Skip to content
ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ podcast artwork

PODCAST · society

ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ

by VOA

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

Publisher-supplied feed metadata · PodParley refreshed May 8, 2023 · Source feed

Episodes

  1. ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ዐይን የቃኘ መጽሃፍ ለንባብ በቃ - ኦክቶበር 11, 2023

    "Unleashing Diplomatic Dynamo: Ethiopia Unbound-Western Loss, China's Rise " ፣ በቀድሞው ዲፕሎማት ዘነበ ኃይለማሪያም ገነሜ ተጽፎ በቅርቡ ለአንባቢያን የቀረበ መጽሐፍ ነው። በዳላስ ቴክሳስ በንግድ አማካሪነት የሚሰሩት ጸሓፊው ፣የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ገጽታ፣ የዲያስፖራውን ሚና፣ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮችን በወፍ በረር ቃኝተዋል ። ሀብታሙ ስዩም በመጽሃፉ ዙሪያ አነጋግሯቸዋል ።

  2. የኢትዮጵያ ሚዲያ ተጨማሪ ፈተናዎች - ሜይ 11, 2022

    በፖለቲካ፣ በአፋኝ ህጎች በመረጃ ማግኘት እና ከገቢ ጋር በተያያዙ ችግሮች ታጥሮ የኖረው የጋዜጠኝነት ሙያ ቀደም ሲል ከመንግስት ሲደርስበት ከቆየው ጫና በተጨማሪ ባልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች ለሚደርስ ጥቃት ተጋልጧል። ከማህበራዊ ሚዲያ መስፋፋት ጋር ተያይዞም ፈተናዎችም በርትተውበታል። በነዚህና ተያያዥ የኢትዮጵያ ሚዲያ ወቅታዊ ውጣ ውረዶች ዙሪያ በዩናይትድ ስቴትስ የሚሲሲፒ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑትን ዶክተር ዘነበ በየነን አነጋግረናቸዋል።

  3. ዓለም አቀፍ ተቋማት ተልዕኳቸውን ማሳካት ለምን ተሳናቸው? - ኤፕሪል 22, 2022

    ከስምንት አስርት አመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ በርካታ እድሜ ጠገብ ዓለም አቀፍ ተቋማት በዓለም ዙሪያ የሰብዓዊ መብቶችን እና ሰብዓዊነትን ያማከሉ ስራዎችን ያከናውናሉ። ሆኖም ከተቋማቱ እድሜ እኩል የኖሩት ህግጋት እና ፖሊሲዎች አሁን ዓለምን ለገጠሟት ተግዳሮቶች መላ ማምጣት ባለመቻላቸው ትችቶች ይቀርብባቸዋል። ለምን?

  4. ክፍል ሁለት .. ከዚህስ ወደ የት? - ጁላይ 23, 2021

    የትግራዩ ግጭት፡ ሰላም እና አብሮ የመዝለቅ ጥያቄ!

  5. እስረኛ ፖለቲከኞችና እጩ ምዝገባ - ፌብሩወሪ 26, 2021

    በእስር ቤት የሚገኙ ፓለቲከኞች ለመጪው ምርጫ እጩ ሆነው እንዲቀርቡ እየሠራ መሆኑን ባልደራስለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ። አቶ ዳውድ ኢብሳ በሊቀመንበርነት የሚመሩት የኦሮሞ ነጻነትግንባር (ኦነግ) በበኩሉ አብዛኞቹ እስር ቤት የሚገኙ አባሎቹ በእጩነት እንዲመዘገቡ ጠይቋል። በዚህ ጉዳይላይ ያነጋገርናቸው የሕግ ባለሞያ ሕጉን መሰረት አድርገው ትንታኔን ሰጥተዋል።

  6. መጪው ምርጫና የፀጥታ ሥጋት - ፌብሩወሪ 22, 2021

    የፊታችን ግንቦት ለሚደረገው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምርጫ መራጩም ሆነ ተመራጩ ከስጋት ነፃእንዲሆኑና የዜጎች ደህንነት እንዲጠበቅ የፀጥታ ኃይሎች ገዢውንና ተቃዋሚ ፓርቲውን ሳይለዩ ሰላምናደህንነት የማስጠበቅሥራ ለመሥራት መዘጋጀት እንደሚገባቸው የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የፖለቲካፓርቲዎች ገልፀዋል።

  7. ከቀድሙት ልዩ የሆነው የ46ኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት በዓለ ሲመት - ጃንዩወሪ 20, 2021

    "የአሜሪካ ፕሬዘዳንታዊ በዓለ ሲመት ሰላማዊ የሆነ የስልጣን ሽግግር ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ የአሜሪካ ድምጹ ስቲቭ ሬዲስች የዩናይትድ ስቴትስ 46ኛው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት ከቀደሙት በምን እንደሚለይ ያደረሰንን ዘገባ ኤደን ገረመው አጠናቅራዋለች፡፡"

