PODCAST · society
ባሕል - የአሜሪካ ድምፅ
by VOA
የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
Episodes
-
የጽንስ ማቋረጥ እሰጥ አገባ በዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት - ዲሴምበር 02, 2021
በትላንትናው ዕለት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍ/ቤት ጽንስ ማቋረጥን በሚደግፍ የግዛት ሕግ ዙሪያ ክርክሮችን የሰማ ሲሆን፤ በጽንስ ማቋረጥ ዙሪያ ለብዙ አስርት ዓመታት የዘለቀውን ክርክር ተከትሎ የተቃውሞ ድምጾች ሲስተጋቡ ውለዋል፡፡
-
እሬቻ ወይም የምስጋና በዓል - ሴፕቴምበር 16, 2021
የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ጸሐፊ አባገዳ ጎበና ሆላ ኢሬሳ የ2014 የእሬቻ ክብረ በዓል መስከረም 22 በአዲስ አበባ ከተማ "በሆራ ፊንፊኔ" እና መስከረም 23 በቢሾፍቱ "ሆራ አርሳዲ" እንደሚከበር ተናግረዋል። በዘንድሮ በዓልም በተሳታፊዎች ቁጥር ላይ ገደብ ሳይደረግ ሆኖም ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተገቢው ጥንቃቄ ተደርጎ እንደሚከበር አስታውቀዋል።
-
ቆሼ አካባቢ ለሚኖሩ እናቶች የስራ እድል የፈጠረችው የ'ቱባ ኢትዮጵያ ዲዛይን' መስራቿ ወጣት - ሴፕቴምበር 02, 2021
ቅድስት ተስፋዬ የቱባ ኢትዮጵያ ዲዛይን መስራች እና ስራ አስኪያጅ ናት፡፡ ከዓመታት በፊት የቆሼ አካባቢ ተደርምሶ የፈጠረው ሰብዓዊ አደጋ አካባቢን ለመጠበቅ ተመልሶ በጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ነገሮች ላይ እንድትሰራ አድርጓታል፡፡ አሁን ከክርና ከቆድ የተሰራ ቦርሳ ታመርታለች፡፡ ቦርሳው የሚስራበትን ክር ደግሞ በዛ አካባቢ የሚኖሩ እናቶች በቤት ውስጥ ሰርተው እንዲሰጧት በማድረግ ተጨማሪ ለእናቶቹ ገቢ አስገኝታለች፡፡
-
'የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮች' ቆይታ ከአእምሮ ሃኪሙ ዶ/ር ዮናስ ላቀው ጋር - ሴፕቴምበር 01, 2021
ብዙ ሰዎች በአማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል ታክመው ከዳኑ በኋላ እዛ መታከማቸውን መናገር ይፈራሉ ይላል ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድንገት እነዚህ ሰዎች ከሰው ለየት ያለ ነገር ሲናገሩም ሆነ ሲሰሩ ቢታዩ “እሱ/ እሷ ድሮስ ከአማኑኤል አይደል እንዴ የመጡት?” ይባላሉ ይላል ዶ/ር ዮናስ ላቀው፡፡ እንደውም ከነጭራሹም እዛ የምትሰሩት እራሳቹ ‘እብዶች አይደላቹ እንዴ?’ ተብዬም አውቃለሁ ይላል፡፡ ሙሉውን ቃለምልልስ ያድምጡት፡፡
-
ደብረ ታቦር - ኦገስት 20, 2021
ደብረ ታቦር ወይም ቡሄ ወይም ታቦሬ አንዳንድ ቦታ ደግሞ ኡኬ ይባላል። ህፃናት የሚያከብሩት የልጆች በዓል ነው። በኣሉ በባህላዊ አከባበሩ ምን እንደሚመስል ከአምቦ ነቀምቴና ኩዩ የታሪክና ባህል ምሁር እንዲሁም ስለበኣሉ የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ።
-
የቲያትር 100ኛ ዓመት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሲዘከር - ጁላይ 31, 2021
