጎጆ የህሙማን መጠለያ ተቋምን በመመስረት በሺዎች ለሚቆጠሩ አቅመ ደካማ ህሙማን ድጋፍ እየሰጠች የምትገኘው ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የህፃናት ስነ-ባህሪና የእድገት ሁኔታን የሚያጠና ተቋም በጥቁር አምበሳ ሆስፒታል ስር እንዲጀመር ያደረገች የህፃናት ሀኪም ናት።

  7. የአዲስ አበባ መምህራን ስራ ከመጀምራቸው በፊት እንዲከተቡ ስለሚያደርገው መመሪያ ምን ይላሉ? - ኦክቶበር 02, 2021

    ጥቅምት 1 ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የአ.አ ትምህርት ቢሮ መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር አባላት ከስራቸው አንጻር ከፍተኛ የሆነ የኮቪድ 19 ተጋላጭነት እንዳላቸው በመገንዘብ እራሳቸውንም ሆነ ቤተሰባቸውን ከበሽታው እንዲጠብቁ ለማስቻል አስገዳጅ የሆነ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ አስገዳጅ የሆነ መመሪያ ወጥቷል፡፡ በዚህ ጉዳይ ምምህራኑ ምን ይላሉ?

  8. ለተቸገሩ ህሙማን እና አስታማሚዎች ማረፊያ የሆነችው ሀኪም - ሴፕቴምበር 03, 2021

    አሜሪካ በየአመቱ ለአፍሪካ ወጣት መሪዎች በምታዘጋጀው የማንዴላ ፌሎውሺፕ በዚህ አመት ከኢትዮጵያ ከተመረጡት መሀከል ጎጆ የህሙማን መጠለያ ተቋምን የመሰረተችው ዶክተር ሰላሜነሽ ፅጌ አንዷ ናት። ተቋሙ ከኢትዮጵያ የገጠር ከተሞች ለተጨማሪ ህክምና አዲስ አበባ የሚመጡ፣ ማረፊያ በማጣትና ገንዘባቸውን ለህክምና በመጨረስ ለጎዳና ህይወት የሚዳረጉ ህሙማንን በጊዜያዊነት የሚያስጠልል ሲሆን ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ከ81 ሺህ በላይ የሚሆኑ ህሙማን ረድቷል።

  9. 'የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች' ቆይታ ከአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር ዮናስ ላቀው ጋር - ሴፕቴምበር 01, 2021

    ብዙ ሰዎች በአማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል ታክመው ከዳኑ በኋላ እዛ መታከማቸውን መናገር ይፈራሉ ይላል ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድንገት እነዚህ ሰዎች ከሰው ለየት ያለ ነገር ሲናገሩም ሆነ ሲሰሩ ቢታዩ “እሱ/ እሷ ድሮስ ከአማኑኤል አይደል እንዴ የመጡት?” ይባላሉ ይላል ዶ/ር ዮናስ ላቀው፡፡ እንደውም ከነጭራሹም እዛ የምትሰሩት እራሳቹ ‘እብዶች አይደላቹ እንዴ?’ ተብዬም አውቃለሁ ይላል፡፡ ሙሉውን ቃለምልልስ ያድምጡት፡፡

  10. 'ዓለምን በቀጣይ ከሚያሰጓት ወረሽኞች ለመከላከል የሚያጠናው ግሎባል ዋን ሄልዝ' ቆይታ ከፕሮፌሰር ወንድወሰን አበበ ጋር - ኦገስት 26, 2021

    ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢንሺየቲቭ ወይም አንድ የዓለም ጤና ተነሳሽነት በአሜሪካ ሃገር በሚገኘው በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የተመሰረተ ሲሆን ዓላማውም ከአካባቢ፣ ከእንሣት እና ከሰዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ ኮቪድ 19፣ ኢቦላ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ በነፍሳት ፣ በውሃ፣ በዓየር..የሚመጡ በሽታዎችን በኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሜክሲኮ፣ ብራዚል እና ታይላንድ...እየተንቀሳቀሰ የሚያጠና ነው፡፡ ይሄ ተነሳሽነት ከተመሰረተ ዘንድሮ 10ኛ ዓመቱ ይዟል፡፡