  8. የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ብሔርተኝነት የሚታይባቸው እና በወከሉት ብሔር ላይ የተበዳይነትን መንፈስ ለማስፈን እየሰሩ መሆኑን የሚያሳይ ጥናት ይፋ ሆነ - ዲሴምበር 29, 2020

    ‘የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ብሄርተኝነት’ የሚል ጥናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ዲፓርትመንት መምህር በሆኑት በዶ/ር ሙላቱ አለማየሁ እና በኖርዌይ ኤን ኤል ኤ(NLA) ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የጋዜጠኝነት መምህር ቴሬ ሸዳል ባለፈው ሳምንት ይፋ ተደርጓል፡፡

  9. የባይደን የድል ንግግር፤ ስለምርጫው ውጤት የዓለም ምላሽ - ኖቬምበር 08, 2020

    የዩናይትድ ስቴትስ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለአንድነትና ተከፋፍሎ የተራራቀውን የፖለቲካ አካሄድ ለማቀራረብ የሚጣራ ንግግር አድርገዋል። ተመራጩ ፕሬዚዳንት የድል ንግግራቸውን ያደረጉት የዘንድሮው ምርጫ ውጤት ወደ እርሣቸው ማጋደሉ ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ ነበር።

  10. ኢትዮ ኤርትራዊያን ሴቶች ድምጻቸውን ከምን አኳያ ሰጡ? - ኖቬምበር 05, 2020

    አርባ ስደስተኛው የአሜሪካ ምርጫ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀርቶታል፡፡ በዓለም ዙሪያ በጉጉት የሚጠበቀው ይሄ ምርጫ ለሁሉም ሰው የተለያየ ትርጉም አለው፡፡ በምርጫው የተሳተፉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኤርትራዊያን ሴቶች ለ46ኛው ፐሬዘዳንታዊ ምርጫ ድምጻቸውን በምን መመዘኛ ሰጡ? የአሜሪካ ድምጿ ኤደን ገረመው ታሰማናለች፡፡

  11. በ2012 ዓ.ም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተከሰቱ የተማሪዎችን ግጭት የብሔር መልክ ለማስያዝ ማህበራዊ ሚዲያው ሰፊ ሚና ተጫውቷል- ጥናት - ኦገስት 26, 2020

    የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል በዛሬው ዕለት፤ በ 2012 ዓ.ም ከመስከረም እስከ የካቲት ወር ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ማዕከላት ውስጥ የተፈጠሩትን ግጭቶች በተመለከተ 54 ገጽ ያለው ጥናት ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መስረት ጥናቱ ባተኮረባቸው 6 ወራት ውስጥ ብቻ የ12 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን፣ 57 ተማሪዎች ከባድ እና ቀላል እንደደረሰባቸው እና የትምህርት መስተጓጎል መፈጠሩ ተገልጿል፡፡

  12. የትግራይ ህዝብ ትግል በህወሐት ተጠልፏል ሲል “ፈንቅል ትግራይ ’’ ወቀሰ - ኦገስት 25, 2020

    የትግራይ ህዝብ ያቀረባቸው ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ የተደረገው ጥረት ውጤታማ ባለመሆኑ ፣በክልሉ የሚገኘውን የህወሐት ዓመራር በተለያዩ የትግል ስልቶች ለመለወጥ ያለመ የወጣቶች እንቅስቃሴ ጥረት እያደረገ መሆኑን የእንቅስቃሴው ሊቀመንበር ለአሜሪካ ድምጽ አስታወቁ።

  13. “የቀረበው ስሞታ በዓለም አቀፍ አሰራር ተቀባይነት ያለው አይደለም” -ም/ጠ/ዐ/ህ ፍቃዱ ጸጋ - ኦገስት 19, 2020

    የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ ሂዩማን ራይትስ ዋች ከሰሞኑ ያወጣውን በቁጥጥር ስር የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን የሚመለከት መግለጫ የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓት ጠንቅቆ ባለማወቅ የተሰጠ እና የተቻኮለ መሆኑን ጠቆመ።

  14. የሰላም ሚኒስተር የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ - ኦገስት 15, 2020

    የሰላም ሚኒስተር የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ በጥር 2012 የህገ ወጥ መሳሪያ ቁጥጥርን ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ መስረት በቀጣይ ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ዜጎች የጦር መሳሪያቸውን እንዲያስመዘግቡ ይጠበቃልም ተብሏል፡፡ ኤደን ገረመው በሰላም ሚኒስተር የሚኒስተር አማካሪ የሆኑትን አቶ ሚናስ ፍስሃ አነጋገራለች፡፡

  15. "ጾታዊ ጥቃትን በተመለከተ የወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ ከትርጓሜ ጀምሮ ብዙ ክፍተት አለው" ወ/ት ሌንሳ ቢየና - ጁን 27, 2020