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የጎንደር ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበባት ክፍል ዘመናዊ ቲያትር በኢትዮጵያ የተጀምረበትን መቶኛ ዓመት በማሰብ ለሁለት ቀናት የቆየ መርሃግብር አካሂዷል፡፡ መርሃግብሩን የወልቂጤ፣ ደብረማርቆስ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበብ ክፍሎችም የተሳተፉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ቲያትር ጅማሮን አስታኮ በመላው ሃገሪቱ የቲያትር ጥበብ እንዲነቃቃ እና እንዲያድግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ስለቲያትር ቡድን አባላትም በቦታው ተገኝተው ውይይቱን ተካፍለዋል፡፡
-
"መልካም ወንዶችን በማበረታታት የሴቶችን እኩልነት ማፋጠን እንችላለን" አቶ ጌታአለም ካሳ - ጁላይ 08, 2021
የሴቶች እኩልነትን በጤናው፣ በትምህርት እና በተለያዩ ዘርፎች ውስጥ ለማካተት የተለያዩ ጥረቶች የሚደረጉ ሲሆን ሃገር በቀል የሆነው ሕይወት አትዮጵያ የሴቶች እኩልነትን ለማሳካት የወንዶች ማሳተፍ አስፈላጊነት ያምናል፡፡ ወንዶችን በሙሉ እንደ ጥቃት አድራሽ ከመውሰድ ይልቅም መልካሞቹን በማበረታታት እና ተምሳሌትነት በማድረግ እንዲሁም ለወንዶች እና የሃይማኖት አባቶች ስለሴቶች እኩልነት አስፈላጊነት እና ስነተዋልዶም ጭምር መረዳት የሚችሉበትን ሁኔታ ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡
-
ከ25 ዓመታት የአርት ስኩል ሞዴልነት ወደ ሰዓሊነት የመጣችው የሁለት ልጆች እናት- ፍቅርተ አያና - ሜይ 17, 2021
ፍቅርተ አያና ላለፉት 25 ዓመታት በአለፈለገ ሰላም የስነጥበብ ትምህርት ቤት አርት ስኩል ውስጥ በአካለ ተምሳሌት ሞዴልነት ክረምት ከበጋ ሳትል ለረዥም ሰዓት ያህል በአንድ ዓይነት ቅርጽ አንድ ቦታ ላይ ብቻ አተኩራ በማየት እድሜዋን አሳልፋለች፡፡የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ፍቅርተን በመሳል እጅግ ብዙ ታዋቂ ሰዓሊያን እጃቸውን አፍታተዋል፡፡ፍቅርተ አሁን ላይ ስዕል መሳል ጀምራለች፡፡ ይሁንና ደሞዟ ለቀለም፣ ለቡሩሽ እና ለሸራ የሚበቃ ባለመሆኑ ድጋፍ ያስፈለገኛል ትላለች፡፡
-
ታዳጊዎች ጠያቂ እንዲሆኑ በዓመት አንዴ በገጠር ከተሞች የሚጓዘው የአስትሮ ባስ ቡድን - ሜይ 08, 2021
አስሮ ባስ ኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች ከፈጠራ ባለሞያዎች፣ የጠፈር ምሁራን፣ አርቲስቶች ጋር የሚተዋወቁበት ዕድል የፈጠረ የጉዞ መርሃግብር ነው፡፡ ኤደን ገረመው ከመስራቹ ያብባል ታደሰ ጋር ያደረገችው ቆይታ እንዲህ ይደመጣል፡፡
-
በተቋሟ የሚሰሩ ሴቶችን የምታበቃው የተፈጥሮ የውበት መጠበቂያ አምራቿ ወጣት - ሜይ 08, 2021
ዮርዳኖስ ጉሽ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት የተማረች ሲሆን በተለያዩ የብሮድካስት እና የህትመት ሚዲያዎች ላይም ሰርታለች፡፡ በአሁን ሰዓት ደግሞ ኢትዮጵያን ስኪን ቢውቲ ሲክሪትስ የተሰኘ የተፈጥሮ የቁንጅና ግብዓቶች የሚያመርት ተቋም ከፍታለች፡፡ ዮርዳኖስ ባለፉት ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ አብረዋት የሚሰሩ 12 ሰራተኞቿ የራሳቸውን ሱቅ ከፍተው እንዲወጡ በማድረግም ሴቶችን ማብቃት ላይ የራሷን ሚና እየተጫወተች ትገኛለች፡፡
-
በአሜሪካ የቤት ለቤት ማዋለድ አገልግሎት የምትሰጠው ትግስት ቶሌራ - ሜይ 06, 2021
ትግስት ቶሌራ በአሜርካ ሃገር በአሪዞና ግዛት ተክሰን ከተማ ነዋሪነቷን ያደረገች አዋላጅ ሃኪም ናት፡፡ በምትኖርበት በተክሰን ከተማም ኦዳ በረዝ የተሰኘ የቤት ለቤት የማዋለድ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም የከፈተች ሲሆን እስካሁን ድረስም ወደ 60 የሚጠጉ ሕጻናትን አዋልዳለች፡፡