  11. "የፓርኪንሰን ችግር ሰፊ ቢሆንም ስራችንን ከአዲስ አበባ ውጪ እንዳናስፋፋ የበጀት ችግር አለብን" ክብራ ከበደ - ጁላይ 15, 2021

    የፓርኪንሰን ሕሙማን ድጋፍ ማኅበር በኢትዮጵያ ከተመሰረተ አስራ ሁለት ዓመት ይሆነዋል፡፡ የድርጅቱ መስራች ክብራ ከበደ ትሰኛለች፡፡ ማኅበሩ ከተመሰረተ ጀመሮ በበሽታው ዙሪያ ግንዛቤን ለመፍጠር የእግር ጉዞዎች፣ የውይይት ምሽቶች፣ የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ሲሆን ለሕሙማኑም የምክር፣ የገንዘብ እና የሕክምና ድጋፍ እንዲያገኙ በማመቻቸት እየሰራ ይገኛል፡፡

  12. 'ከሰኔ 30 በኋላ ምን ይመጣ ይሆን?' ዘላቂ መፍትሄ ያጣው የሃኪሞች ስራ አጥነት - ጁን 26, 2021

    ኢትዮጵያ እጅግ አነስተኛ የሆነ የጤና ባለሞያ ካለባቸው ሃገራት መሃከል ናት፡፡ ይሁንና በሃገሪቱ የህክምና ባለሞያዎች ስራ አጥ ናቸው፡፡ ከወራት በፊት በአማራ ክልል የሕክምና ባለሞያዎች የስራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በዚህ መሰረትም የጤና ሚኒስቴር እና የክልሉ የጤና ቢሮ እስከ ሰኔ 30 ድረስ የሚቆይ የ3 ወራት የስራ እድል አመቻችተው ነበር፡፡ ይሁንና ከቀናት በሁላ የኮንትራት ጊዜያቸው ስለሚያልቅ የስራ አጥነት ስጋት ውስጥ ናገጥሟቸዋል፡፡

  13. የመጀመሪያው የድንገተኛ እና አደጋ ጽኑ ህክምና መሪ እቅድ ምን ይመስላል? - ጁን 15, 2021

    በኢትዮጵያ ለመጀምሪያ ጊዜ የድንገተኛ እና ጽኑ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እና ተደራሽነት ለመጨመር የሚያስችል የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ ባለፈው ሳምነት የጤና ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡ መሪ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግም 200 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የድንገተኛ እና ጽኑ ህክምና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር አለኝታ ገብረየስ ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል፡

  14. "ሱስ ያለኝን ሁሉ ካሳጣኝ በኋላ እራሴን ላጠፋ ሞክሬ ነበር" ከሱስ ሕይወት የወጣ ወጣት - ጁን 11, 2021

    በትምህርት ላይ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ፣ ለመዝናናት ወይም ስራ በማጣት ከሚመጣ ጭንቀት እና ድብርት ለመውጣት በሚል እና በተለያዩ ሌሎች ምክንያቶች ወጣቶች ወደ ሱስ ዓለም ይገባሉ፡፡ ይሁንና ከጊዜ በኋላ ከገቡበት መውጣት እየፈለጉም ሲያቅታቸው እና ሲፈተኑ ይታያል፡፡ ኤደን ገረመው ሁለት ከዚህ ቀደም በሱስ ሕይወት ውስጥ የነበሩና በሱስ የተነሳ ሕይወታቸውን እስከማጥፋት ከደረሱ በኋላ የወጡ ወጣቶችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

  15. 'ወጣቶችን ከሱስ ህይወት ለመታደግ በነጻ አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም ድጋፍን ይሻል' ሲስተር ይርገዱ ሃብቴ - ጁን 05, 2021

    የመጨረሻ ልጃቸው አስከፊ የሆነ የሱስ ሕይወት ገብቶ ከ10 ዓመት በላይ ከባድ ጊዜ አሳልፈዋል፡፡' ልጄ ጠፋ' ብዬ አምላኬን ብዙ ጊዜ አማርሬዋለሁ ይላሉ፡፡ ያ ቀን አልፎ ታዲያ ልጃቸው ከነበረበት ወጥቶ አሁን ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሶላቸዋል፡፡ ይሄ የሕይወት ተሞክሯቸው ግን በሱስ የተጎዱ ወጣቶችን እየሰበቡ በማሳረፍ የጤና እና የስነ ልቦና ድጋፍ የሚያገኙበትን አዲስ ሕይወት የእጽ እና የአልክሆል እና የሱሰኝነት ህክምና ማገገሚያ ማዕከልን ወደ መመስረት መርቷቸዋል፡፡

