PODCAST · news
ኮሮናቫይረስ/ኮቪድ-19 - የአሜሪካ ድምፅ
by VOA
የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
Episodes
-
ኢትዮጵያ ሦስተኛው የኮቪድ ማዕበል አስግቷል - ኦገስት 31, 2021
በኢትዮጵያ የኮቪድ ወረርሽኝ ሦስተኛው ማዕበል እየጀመረ መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት አስታወቀ። ዴልታ የተሰኘው አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ በሃገሪቱ መኖር አለመኖሩን በቅርቡ እንደሚያረጋግጥም ገለፀ። ወደ 22 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በስድስት ወር ውስጥ የኮቪድ ክትባትን ለማዳረስም እየተሠራ ነው ተባለ።
-
የአይምሮ ጤና ከአካላዊ ጤና እኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል - ኦገስት 26, 2021
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ሀገራት የአይምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በሽታው በቀጥታ በአይምሮጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ወረርሽኙ በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ባደረሰው ተፅእኖ ምክንያት ለአይምሮ ጤና ይደረግ የነበረው የገንዘብ ድጎማ በመመናመኑም ቀድሞውንም ደካማ የነበረው የህክምና አቅርቦት መቀነስ ችግሩን እያባባሰው ነው።
-
የባይደን አስተዳደር ሁሉንም አሜሪካዊያን ለማስከተብ አዲስ ዕቅድ አውጥቷል - ጁላይ 12, 2021
በዩናይትድ ስቴትስ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው ሕዝብ በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣው የኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ክትባትን አልወሰደም፡፡ በክትባቱ ዙሪያ ያለው የሃሳብ ልዩነትም ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት እያከበደው ይገኛል፡፡
-
በኮቪድ 19 ተጠቅተው ጽኑ ህሙማን ክፍል የገቡ አፍሪካዊያን የመሞት እድላቸው እጅግ ሰፊ ነው - የአፍሪካዊያን ጽኑ ህሙማን ጥናት - ጁን 12, 2021
በኮቪድ 19 የተጠቁ እና በጽኑ የታመሙ አፍሪካውያን በሌላው የዓለም ካሉ ታማሚዎች ጋር ሲንጻጸር የመሞት እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን የአፍሪካ የኮቪድ 19 ጽኑ ህሙማን ላይ የተደረገ ጥናት አመላከተ፡፡ ጥናቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአስር የአፍሪካ ሃገራቶች ተካሂዷል፡፡ ይሄ ጥናት በቅርቡ ዘ ላንሴት በተሰኘው የህክምና መጽሄት ላይ ታትሟል፡፡
-
ዩናይትድ ስቴትስ እስከ ሰኔ ወር ማብቂያ ድረስ 80ሚሊየን ክትባቶችን እንደምትለግስ ቃል ገባች - ጁን 05, 2021
ከመጪው የአሜሪካ የነጻነት ቀን ጁላይ ፎር በፊት 70 በመቶ የሚሆኑ አሜሪካዊያን አዋቂዎች የኮቪድ 19 ክትባት እንዲወስዱ ፕሬዘዳንት ጆባይደን ለአንድ ወር የሚቆይ ማበረታቻ መርሃግብር ጀመሩ፡፡ በተጨማሪም አተዳደራቸው ሃሙስ ዕለት 25 ሚሊየን የሚሆን ክትባት በተባበሩት መንግስታት በኩል ለኮቫክስ እንደሚለግስ አስታውቋል፡፡ ይህም እስከ ሰኔ ማብቂያ ድረስ 80 ሚሊየን ክትባት ለመለገስ ቃል ከተገባው ውስጥ የመጀመሪያው ነው፡፡
-
የኮቪድ-19 ክትባት በትግራይ ክልል - ሜይ 21, 2021
መቀሌ ከተማ ከባለፈው መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ካደረጉ ሰዎች 37 በመቶ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል። ቢሮው በከተማው እስከ አሁን ለ23ሺህ ሰዎች የቫይረሱ ክትባት እንደተሰጠ አስታውቋል። ምርመራውና ክትባቱ በክልሉ ሌሎች ከተሞች ለማካሄድ ማቀዱ ነው የገለፀው።
-
በአፍሪካ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች ወረርሽኝ ሊያገረሽ ይችላል - ሜይ 07, 2021