    ባለፉት ሳምታት ጾታዊ ጥቃትን የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ የቅጣት ሕጉ እንዲጠብቅ የሚጠይቅ ዝም አልልም የሚል የማሕበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀምሯል፡፡ ኤደን ገረመው በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማሕበር ስራአስፈጻሚ ዳይሬክተር የሆኑትን ወ/ት ሌንሳ ቢየናን ከሕግ አንጻር ያለው ክፍተት ምን ይመስላል? ሕጉስ በምን መልኩ ነው መሻሻል ያለበት? ስትል ጠይቃለች፡፡

  16. ውርድወት ሃገር በቀል የምርምር ፕሮግራም - ኤፕሪል 16, 2020

    የመብቶች እና የዴሞክራሲ እድገት ማሕበር(CARD) ውርድወት የምርምር ሥራ (ውርድወት ፌሌውሺፕ) በመጀመር ለምርምር አድራጊዎች የውድደር ጥሪ አቅርቧል፡፡ ይህ ምርምር ማኅበራዊ መበላለጦችን እንዲሁም በቁጥር አናሳ የሆኑ እና ለጥቃትና መድልዖ ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የእኩል ዕድል እና የእኩልነት መብት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አገር በቀል ዕውቀቶች እና ተሞክሮዎች ላይ እንዲሠሩ ድጋፍ የሚያደርግ መርሐ ግብር መሆኑ ታውቋል።

  17. ዲሞክራሲ በተግባር - ፌብሩወሪ 13, 2020

    በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለውን የድንበር ጉዳይ በዘላቂነት ለመፍታት “የኛ የመሪዎች ተገናኝቶ መነጋገር አስፈላጊ ነው” ብለዋል የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የክልሉ ገዥ ፓርቲ ህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል።

  18. ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነቶችን በግዛቷ ለማስፈጸም እየተሰናዳች ነው። ከዚህ እርምጃ ምን ትጠቀማለች? - ዲሴምበር 23, 2019

    ኢትዮጵያ ዓለምአቀፍ የግልግል ዳኝነቶችን በግዛቷ ለማስፈጸም እየተሰናዳች ነው። ከዚህ እርምጃ ምን ትጠቀማለች?

  19. አቶ ዳውድ ኢብሳ ከቪኦኤ ጋር - ዲሴምበር 04, 2019

    ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ “ከመቼውም ጊዜ በላይ የተወሳሰበ ነው” ያለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አጠቃላይ የሃገራዊ ንግግር መድረክ እንዲጠራ ጠይቋል።

  20. የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ለማስፈፀም እየተሰራ ነው - ኦክቶበር 09, 2019

    የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ለማስፈፀም የሚረዳ የህግ ሰነድና የአሰራር ማዕቀፎችን እያዘጋጀ መሆኑን የውሳኔ ህዝብ ማስፈፀሚያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት አስታውቀ።

  21. ፕሮፌሰር መረራ ስለፓርቲዎቹ ስምምነት - ኦክቶበር 02, 2019

    በኦሮምያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን ዘግበናል፡፡

  22. የኒውዚላንዱ ጨካኝ ግድያ ለማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች የማንቂያ ደውል ነው - ኤፕሪል 11, 2019

    ኒውዚላን ውስጥ በቅርቡ የዓርብ ጸሎታቸውን ለማድረስ መስጊድ ውስጥ በተሰበሰቡ አማንያን ላይ የተፈጸመውን ጨካኝ ግድያ የሚያሳዩ በወቅቱ የተቀረጹ የቪዲዮ ቅጂዎች የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላላቸው ኩባንያዎች የማንቂያ ጥሪ ሆኗል።

  23. ዲሞክራሲ በተግባር - ፌብሩወሪ 06, 2019

    የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን እንደዚሁም የዕርቀ ሰላም ኮሚሽንን በማቋቋም እና የአባለቱን ሹመት በማፅደቅ ሂደት በፓርላማው የታየው ድጋፍና ተቀውሞ የዛሬውን የኢህአዴግ ውስጣዊ ሁኔታ በግልፅ ያሳየ ነው ይላል ቀጣዩ ዘገባ፡፡

  24. ዲሞክራሲ በተግባር - ሴፕቴምበር 14, 2018

    በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ፣ በተለይም መንግሥት ባቀረበላቸው ጥሪ መሠረት ወደ ሀገር ገብተው ሰላማዊ ትግል ለማካሄድ በወሰኑ በርካታ ድርጅቶች ላይ ያተኩራል።

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

HOSTED BY

VOA

Produced by የአሜሪካ ድምፅ

CATEGORIES

Frequently Asked Questions

How many episodes does ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ have?

ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ currently has 50 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ about?

የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡

How often does ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ release new episodes?

ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ has 50 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ?

You can listen to ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ?

ዲሞክራሲ በተግባር - የአሜሪካ ድምፅ is created and hosted by VOA.
URL copied to clipboard!