  16. የኩላሊት ህክምና አገልግሎት ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ከተሞችን ለማዳረስ ያሰበው ኢትዮጵያን ኪድኒኬር - ጁን 04, 2021

    ኢትዮጵያን ኪድኒ ኬር ከተመሰረተ ስምንት ወራት ሆነው፡፡ ተቋሙ በኩላሊት ህክምና ላይ ግንዛቤን ለመፍጠር፣ እንዲሁም ጥናቶችን ለመስራት እና ከአዲስ አበባ ውጪ ላሉ ህሙማን የእጥበት አገልግሎት እና የህክምና ተደራሽነትን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ የተቋሙ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር እሴተ ጌታቸው ይናገራሉ፡፡

  17. ያልተዘመረላቸው ጀግና ተሸላሚ ዶ/ር ትልቅሰው ተሾመ ማናቸው? - ጁን 03, 2021

    ዶ/ር ትልቅሰው ተሾመ በኢትዮጵያ በስኳር ህመም እና በሌሎች የጤና ችግሮች ምክንያት የሚከሰት የዓይነስውርነት ችግረን ለመቅረፍ ከ14 ዓመት በፊት የመጀመሪያውን የሬቲና ህክምና ያስጀምሩ ሃኪም ናቸው፡፡ እስከዛሬ ድረስም ከ7000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የቀዶ ጥገና አገልግሎትን በመስጠት ህሙማንን ወደ ውጪ ሃገር ከሚደረጉ ጉዞዎችና ከዓይነስውርነት እየታደጉ ይገኛሉ፡፡ የአሜሪካ የዓይን ህክምና አካዳሚ በጎርጎሮሳዊያኑ 2020 ዓ.ም ያልተዘመረላቸው ጀግና ሲል ሸልሟቸዋል፡፡

  18. በአሜሪካ የቤት ለቤት ማዋለድ አገልግሎት የምትሰጠው ትግስት ቶሌራ - ሜይ 06, 2021

    ትግስት ቶሌራ በአሜርካ ሃገር በአሪዞና ግዛት ተክሰን ከተማ ነዋሪነቷን ያደረገች አዋላጅ ሃኪም ናት፡፡ በምትኖርበት በተክሰን ከተማም ኦዳ በረዝ የተሰኘ የቤት ለቤት የማዋለድ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም የከፈተች ሲሆን እስካሁን ድረስም ወደ 60 የሚጠጉ ሕጻናትን አዋልዳለች፡፡

  19. በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት የተከተቡ ሰዎች ምን ይላሉ? - ሜይ 04, 2021

    ኢትዮጵያ የካቲት 28 2013 ዓ.ም 2.2 የአስትራዜኒካ ክትባት በመጋቢት አጋማሽ ደግሞ 300,000 የሳይኖፋርም ክትባቶችን ያገኘች ሲሆን የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት መሰጠት ሂደትም ጀምራለች፡፡ በሃገሪቱ ያለው የክትባት አሰጣጥ ሂደት ምን ይመስላል? የኅብረተስቡስ ግንዛቤ ስትል ኤደን ገረመው በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ እና የብሔራዊ የክትባት አስተባባሪ የሆኑትን ዶ/ር ሙሉቀን ዮሃንስ፣ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

  20. ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021

    ወ/ሮ ዮዲት አምሃ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ በአሜሪካ ሃገር በሴቶች እና ብቸኛ ስደተኛ ህጻናት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በጾታ እኩልነት ዙሪያም ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡ ኮቪድ 19 በከፍተኛ ሁኔታ የአገልግሎት ዘርፉን ማጥቃቱና በዚህም የተነሳ በዘርፉ ውስጥ ያሉ እጅግ ብዙ ሴቶች መቸገራቸውን አንስተው የመፍትሄ አማራጮችን እና የተለያዩ ሴቶችን ያበቃሉ ያሏቸውን እድሎች ጠቁመዋል፡፡

  21. ኮቪድ 19 የፈጠረው የስራ ጫና እና ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች እያሳለፉት ያለው ጊዜ - ኤፕሪል 01, 2021