-
የጥበብ ንግድ ባንክ በሰዓሊ እና የፎቶ ባለሞያ ሌይኩን ናሁሰናይ - ኤፕሪል 22, 2021
ሰዓሊ ሌይኩን ናሁሰናይ ከሰሞኑም ዘጋርዲያን ወይም "ጠባቂ" የተሰኘ በ17ኛው መቶ ክፍለዘመን የኢትዮጵያ የእንጨት ስራዎች ላይ የተመሰረተ ልዩ መንፈሳዊ ስራዎችን ለዕይታ አቅርቧል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሰዓሊ፣ ገጣሚ እና ባለቅኔ ገ/ክርስቶስ ደስታ የግጥም ስራዎች ያካተተ እና የእራሱን የተለያዩ የስነጥበብ ስራዎች ስብስብ የያዘ አርንጓዴ የኪስ መጽሃፍ አሳትሟል፡፡ ቃለምልልሱ ለይኩን በአረንጓዴ መጽሃፉ ላይ ካሰፈረው የገብረክርስቶስ ግጥም ላይ ጥቂት ከሚያነብበት ይጀምራል፡፡
-
ኮቪድ-19 በሴቶች ሕይወት ላይ ያሳደረውን ጫና እና መፍትሄዎቹ - ቆይታ ከዮዲት አምሃ ጋር - ኤፕሪል 16, 2021
ወ/ሮ ዮዲት አምሃ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ በአሜሪካ ሃገር በሴቶች እና ብቸኛ ስደተኛ ህጻናት ላይ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በጾታ እኩልነት ዙሪያም ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ፡፡ ኮቪድ 19 በከፍተኛ ሁኔታ የአገልግሎት ዘርፉን ማጥቃቱና በዚህም የተነሳ በዘርፉ ውስጥ ያሉ እጅግ ብዙ ሴቶች መቸገራቸውን አንስተው የመፍትሄ አማራጮችን እና የተለያዩ ሴቶችን ያበቃሉ ያሏቸውን እድሎች ጠቁመዋል፡፡
-
ከአንድ እስከ 8 ዓመት እድሜ ያሉ ሕጻናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩ መጽሃፍትን የማሰባሰብ እና ማዕከል መክፈት መርሃግብር - ማርች 25, 2021
የነገ ተስፋ ሕጻናት ለአዲስ አበባ፤ የተሰኘው መርሃግብር በአ.አ አስተዳደር የህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት መርሃግብር በኩል በ 10 ክፍለከተማዎች ከአንድ እስከ ስምንት ዓመት እድሜ ላሉ ሕጻናት የሚያገለግል የመጽሃፍት ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ቢሮው በጎፍቃደኞች በዚህ የእድሜ ክልል ላሉ ሕጻናት የሚያገለግሉ መጽሃፍትን እንዲለግሱም ጥሪ አድርጓል፡፡ የመርሃግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ታቦር ገብረመድህን ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡
-
ኮቪድ 19 የፈጠረው ጎጆ የአሁነኛ ጥበብ ቆይታ መርሃግብር - ማርች 20, 2021
የአሁነኛ ጥበብ ምሽት ወይም ኮንቶፖራሪ ናይትስ ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በሶስት የጥበብ ባለሞያዎች የተጀመረ ሲሆን ወጣት የፈጠራ ሰዎች ስራ የማሳያ፣ የመቀናጃ እና እንዲሁም የሚያንጹ ሂሶች የሚቀበሉበትን መድረክ ፈጥሯል፡፡ ከመስራቾቹ መሃከል አንዱ የሆነው ዳዊት ሰቶ ከአሚሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ ነበረው፡፡
-
በየጊዜው የሚደረጉ የጽዋ፣ ጀማ እና የጸሎት መርሃግብሮች ሴቶችን ለማብቃት ምን ሚና አላቸው? - ማርች 20, 2021
ከ160 ዓመት በፊት በጉራጌ ዞን እንደኖረች እና ለሴቶች መብት መከበር ትታገል እንደነበር በሚነገርላት በቃቄ ውርድወት ስም የተሰየመው መብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) የሚያዘጋጀው 'ውርድወት የምርምር መርሃግብር' ወይም ፌሎውሺፕ የመጀመሪያ ምርምር ውጤቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ጥናቱ በየጊዜው በሴቶች የሚደረጉ የጽዋ ፣ ጀማ እና የጸሎት ቡድኖች በሴቷ ስነልቦናዊ እና ኢኮኖሚያ ሕይወት ዙሪያ ያላቸውን ሚና ላይ ያተኮረ ነው፡፡