በአፍሪካ ለኮሮና ቫይረስ የሚሰጠው ህይወት አዳኝ ክትባት ስርጭት በጣም አነስተኛ በመሆኑና አዳዲስ የቫይረሱ ዝርያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን ተከትሎ የአፍሪካ ሀገራት የአዲስ ልውጥ ቫይረስ ወረርሽኝ ያሰጋቸዋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቋል።
-
በኢትዮጵያ የኮቪድ 19 ክትባት የተከተቡ ሰዎች ምን ይላሉ? - ሜይ 04, 2021
ኢትዮጵያ የካቲት 28 2013 ዓ.ም 2.2 የአስትራዜኒካ ክትባት በመጋቢት አጋማሽ ደግሞ 300,000 የሳይኖፋርም ክትባቶችን ያገኘች ሲሆን የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት መሰጠት ሂደትም ጀምራለች፡፡ በሃገሪቱ ያለው የክትባት አሰጣጥ ሂደት ምን ይመስላል? የኅብረተስቡስ ግንዛቤ ስትል ኤደን ገረመው በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ እና የብሔራዊ የክትባት አስተባባሪ የሆኑትን ዶ/ር ሙሉቀን ዮሃንስ፣ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎችን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች፡፡
-
በኮቪድ-19 እና በፖለቲካ አለመረጋጋት የተፈተኑት የኢትዮጵያ ሚዲያ - ሜይ 03, 2021
በብዙ ፈተኛዎች ውስጥ የኖረው የኢትዮጵያ ሚዲያ አሁን ደግሞ ዓለምን ባጠቃው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በተለይ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በማስታወቂያ እጥረት ምክንያት ገቢ መቀነስ፣ መረጃ የማግኘት ችግር፣ ባልታወቁ አካላት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርስ ማስፈራራትና ጥቃት እንዲሁም የሚዲያዎች መዘጋት ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት ትልቅ ፈተናዎች ነበሩ።
-
"ቅንነት ትልቅ ዋጋ አለው" - ቬርሳቬል መላኩ - ሜይ 03, 2021
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአነስተኛ የንግድ ዘርፎች ላይ የነበረው ጫና የበረታ ሲሆን ብዙዎችን ከገበያ ውጪ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ ጫና ካረፈባቸው አነስተኛ የንግድ ተቋማት መሀከል በአሜሪካን ሀገር፣ ቨርጂንያ ግዛት የሚገኘው ዘመን የጉዞ ወኪል አንዱ ሲሆን የድርጅቱ ባለቤት ቬርሳቬል መላኩ ድርጅቷ ከስራ ውጪ የሆነበትን አንድ አመት በሰሜን አሜሪካ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ነፃ የማማከርና የመረጃ አገልግሎት በመስጠት ስታገለግል ቆይታለች።
-
በኢትዮጵያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ የሚገኘው ኮቪድ-19 - ኤፕሪል 27, 2021
በኢትዮጵያበኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን በበሽታው ምክንያት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ቀጥሏል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ውስጥ የፅኑ ህሙማን አልጋ፣ ኦክስጅንና ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያዎች እጥረት የተከሰተ ሲሆን የቫይረሱ ተጠቂዎች ህክምና ለማግኘት መቸገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የታማሚ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
-
የኮቪድ-19 ምርመራ በትግራይ ክልል - ኤፕሪል 16, 2021
በትግራይ ክልል ባለፉት አምስት ወራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምርመራ አልተካሄደም ሲል የክልሉ ጤና ምርምር ተቋም አስታወቀ። ተቋሙ እንደገለፀው በክልል አሁን ባለው የፀጥታ ችግርና በጤና ተቋማት ላይ በደረሰው ጉዳት የኮቪድ-19 ምርመራ ለማካሄድ አዳጋች እንዳደረገው ገልጿል። በቅርብ ቀናት በመቀሌ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት የኮረና ምርመራ እየተጀመረ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል።