    ያለፈውን አንድ ዓመት ከኮቪድ 19 ጋር ሲታገሉ የከረሙት ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች ዘንድሮም ወረሽኙ በማገርሸቱ ከባድ የስራ ጫና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ ሃኪሞች በስራ ጫና ለሚመጣ ጭንቀት፣ ድብርት እና መዳከም ወይም በእንግሊዘኛው በርን አውት መጋለጣቸው እየተነገረ ነው፡፡ በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞችም ከፍተኛ ለሆነ ጭንቀት፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ ድካም በመጋለጣቸው የተለያ ባህሪ ማዳበር፣ ማልቀስ እና ጭንቀት እንደ ታየባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አጋርተዋል፡፡

  22. ታዳጊ እናቶች እና ልጆቻቸውን ከጎዳና ላይ አንስቶ እራሳቸውን እንዲችሉ የሚረዳው መሰረት በጎ አድራጎት - ማርች 25, 2021

    ገና በለጋ እድሜዋ የቤተሰቧን ሕይወት ለማሻሻል ስትል ወደ ትዳር የገባቸው ወ/ሮ መሰረት አዛገ በልጅነቷ የልጅ እናት ብትሆንም ኑሮን ታግላ እራሷን አብቅታለች፡፡ ነገር ግን በለጋ እድሜ የልጅ እናት መሆን የሚያመጣውን ችግር ለመቅረፍ በጎዳና ላይ የወደቁ እናቶችን በመሰብሰብ እና መጠለያ በመስጠት የተሃድሶ መርሃግብር እንዲያገኙና በኋላም ቤት ተከራይተው እራሳቸውን ችለው እንዲወጡ ለመርዳት በመሰረት በጎ አድራጎት ድርጅት በኩል እየጣረች ነው፡፡

  23. በየጊዜው የሚደረጉ የጽዋ፣ ጀማ እና የጸሎት መርሃግብሮች ሴቶችን ለማብቃት ምን ሚና አላቸው? - ማርች 20, 2021

    ከ160 ዓመት በፊት በጉራጌ ዞን እንደኖረች እና ለሴቶች መብት መከበር ትታገል እንደነበር በሚነገርላት በቃቄ ውርድወት ስም የተሰየመው መብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) የሚያዘጋጀው 'ውርድወት የምርምር መርሃግብር' ወይም ፌሎውሺፕ የመጀመሪያ ምርምር ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በየጊዜው በሴቶች የሚደረጉ የጽዋ ፣ ጀማ እና የጸሎት ቡድኖች በሴቷ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያ ሕይወት ዙሪያ ያላቸውን ሚና ላይ ያተኮረ ነው፡፡

  24. "እራሳችንን ማወቅ እና ሁለንተናዊ ደህንነታችን ላይ መስራት ይኖርብናል" ዮፍታሄ ማን ያዘዋል - ማርች 18, 2021

    ዮፍታሄ ማን ያዘዋል የክሁል ሁለንተናዊ ዕድገት ማዕከል መስራች እና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የተመሰከረለት የዮጋ አሰልጣኝ ነው፡፡ ከአመታት በፊት በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የስነሕንጻ አርክቴክቸር ተማሪ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ እራሱን ለማወቅ እና የሚወደውን ነገር ለመስራት ይመራመር እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ዮፍታሄ በአሁን ሰዓት በክሁል ማዕከል ውስጥ የተለያዩ የዮጋ፣ የጥሞና፣ የቀናንነት እና እንዲሁም ልምድ የመለዋወጥ መርሃግብሮችን በማዘጋጀት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

  25. "ኮቪድ ሲመጣ የምንበላው ስላልነበረን አግብቻለሁ" የ17 ዓመት ወጣት - ማርች 12, 2021

    ሃብታም በአማራ ክልል በጎንደር ትክል ድንጋይ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ከኮቪድ 19 በፊት እናቷ ቤት ተከራይታላት ትምህርቷን ትከታተል ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ኮቪድ 19 ሲገባ ስራ በመጥፋቱ ምክንያት ቀድሞም ቢሆን እዚህ ግባ የማይባለው የእናቷ ድጎማ ጭራሹን ቆመ፡፡ "እናቴ እስከመቼ እንዲህ ትኖራለች? ኮቪድ ሲመጣ ስራ ቆም እንጂ ሆድ እህል መጠየቁን አያቆም ብዬ ለትዳር ስጠየቅ አይኔን አላሸሁም” ትላለች፡፡