-
ግጭት በሕይወታቸው ላይ ያሳደረውን ስቃይ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ይናገራሉ - ማርች 13, 2021
በሳምንቱ መግቢያ ላይ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተከብሯል፡፡ በኢትዮጵያም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍል ያሉ ግጭቶች ለሴቶች እና ህጻናት መፈናቀል፣ ለአካላዊ እና ስነልቦናዊ ጥቃት እንዳጋለጧቸው ይታወቃል፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢዎች ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በማስመልከት ኮቪድ 19 እና ግጭት በሴቶች ላይ ያሳደረውን ጫና ከተለያየ የሃገሪቱ ክፍል አሰባስበው የላኩትን ዘገባ ቆንጂት ታዬ እና ኤደን ገረመው እንደሚከተለው አጠናቅረውታል፡፡
-
"ኮቪድ ሲመጣ የምንበላው ስላልነበረን አግብቻለሁ" የ17 ዓመት ወጣት - ማርች 12, 2021
ሃብታም በአማራ ክልል በጎንደር ትክል ድንጋይ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ከኮቪድ 19 በፊት እናቷ ቤት ተከራይታላት ትምህርቷን ትከታተል ነበር፡፡ ባለፈው ዓመት ኮቪድ 19 ሲገባ ስራ በመጥፋቱ ምክንያት ቀድሞም ቢሆን እዚህ ግባ የማይባለው የእናቷ ድጎማ ጭራሹን ቆመ፡፡ "እናቴ እስከመቼ እንዲህ ትኖራለች? ኮቪድ ሲመጣ ስራ ቆም እንጂ ሆድ እህል መጠየቁን አያቆም ብዬ ለትዳር ስጠየቅ አይኔን አላሸሁም” ትላለች፡፡
-
ለሴቷ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ምጣኔ እና የሚኖረው ጠቀሜታ - ማርች 10, 2021
በአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም የተባበሩት መንግስታት ተቋማት የቤተሰብ ምጣኔ 2020(ሃያ ሃያ) የዓለም አቀፍ የትብብር እና ተነሳሽነት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ ሪፖርቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ 67 ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሃገራት ላይ የተሰራ ሲሆን ምንም እንኳን በድሃ ሃገራት ውስጥ ያለው የቤተሰብ ምጣኔ ተጠቃሚነት ቢጨምርም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ግን የቤተሰብ ምጣኔ እቅዱን በተገቢው መንገድ ለማስኬድ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረ አመላክቷል፡፡
-
በስራ ቦታ እድገት እና የሴቶችን ፈተና ያካተተው የሕይወቴ ቅኝት - ማርች 08, 2021
ፍጹም አጥናፈወርቅ ኪዳነማሪያም የጽኑ ሴቶች ማህበር አባል እና የሴቶች መብትን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ሃሳቧን በግልጽ በመናገር እና ሴቶችን በማስተባበር ትታወቃለች፡:በቅርቡም የሕይወቴ ቅኝት የተሰኘ እና በእውነተኛ የግል የሕይወት ተሞክሮዎቿ እና አጋጣሚዎች ዙሪያ ያተኮረ መጽሃፍ ለንባብ አብቅታለች፡፡
-
እኮ ትምህርት ለምን? - ክፍል አንድ - ማርች 03, 2021
መማር ምንድ ነው? በእርግጥ ከትምህርት ልናገኝ የምንጠብቅና የምናገኘው አንድ ይሆኑ?