-
ኮሮና በትምህርት ላይ የሚያሳድረው ጫና እንደቀጠለ ነው - ኤፕሪል 15, 2021
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለዘጠኝ ወራት ተዘግተው የቆዩት ትምህርት ቤቶች አሁን በፈረቃ ማስተማር ቢጀምሩም ከትምህርታቸው ርቀው የቆዩት ተማሪዎች ላይ ያሳደረው ጫና ግን እንደቀጠለ መሆኑን ተማሪዎች ይገልፃሉ። በወረርሽኙ ምክንያት የመተዳደሪያ ገቢያቸውን ያጡ ወላጆችም የልጆቻቸውን የትምህርት ወጪ ለመሸፈን በመቸገራቸው አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሳይመለሱ ቀርተዋል።
-
ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ - ኤፕሪል 13, 2021
በኢትዮጵያ ህዝቡ ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያደርገው ጥረት አናሳ ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር ገለጸ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ እንዳስታወቀው፣ ለአለፉት ስድስት ወራት ለተደረጉት የዳሰሳ ጥናቶች ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች ዝቅተኛ ናቸው። በተለይ ት/ቤቶች ላይ 79 በመቶው የነበረው ወደ 76 በመቶው መውረዱን ጥናቱ ያሳያል ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ምርምርና ጥናት ግብረ ኃይል አስተባባሪ ዶ/ር አበባየሁ ገበየሁ ተናግረዋል።
-
የሀይማኖት አባቶች የፀረ-ኮቪድ 19 ክትባት ወሰዱ - ኤፕሪል 08, 2021
በኢትዮጵያ የሀይማኖት አባቶች ዛሬ የኮቪድ-19 ክትባትን ወስደዋል። ኅብረተሰቡ የመከተብ ዕድል ሲያገኝ ክትባቱን እንደሚገባውም ያሳሰቡት የኃይማኖችት አባቶቹ፤ ሕዝቡ ራሱን ከኮሮናቫይረስ እንዲከላከልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
-
ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በታንዛኒያ - ኤፕሪል 07, 2021
ታንዛኒያ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትኩረት አለመሰጠቷ እንደሚያሳስባቸው እዚያ ለብዙ ዓመታት የኖሩ ትውልደ-ኢትዮጵያ ገልፀዋል። የኮቪድ-19 ክትባት የሚኖሩበት ሀገር ውስጥ እንደሌለም አመልክተዋል። ለኢትዮጵያዊያኑ ስጋት ምላሽ በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መልስ ሰጥቷል።
-
ኮቪድ 19 የፈጠረው የስራ ጫና እና ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች እያሳለፉት ያለው ጊዜ - ኤፕሪል 01, 2021
ያለፈውን አንድ ዓመት ከኮቪድ 19 ጋር ሲታገሉ የከረሙት ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞች ዘንድሮም ወረሽኙ በማገርሸቱ ከባድ የስራ ጫና ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በዓለም ዙሪያ ሃኪሞች በስራ ጫና ለሚመጣ ጭንቀት፣ ድብርት እና መዳከም ወይም በእንግሊዘኛው በርን አውት መጋለጣቸው እየተነገረ ነው፡፡ በተመሳሳይ ኢትዮጵያዊያን ሃኪሞችም ከፍተኛ ለሆነ ጭንቀት፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ ድካም በመጋለጣቸው የተለያ ባህሪ ማዳበር፣ ማልቀስ እና ጭንቀት እንደ ታየባቸው ለአሜሪካ ድምጽ አጋርተዋል፡፡
-
በኤርትራ በኮቪድ ምክንያት የተቋረጠው የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ጀመረ - ማርች 29, 2021
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በፈጠረው ስጋት ምክንያት ከኣንድ ዓመት በፊት ተቋርጦ የነበረው የህዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ዛሬ ሰኞ መጋቢት 20 በከፊል ጀምሯል። ዛሬ የጀመረው የአውቶብስ አገልግሎት በአስመራ ከተማና በሌሎች የተመረጡ ከተማዎችና ገጠሮች የሚሰጥ ሲሆን በተወሰነ ደረጃ ለሙከራ የተጀመረ እንደሆነ ታውቋል።