  26. የኮቪድ-19 አንደኛ ዓመት - ማርች 11, 2021

    ኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ተብሎ በዓለም የጤና ተቋም ከታወጀ ልክ ዛሬ አንድ አመት ሆነው፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያለፈው አንድ ዓመት ኮቪድ-19ን በመከላከሉ ረገድ ምን ተሰራ፣ የክትባት ስርጭቱ ሂደት ምን ይመስላል በሚለው እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

  27. መንግስት በግጭት ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን እንዲከላከል የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ - ፌብሩወሪ 12, 2021

    ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ህዝቦች ሃብት ንብረታቸውን በመተው ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ሴቶችም መደፈራቸው ተሰምቷል፡፡ ሴታዊት የጾታ ንቅናቄ በግጭት ቀጠና እና በሃገር ውስጥ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለሴቶች ጥበቃ ቅድሚያ እንዲሰጥ እና ጥቃት ፈጻሚ አካላትም በተገቢው መንገድ ለህግ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡

  28. የኢትዮጵያ ሕክምና መረጃዎች ማዕከላዊ በሆነ መንገድ እንዲሰነዱ የሚያግዘው ወጣት - ፌብሩወሪ 09, 2021

    ኦርቢት ሄልዝ ከ4 ዓመታት በፊት በጳዚዮን ቸርነት የተቋቋመ የቴክኖሎጂ የጤና ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የጤና ስርዓት ማዕከላዊ በማድረግ የህሙማን መረጃ ሳይዘነጋና ሳይጠፋ እንዲሰነድ በተጨማሪም የታዘዙ መድሃኒቶች በተገቢው መልኩ እንዲከፋፍሉ በማድረግ ህሙማን በተለያዩ ህክምናዎች የሚያጠፏቸውን ጊዜና ገንዘብ እንዲሁም መጉላላት እንዲቀር እየሰራ ያለ ተቋም ነው፡፡

  29. በኮቪድ 19 ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴት ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እንዲመለሱ ልዩ ጥረት ያስፈልጋል ተባለ - ፌብሩወሪ 04, 2021

    በማላላ ፈንድ አማካኝነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሻምፒዮኖች በኩል የተሰራው እና ከ 1300 በላይ ቤተሰቦች የተሳተፉበት ጥናት ባለፈው ሳምንት ይፋ ሆኗል፡፡ በጥናቱ መሰረትም በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በድጋሚ በተከፈተበት በአሁን ሰዓት በሃገር ዓቀፍ ደረጃ ልጃገረዶች ላይ ያተኮረ እና ወደ ትምህርት ገበታቸው ሙሉ ለሙሉ እንዲመለሱ የሚያበረታታ አካሄድ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡

  30. "ሴት የህክምና ባለሞያዎች ለስራቦታ ጾታዊ ጥቃት ተጋላጮች ናቸው" ዶ/ር ሰናይት በየነ - ጃንዩወሪ 29, 2021

    የኢትዮጵያ ሴት ሃኪሞች ማህበር ከተመሰረተ 3 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን ሴት የህክምና ባለሞያዎች በስራ ገበታቸው ላይ የሚደርስባቸውን መገለል፣ የጾታ ጥቃት ለማስቀረት በተጨማሪም ባለሞያ ሴቶችን በአመራር ለማብቃት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ ሴት የህክምና ባለሞያዎች በህክምናው ዘርፍ ውስጥ ስላላቸው ሚና እና እንዲሁም ስለሚያጋጥሟቸው ችግሮች የኢትዮጵያ ሴት ሃኪሞች ማኅበር ፕሬዘዳንት እና በጤና ሚኒስቴር አማካሪ ዶ/ር ሰናይት በየነ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

  31. ስለ ኮቪድ 19 ክትባት ፦ቆይታ ከዶ/ር ኤርሚያስ በላይ ጋር - ዲሴምበር 10, 2020

    የኮቪድ 19 ክትባትን ለማግኘት ለወራት ሲደረግ የቆየው ምርምር መልካም ውጤቶችን እያስገኘ ነው። የዮናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እንዳስታወቀው 5 ዓይነት ክትባቶች የምርምር ሂደቱ ሶስተኛ ደረሣ ላይ ደርሰዋል። ለመሆኑ በዚህ ደረጃ ላይ ምን ዓይነት ተግባራት ይከናወናሉ? ከባለሙያ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል።