-
"በጠመንጃ እና በሰላም አስከባሪ ታጅበን የሰላም ጉዞ አድርገናል ማለት አንችልም" ያሬድ ሹመቴ - ማርች 02, 2021
ከአዲስ አበባ ወደ አድዋ ሶሎዳ ተራራ የሚደረገው ጉዞ አድዋ ተጓዦች በዓሉን በአዲስ አበባ ለማክበር በጉዞ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ቀድሞ ይጓዙት ከነበረው ከ 1090 ኪ.ሜ ውስጥ ማሳካት የቻሉት 600 ኪ.ሜ ብቻ መሆኑን የገለጹ ሲሆን በመነሻቸው ላይ ዓላማ ባደረጉት መሰረትም ህዝቡ መሃል በመግባት ያለውን መከራ እና ችግር መታዘባቸውን በመግለጽ ከብሽሽቅ ፖለቲካ ሊወጣ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡
-
የኢትዮጵያ ዘመናዊ ቲያትር 100ኛ ዓመት ሊከበር ነው - ፌብሩወሪ 26, 2021
ኢትዮጵያ ውስጥ ዘመናዊ ቲያትር የተጀመረበት 100ኛ ዓመት ሊከበር መሆኑ ተበሰረ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ስለቲያትር ያገባናል ባሉ አስራአንድ የቲያትር ባለሞያዎች የተመሰረተው ‘ስለቲያትር’ የተሰኘ ቡድን ከኢትዮጵያ የቲያትር ማኅበር ጋር በመተባበር ዓመቱን በሙሉ የሚዘልቅ እና በሃገሪቱ እየተዳከመ የመጣውን የቲያትር ሙያ የሚያነቃቃ መርሃግብሮችን ማቀዱን ይፋ አድርጓል፡፡ በዛሬ ዕለትም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር የመጀመሪያውን ውይይት አድርጓል፡፡
-
ወጣቱ የዲጂታል ሰዓሊ እና የዩኒቨርስቲ ቆይታው - ፌብሩወሪ 17, 2021
አያና ከበደ የአራተኛ ዓመት የኢትዮጵያ የአርክቴክቸር እና የከተማ ልማት ዩኒቨርሲቲ የስነህንጻ ንድፍ አሪክቴክቸር ተማሪ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በዲጂታል ንድፎቹ እና ስዕሎቹ ተቀባይነት እያገኘ የመጣ ወጣት ነው፡፡
-
ስለ አንጋፋው አርቲስት አሊ ቢራ - ፌብሩወሪ 12, 2021
የአንጋፋውን አርቲስት አሊ ቢራን የሕይወት ታሪክ የሚዳስሰ መድሐፍ በአማርኛ፣ ኦሮምኛና በእንግሊዝኛ ተጽፎ ሰሞኑን ተመርቋል።
-
መንግስት በግጭት ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃትን እንዲከላከል የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ - ፌብሩወሪ 12, 2021
ባለፉት ሶስት ዓመታት በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ ህዝቦች ሃብት ንብረታቸውን በመተው ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ህይወታቸው አልፏል፡፡ ሴቶችም መደፈራቸው ተሰምቷል፡፡ ሴታዊት የጾታ ንቅናቄ በግጭት ቀጠና እና በሃገር ውስጥ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ለሴቶች ጥበቃ ቅድሚያ እንዲሰጥ እና ጥቃት ፈጻሚ አካላትም በተገቢው መንገድ ለህግ እንዲቀርቡ የሚጠይቅ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡
-
"ሴት የህክምና ባለሞያዎች ለስራቦታ ጾታዊ ጥቃት ተጋላጮች ናቸው" ዶ/ር ሰናይት በየነ - ጃንዩወሪ 29, 2021