-
ኤርትራ ውስጥ በኮቪድ የተቋረጠው ትምህርት ሊጀምር ነው - ማርች 24, 2021
ኤርትራ ውስጥ የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመግታት በተወሰደው እርምጃ ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በሚመጣው ሣምንት እንደሚጀመር የኤርትራ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። ትምህርት መጀመሩ የወረርሽኙ ስጋት ቀንሷል ማለት እንዳልሆነ የገለፀው የትምህርት ሚኒስቴር ሲዘወተሩ የነበሩ የኮቪድ-19 መክላከያ መንገዶች መተግበር እንዳለባቸው አጥብቆ አሳስቧል።
-
የኮቪድ ሥርጭት መባባስ እና የህብረተሰቡ ጥንቃቄ በኢትዮጵያ - ማርች 19, 2021
በኢትዮጵያ በኅብረተሰቡ ዘንድ እየታየ ያለው መዘናጋት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ሊያባብሰው ስለሚችል ማኅበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የጤና ባለሞያዎች እየመከሩ ነው። የጉደር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሕክምና ክፍል ኃላፊና የማዕከሉ ኮቪድ-19 ሕክምና አስተባባሪ ዶ/ር ናሆም ተሾመ፤ እርሳቸው በሚሠሩበት ሆስፒታል ውስጥ የታማሚዎች ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል።
-
ፕሬዚዳንት ኬንያታ የፖለቲካ ስብሰባን ለአንድ ወር አገዱ - ማርች 12, 2021
የኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ዛሬ በሀገሪቱ እየተንራፋ የመጣዉን ኮቪድ-19 ወረርሺኝ ለምግታት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ፕሬዚዳንቱ፣ በተለይ ለቫይረሱ መስፋፋት መነሻ የተባለውን የፖለቲካ ስብሰባ ለአንድ ወር እንዲታገድ ውሳኔ አሳልፈዋል።
-
የኮቪድ ክትባት በኢትዮጵያ - ማርች 12, 2021
ኢትዮጵያ ነገ መጋቢት 4/2013 ዓ.ም. የኮቪድ-19 ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ መስጠት እንደምትጀምር ተገለፀ። ክትባቱ ቅድሚያ የሚሰጠው ለጤና ባለሙያዎችና በጤና ተቋማት ውስጥ ለሚሠሩ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
-
የኮቪድ-19 አንደኛ ዓመት - ማርች 11, 2021
ኮቪድ 19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ተብሎ በዓለም የጤና ተቋም ከታወጀ ልክ ዛሬ አንድ አመት ሆነው፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ያለፈው አንድ ዓመት ኮቪድ-19ን በመከላከሉ ረገድ ምን ተሰራ፣ የክትባት ስርጭቱ ሂደት ምን ይመስላል በሚለው እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
-
ኮቪድ በኢትዮጵያ እየተባባሰ ነው - ማርች 04, 2021
ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት አሥር ቀናት በየቀኑ 12 ሰዎች በኮቪድ-19 እየሞተ መሆኑ ተገለፀ። ለመጭው ሃገር ሃቀፍ ምርጫ መደረግ ባለባቸው ጥንቃቄዎች ላይም መሥሪያ ቤታቸው እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።
-
የኮቪድ ክትባት በኢትዮጵያ - ፌብሩወሪ 12, 2021
ኢትዮጵያ በ2013 ዓ.ም ሚያዝያ ወር መጨረሻ ላይ ዘጠኝ ሚሊዮን ፀረ ኮቪድ-19 ክትባት ወደ ሀገር ለማስገባት እየሰራች መሆኗን አስታወቀች ። የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፀው እስከ 2013 ዓመት መጨረሻ ከአጠቀላይ የኢትዮጵያ ህዝብ 20 ፐርሰንት የሚሆኑት ክትባቱን እንዲያገኙ እየተሰራ ነው።
-
የማይስ ኮንቬንሽን ቢሮ ተስፋዎች እና የጸጥታ ስጋት ያጠላበት የኢትዮጵያ የቱሪዝም - ፌብሩወሪ 09, 2021