  32. ብርቱካናማ ዓለም የ16ቱ ቀናት ዘመቻ በድረገጾች ላይ እየተካሄደ ይገኛል - ዲሴምበር 03, 2020

    የጸረ ጾታዊ ጥቃት የ16 ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕዳር 15 ቀን ተጀመሯል፡፡ ዘመቻው ዘንድሮ ድጋፍ፣ ምላሽ፣ መከላከል እና ማሰባሰብ የሚሉ መሪ ቃላትን ይዟል፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ በየዓመቱ በሰፊው እንቅስቃሴ የሚያደርጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የየሎው ሙቭመንት አባላት ዘንድሮ በኮቪድ 19 እና በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ዘመቻውን በድረገጽ ላይ ብቻ ለማድረግ ተገደዋል፡፡

  33. የዘምቢል መልስ ዘመቻ ኢትዮጵያን ከፕላስቲክ ማጽዳት - ኖቬምበር 14, 2020

    ኤልሻዳይ ግርማ በአትላንታ ጆርጂያ የቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት የሶስተኛ ዓመት የአካባቢያዊ ምህንድስና ተማሪ እና የግሪን ኢትዮጵያ የድረገጽ እንቅስቃሴ መስራች ናት፡፡ የዘምቢል መልስ ኢትዮጵያን ከፕላስቲክ ከረጢቶች እና ምርቶች ነጻ በማውጣት አካባቢን የማጽዳት ዓላማ ይዞ የሚንቀሳቀሰ ሲሆን፤ ዘንቢልን የመሳሰሉ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውሉ እንዲሁም አርጅተው ሲጣሉ አካባቢን የማይበክሉ መገበያያዎችን ሰዎች እንዲጠቀሙ እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

  34. "ኢትዮጵያ ጾታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን እስከ እድሜልክ ድረስ ተወቃሽ የሚያደርግ የምዝገባ ስርዓት ልትጀምር ነው" - ኦክቶበር 29, 2020

    በኢትዮጵያ የጾታዊ ጥቃት ቁጥር ለመቀነስ በፍርድ ቤት ወንጀልኝነታቸው የተረጋገጡ ጥቃት አድራሾችን ማዕከላዊ በሆነ መልኩ የሚመዝግብ እና ከተመረጡ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎች ለማግለል የሚረዳ የብሄራዊ የጾታዊ ጥቃት አድራሾች ምዝገባ ሊጀመር ነው ተባለ፡፡ኤደን ገረመው በሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬተር የሆኑት አቶ አድነው አበራን እና የኢትዮጵያን ሴቶች ማህበራት ንቅናቄ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህንን አነጋራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡

  35. ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ቫይረስ ያላቸው ምላሽ ምን እንደሚመስል እና አመጋገባቸው አግዟቸው እንደሆን የሚያጠና ጥናት ይፋ ሆነ - ኦክቶበር 24, 2020

    የጤና ሚኒስተር ለአንድ ዓመት የሚቆይ የምርምር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል፡፡ ኮቪድ 19 ከሌሎች የአውሮፓ ሃገራቶች አንጻር በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ ያለው ጉዳት እንዴት ሊቀንስ ቻለ? ባህላዊ ሕክምና? የዓየር ንብረት? አመጋገብ ወይስ ሌላ የሚለውን ጥናቱ እንደሚያካትት እና ከ6 ሺ በላይ ሰዎች ላይ እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስተር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገረዋል፡፡

  36. የወባ ሣምንት - ኦክቶበር 20, 2020

    አማራ ክልል ውስጥ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከመቶ ሺ በላይ ሰው በወባ መያዙን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

  37. "በሰባት ወር ጊዜ ውስጥ ከ 5 ሚሊየን ብር በላይ እርዳታ መለገስ የቻለው የኢንስታግራም ገጽ" የእምቧ ቤተሰብ - ኦክቶበር 15, 2020