የኢትዮጵያ ሴት ሃኪሞች ማህበር ከተመሰረተ 3 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን ሴት የህክምና ባለሞያዎች በስራ ገበታቸው ላይ የሚደርስባቸውን መገለል፣ የጾታ ጥቃት ለማስቀረት በተጨማሪም ባለሞያ ሴቶችን በአመራር ለማብቃት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ ሴት የህክምና ባለሞያዎች በህክምናው ዘርፍ ውስጥ ስላላቸው ሚና እና እንዲሁም ስለሚያጋጥሟቸው ችግሮች የኢትዮጵያ ሴት ሃኪሞች ማኅበር ፕሬዘዳንት እና በጤና ሚኒስቴር አማካሪ ዶ/ር ሰናይት በየነ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
-
'የአሁኑን እየከተቡ የኋላውን መዘከር' ጥቂት ከፎቶግራፍ ባለሞያ መክብብ ታደሰ ጋር - ጃንዩወሪ 28, 2021
መክብብ ታደሰ ወጣት የፎቶግራፍ ባለሞያ ሲሆን በተጨማሪም 'ጉጉት' የተሰኘ በድረገጽ ላይ በነጻ የሚሰራጭ ወጣት የፈጠራ እና የጥበብ ባለሞያዎች የሚዘከሩበት መጽሄት አጋር መስራች ነው፡፡ መክብብ በልጅነቱ አባቱ የስነ ሕንጻ ባለሞያ እንዲሆንላቸው ብለው ያስጀመሩት የስዕል ትምህርት አሁን ላለበት የፎቶግራፍ ስራ እንደገፋፋው ይናገራል፡፡
-
በሥነ-ጥበብ ማህበረሰብን ማከም ይቻላል - የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ዮናስ ሀይሉ - ጃንዩወሪ 19, 2021
ስደት በኢትዮጵያ ሥነ-ጥበብ እንዴት ይገለፃል የሚል አውደ ርዕይ በጀርመን ባህል ማእከልና በአለም አቀፉ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አማካኝነት ተዘጋጅቶ ነበር። በድህረ ገፅ አማካኝነት በኢትዮጵያና በጀርመን በታየው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ ስራዎቹን ያቀረበው ዮናስ ሀይሉ ሥነ-ጥበብ ማህበራዊ እውነታዎችን ለመነጋገርና የጋራ እሴቶችን ለማጎልበት ትልቅ ሚና አለው ይላል።
-
"የአድዋ ድል የመላ አፍሪካውያን መሆኑን ለማሳየት በአፍሪካ ጫፍ ላይ የጉዞ አድዋን ሰንደቅ እንተክላለን" ያሬድ ሹመቴ - ጃንዩወሪ 08, 2021
በየዓመቱ የአድዋን ድል ለመዘከር የሚደረገው “ጉዞ አድዋ” ተብሎ የሚጠራው የአርባ ስድስት ቀናት የእግር ጉዞ ስምንተኛ ዓመት መርኃግብር በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚጀመር አስተባባሪዎቹ አስታውቀ። ለ125ኛው የአድዋ ድልም የዚሁ ዝግጅት አካል የሆነ ሌላ ቡድን ወደ ኪሊማንጃሮ እንደሚጓዝና ድሉ የአፍሪካም ድል መሆኑን ለማሳየት በሚል ሃሳብ በዕለቱ በተራራው አናት ላይ የኢትዮጵያ፣ ያፍሪካ ሕብረትና የቱሪዝም ኢትዮጵያ ሰንደቅን እንደሚያውለበልቡ አዘጋጆቹ አመልክተዋል።
-
የፈንድቃ የባህል ማዕከል መስራች መላኩ በላይ የኔዘርላድ ፕሪንስ ክላውስ ሎሬት ተሸላሚ ሆነ - ዲሴምበር 31, 2020
ከጎዳና ሕይወት በመነሳት ከታዳሚዎች በሚያገኛት የሽልማት ገንዘብ ትምህርቱን የተማረው እና ሕይወቱን የቀየረው የባህል ተወዛዋዡ መላኩ በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ የጀመረባትን የፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት ከአምስት ዓመታት በፊት ገዝቶ ወደ ባህል ማዕከልነት ማሻገር የቻለ ወጣት ነው፡፡ በቅርቡም መላኩ በፈንድቃ የባሕል ማዕከል ለሚሰራቸው ስራዎች የኔዘርላንድስ የዘውድ ሽልማት የሆነው የፕሪንስ ክላውስ 2020 ሎሬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
-
"ሴቶች በመንግስት የልማት ተቋማት ቦርድ ውስጥ ሃምሳ በመቶ መቀመጫ እንዲያገኙ እየሰራን ነው፡፡" ናሁሰናይ ግርማ - ዲሴምበር 29, 2020