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ጉባኤዎች፣ አውደ-ርዕዮች እና ሁነቶች ‘ማይስ ኮንቬንሽን’ ቢሮ ባለፈው ሳምንት ከፍታለች፡፡ ይሄ ዘርፍም የቱሪዝሙን ዘርፍ ለማነቃቃት ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ ይሁንና ኮቪድ 19 ላለፈው አንድ ዓመት ለሚሆን ጊዜ በዘርፉ ላይ ያሳደረውን ጫና ባላገገመበት በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የሚነሱ የጸጥታ ችግሮች ዘርፉ በቶሎ እንዳይንሰራራ ስጋት መጣላቸውን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ባለድርሻ አካላት አስታውቀዋል፡፡
-
በኮቪድ 19 ምክንያት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ሴት ተማሪዎች ወደ ት/ቤት እንዲመለሱ ልዩ ጥረት ያስፈልጋል ተባለ - ፌብሩወሪ 04, 2021
በማላላ ፈንድ አማካኝነት በኢትዮጵያ የትምህርት ሻምፒዮኖች በኩል የተሰራው እና ከ 1300 በላይ ቤተሰቦች የተሳተፉበት ጥናት ባለፈው ሳምንት ይፋ ሆኗል፡፡ በጥናቱ መሰረትም በኮቪድ 19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ትምህርት በድጋሚ በተከፈተበት በአሁን ሰዓት በሃገር ዓቀፍ ደረጃ ልጃገረዶች ላይ ያተኮረ እና ወደ ትምህርት ገበታቸው ሙሉ ለሙሉ እንዲመለሱ የሚያበረታታ አካሄድ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
-
የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ሊቀጳጳስ ብጽዕ አቡነ ፋኑኤል ኢትዮጵያውያን ለሰላም እንዲተጉ ጥሪ አደረጉ - ጃንዩወሪ 19, 2021
በሰሜን አሜሪካ በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስትያናት በኮቪድ 19 ምክንያት እያንዳንዳቸው በ50 ሰው ታጅበው እንደሚወጡ ተሰምቷል፡፡ በዓሉን በተመለከተ በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን እና አካባቢዋ ሃገረስብከት ሊቀጳጳስ ብጹወ አቡነ ፋኑኤል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
-
"ቤት ለቤት አስቤዛ ማድረሻውን መተግበሪያ የሰራሁት ከራሴ ችግር ተነስቼ ነው" በረከት ታደሰ - ጃንዩወሪ 14, 2021
በረከት ታደሰ የቴክኖሎጂ ባለሞያ ሲሆን አስቤዛ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ ፈጣሪም ነው፡፡ አስቤዛ ዶት ኮም ሰዎች የሚፈልጓቸውን እቃዎች ለአማራጭ ከቀረቡ ሱፐር ማርኬቶች መተግበሪያውን በመጠቀም እሚያዙበት እና እቤታቸው ድረስ እንዲመጣላቸው የሚያደርግ ነው፡፡ ኤደን ገረመው ከበረከት ታደሰ ጋር የነበራትን ቆይታ እንደሚከተለው አጠናቅራዋለች፡፡
-
ለልጇ የጤና ችግር የወሰደችው አማራጭ ሕይወቷን የቀየረው የቴክኖሎጂ ባለሞያ - ጃንዩወሪ 14, 2021
ዮዲት በቀለ ስታንቶን ነዋሪነቷን በእንግሊዝ ሃገር ያደረገች የቴክኖሎጂ የፈጠራ ባለሞያ ስትሆን ‘ኦፕን ሴንሰርስ’ የተሰኘ የቴክኖሎጂ ተቋም መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ ናት፡፡ ኦፕን ሴንሰርስ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ላሉ ትላልቅ ተቋማት የዓየር ብክለት መጠን መጠቆሚያ መሳሪያዎች ላይ ሶፍትዌር የሚገጥም ሲሆን፤ ዮዲት ለዚህ ፈጠራዋ መነሻ የሆናት የመጀመሪያ ልጇ የነበረባት የአስም ችግር እንደሆነም ትናገራለች፡፡
-
የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ - ጃንዩወሪ 09, 2021
አፍሪካ መቼ ይሆን የኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒት የምታገኘው? ለሚለው ጥያቄ በአፍሪካ ዋናዋ የኮቪድ-19 ተጠቂ በሆነቸው ደቡብ አፍሪካ እንጀምር። የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ የጤና ሰራተኞችና ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች የኮሮናቫይረስ የክትባት መድሃኒት የመከተብ እድል ያገኛሉ ሲሉ አስታውቋል።
-
ኮቪድ-19 በኤርትራ - ዲሴምበር 28, 2020