    የእምቧ ቤተሰብ ባለፉት 7 ወራት ውስጥ የተለያዩ ታዋቂ ግለሰቦችን በመጋበዝ እምቧ ማለት፣ መደነስ፣ ጥሬ ሽንኩርት መብላት የመሳሰሉ አዝናኝ እና አስቂኝ የሆኑ ፈተናዎችን በመፈተን ውርርድ እየተወራረዱ ገቢ ያሰባስባሉ፡፡ ገንዘቡም ተሰባስቦ ለተለያዩ ጉዳዮች እና ችግሮች መፍትሄ እንዲሆን ይደረጋል፡፡ በገጹ ገቢ ከተሰባሰበላቸው ግለሰቦች መሃከል አንዷ የሆነችውን መቅደስ ወ/ሚካኤል እና የቡድኑን መስራች ያሬድ ነጋሽ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

  38. "ሕጻናት የንግግር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ መምህራን እና ወላጆች ሃላፊነት አለባቸው" ሃና አበበ - ኦክቶበር 11, 2020

    ሲናገሩ መንተባተብ/መጎላድፍ ያላባቸው ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ በቁምነገር የመደመጥ እድላቸው በጣም አናሳ ነው በዚhም የተነሳ ብዙዎቹ ለስነልቦና ችግሮች ይዳረጋሉ፡፡ በዚህ ዙሪያ ይበልጥ ግንዛቤ ለመጨበጥ እና በኢትዮጵያስ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ለመቃኘት በመደበኛነት በኖርዌይ ኦስሎ ነዋሪ የሆኑትን የስነልሳን እና የቋንቋ ሃኪም ወ/ሮ ሃና አበበን ጋብዘናል፡፡

  39. ኢዘዲን ካሚል በቴክኖሎጂው ዘርፍ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዲሆን በአፍሪካን ኢኖቬሽን ዊክ ተመረጠ - ኦክቶበር 01, 2020

    የ12 ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው ኢዘዲን 34 የቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎችን አበርክቷል፡፡ ከእነዚህ ውስጥም በጸሃይ ሃይል በመጠቀም ከ60 ኪሎሜትር በላይ መጓዝ የሚችል ባለ3 እግር ተሽከርካሪ፣ ከሩቅ በመሆን ሌባን መቆጣጠሪያ፣ እንዲሁም ከንክኪ ውጪ ፈሳሽ ሳሙና የሚረጭ መሳሪያ እና በእጃችን ፊታችንን እንዳንነካ የሚያስታውስ የእጅ ብራስሌት/ጌጥ ሰርቷል፡፡ አፍሪካን ኢኖቬሽን ዊክ ይህን ወጣት የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ አምባሳደር ይሆን ዘንድ መርጦታል፡፡

  40. ፈለክ የፊት ማስክ የብቃት ማረጋገጫ አገኘ - ሴፕቴምበር 26, 2020

    ፈለክ ኖትቡክ ባለፉት አራት ዓመታት ከማተሚያ ቤቶች የሚጣሉ ወረቀቶችን መልሶ በጥቅም ላይ በማዋል ስራ ላይ ያተኮረ ተቋም ነው፡፡ ኖት ቡኮቹ ተወዳጅ ቢሆኑም ኮቪድ 19 እንደማንኛው የስራ ዘርፍ የራሱን ጫና አሳርፎበታል፡፡ ይህንን ጫና ለመቋቋም እና ለኮቪድ 19 መከላከል ላይ የራሳቸውን አስተዋጻኦ ለማበርከት ማምረት የጀመሩት የፊት ማስክ የብቃት ማረጋገጫ አግኝቷል፡፡ ኤደን ገረመው የድርጅቱን መስራች አቶ ሱሌማን ዳዊትን አነጋራለች፡፡

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

HOSTED BY

VOA

Produced by የአሜሪካ ድምፅ

CATEGORIES

Frequently Asked Questions

How many episodes does ጤና - የአሜሪካ ድምፅ have?

ጤና - የአሜሪካ ድምፅ currently has 50 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is ጤና - የአሜሪካ ድምፅ about?

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

How often does ጤና - የአሜሪካ ድምፅ release new episodes?

ጤና - የአሜሪካ ድምፅ has 50 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to ጤና - የአሜሪካ ድምፅ?

You can listen to ጤና - የአሜሪካ ድምፅ on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts ጤና - የአሜሪካ ድምፅ?

ጤና - የአሜሪካ ድምፅ is created and hosted by VOA.
URL copied to clipboard!