የኢትዮጵያ ጽኑ ሴቶች ማኅበር (ኤውብ) ከ10 ዓመት በፊት በናሁሰናይ ግርማ እና በሮማን ክፍሌ አማካኝነት በጥምረት የተመሰረተ ሲሆን፤ ባለፈው አስር ዓመት ጊዜ ውስጥም እጅግ ብዙ ሴቶች የቋንቋ፣ የንግድ ክህሎት እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎች የሚያገኙበት፣ ትስስር የሚያደርጉበት፣ በስራቸው የበቁ እና የላቁ ሴቶች እውቅና እና ድጋፍ የሚያገኙበት እንዲሁም በፖሊሲ ደረጃ ተጽእኖ የሚያሳድሩበት ሆኗል፡፡
-
በጽኑ የታመሙ ሕጻናትን ዕለት ዕለት በፈገግታ የሚያክመው ፍካት የሰርከስ ቡድን - ዲሴምበር 27, 2020
ከተመሰረተ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ፍካት ሰርከስ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰርክስ ፌስቲቫል አዘጋጅ ነው፡፡ በተጨማሪም ቡድኑ ‘የፈገግታ መድሃኒት’ የሚል መርሃግብር ቀርጾ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሕጻናት ልዩ ክፍል በሳምንት 6 ቀናት ሕጻናቱ በማዝናናት ያስተምራል፡፡ ኤደን ገረመው ከቡድኑ መስራቾች አንዱ የሆነውን የቡድኑን የፈጠራ ዳይሬክተር ደረጀ ዳኜ አነጋግራ ተከታዩን አዘጋጅታልናለች፡፡
-
ወጣት ሴት ተማሪዎችን ከበቁ ሴቶች ጋር የሚያጣምረው መርሃግብር - ዲሴምበር 24, 2020
የዩንቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን ለማብቃትና ስኬታማ ለማድረግ፤ የበቁ ሴቶችን ከወጣት ሴት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጋር የማጣመር መርሃግብርን ማስጀምሩን የሴቶች ሕጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መርሃግብሩ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ተቋም ጋረ በቅንጅት የሚተገበር ሲሆን ሴቶች በፖለቲካውም ሆነ በውሳኔ ሰጪ ቦታ ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎ በማሳደጉ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረም ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ኤደን ገረመው በዚህ ዙሪያ ዘገባ አላት፡፡
-
ወጣት ሴቶችን ከበቁ ሴቶች ጋር በማጣመር ለአመራር የሚያበቃ መርሃግብር - ዲሴምበር 21, 2020
የዩንቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን ለማብቃትና ስኬታማ ለማድረግ፤ የበቁ ሴቶችን ከወጣት ሴት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ጋር የማጣመር መርሃግብርን ማስጀምሩን የሴቶች ሕጻናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ መርሃግብሩ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ተቋም UNWOMEN እና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር የሚተገበር መሆኑን የሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አድነው አበራ ለአሜሪካ ድምጽ አስታውቀዋል፡፡
-
"የምሰራቸው ስራዎች ለሰዎች ስነ ልቦና ቅርብ ናቸው" ዮሃንስ ባልቻ - ዲሴምበር 15, 2020