በኤርትራ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 1039 ከፍ ማለቱን የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
-
ፋይዘር ያመረተውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት የወሰደ ኢትዮጵያዊ የህክምና ባለሙያ - ዲሴምበር 22, 2020
በግዙፉ የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ፋይዘር እና የጀርመኑ የሕክምና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባዮ ኢንቴክ በጋራ የሰሩት የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በአሜሪካን አገር መሰጠት ከጀመረ አንድ ሳምንት አስቆጠረ። ለመሆኑ የኮቪድ 19 ክትባት አወሳሰድ ምን አይነት ነው? ክትባቱ ከተወሰደ በኃላ የሚኖረው ስሜትስ ምን የምስላል? ባለፈው ሳምንት ክትባቱን ከወሰዱ የመጀመሪያ የጤና ባለሙያዎች መሃል አንዱ የሆነውን ኢታና ጨመዳ ዲሳሳን ጋብዘናል።
-
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ - ዲሴምበር 11, 2020
በሕብረተሰቡ ውስጥ እየተስተዋለ ላይ ነው ያለው ከፍተኛ ቸልተኝነትና መዘናጋት አሳሳቢ ሁኔታ መፍጠሩን የኮቪድ - 19 ወረርሽኝን የጥድፊያ መዛመት የደቀነውን ስጋት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ያወጣው መግለጫ አስታወቀ።
-
በኮሮና ምክንያት በ'ኦንላይን' የሚሰጠው የድህረ ምረቃ ትምህርት - ዲሴምበር 08, 2020
በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ኢትዮጵያ አብዛኞቹን ትምህርት ቤቶቿን ዘግታ በቆየችባቸው ግዜያት በክፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ የሁለተኛና የሶስተኛ አመት ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲከታተሉ ቆይተዋል፣ ጥቂቶችም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ በቅተዋል። ይህ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተካሄደ ያለው በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት ሂደት ምን ይመስላል፣ በትምህርት ጥራቱ ላይስ ያሳደረው ተፅእኖ አለ ወይ ስንል ጠይቀናል።
-
"በኮቪድ 19 ምክንያት የተቀዛቀዘው የአካል ጉዳተኞች ስፖርት ትኩረት ያሻዋል" ጥላሁን ጀማነህ - ዲሴምበር 08, 2020
10ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ጉዳተኞችና መስማት የተሳናቸው የስፖርት ፌስቲቫል “አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ምቹና ዘላቂ የተሻለ ዓለምን በድህረ ኮቪድ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል፡፡ ኤደን ገረመው በአካል ጉዳተኞች ስፖርት ክብደት በማንሳት የተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ አምስት ጊዜ ኢትዮጵያን በመወከል የተሳተፈውን አሰልጣኝ ጥላሁን ጀማነህን የዘንድሮውን ውድድር በተመለከተ አናግራው ነበር፡
-
ብርቱካናማ ዓለም የ16ቱ ቀናት ዘመቻ በድረገጾች ላይ እየተካሄደ ይገኛል - ዲሴምበር 03, 2020
የጸረ ጾታዊ ጥቃት የ16 ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕዳር 15 ቀን ተጀመሯል፡፡ ዘመቻው ዘንድሮ ድጋፍ፣ ምላሽ፣ መከላከል እና ማሰባሰብ የሚሉ መሪ ቃላትን ይዟል፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ በየዓመቱ በሰፊው እንቅስቃሴ የሚያደርጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የየሎው ሙቭመንት አባላት ዘንድሮ በኮቪድ 19 እና በተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮች ምክንያት ዘመቻውን በድረገጽ ላይ ብቻ ለማድረግ ተገደዋል፡፡
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
Loading similar podcasts...