ዮሃንስ ባልቻ የ'ጄ አይ ኒድ አርትስ' መስራች ነው ፡፡የግራፊክስ እና አኒሜሽን ባለሞያ ሲሆን ስራዎቹ ልዩ የሆኑ ኢትዮጵያዊ ስዕሎች እና የከተማ ሕይወትን የሚያስቃኙ ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በማሕበራዊ ሚዲያው ላይ ብዙ ተከታይ እያፈሩ መጥተዋል፡፡
-
ኢትዮጵያዊው የማር ወይን ነጋዴ የ750 ሺህ ዶላር አሸናፊ ሆነ - ዲሴምበር 05, 2020
በካሊፎርኒያ ሶኖማ ግዛት የሚኖረው አየለ ሰለሞን የጠጅ ባህል በማጥናት የጠጅ ጣዕም እና ሽታ ያለው የማር ወይን መጥመቅ ችሏል፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታትም ቢ ዲቫይን የተሰኘውን የማር ጠጅ በመሸጥ እና በዓለም ዙሪያ በማስተዋወቅ ላይ ቆይቷል፡፡ የኮቪድ 19 ወረሽኝ ከፍተኛ ወደሆነ ኪሳራ እና የገበያ መቀስዛቀዝ ያደረሰበት ሲሆን ይህን ችግሩን ለመቅረፍም በአሜሪካ ግዙፉ በሆነው የንግድ ውድድር ሻርክ ታንክ ውስጥ በምሳተፍ 750,000 ዶላር አሸናፊ ሆኗል፡፡
-
ከኢትዮጵያ የተሰረቁ ቅርሶችን ተከታትሎ የሚያስመልስ ኮሚቴ ተቋቋመ - ኖቬምበር 29, 2020
ከኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት የተዘረፉ ቅርሶችን የሚያስመልስ አስራዘጠኝ ታዋቂ እና ተጽእኖም ፈጣሪ ሰዎች የተካተቱበት ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቋመ፡፡ ኮሚቴው በዓለም ዙሪያ ያሉ የሃገሪቱን ቅርሶችን በማጥናት ከሃገራት ጋር በስምምነት እና በመግባባት ዓለም ዓቀፍ የቅርስ ጥበቃ ሕግን ባከበረ መልኩ ለመስራት ዓላማ እንዳለው የኢትዮጵያ የባህል እና የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
-
የምስጋና በዓል በትልቁ የኢትዮጵያውያን ቤተሰብ - ኖቬምበር 27, 2020
በየዓመቱ የሕዳር ወር ማብቂያ የመጨረሻው ሃሙስ ዕለት በአሜሪካዊያኑ ዘንድ የሚከበረው የታንክስ ጊቪኝ ወይም የምስጋና በዓል፤ ቤተሰቦች የሚሰባሰቡበት ትልቅ በዓል ነው፡፡ ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደርጉ ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ተስባስበው በመገናኘት ያከብሩታል፡፡ጩኒ ሙላት እና አስራ አንድ ወንድም እና እህቶቿ በየዓመቱ ይህንን ቀን፤ ከነልጆቻቸው ሰላሳ አምስት በመሆን በአንድነት ያከብሩታል፡፡ ይሁንና ዘንድሮ ግን በኮቪድ ምክንያት ይህን ማድረግ አልቻሉም፡፡
-
"ጥበብ ለሃገር ክብር የአርቲስቶች ስብስብ በግጭቱ ለተጎዱ ወገኖች የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር አዘጋጀ" - ኖቬምበር 26, 2020
ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች፣ የመገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎች ጥበብ ለሃገር ክብር በሚል ስያሜ በሃገሪቱ እየተካሄዱ ላሉ ለውጦች የተደራጀ አበርክቶት ለማድረግ መንቀሳቀሳቸውን አስታውቀዋል፡፡ አርቲስቶቹ በነገው ዕለትም በግጭቱ የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ለአንድ ቀን የሚውል 'የሃገር ልጅ የማር እጅ' የተሰኘ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር አሰናድተዋል፡፡
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
Loading similar podcasts...