PODCAST · news
እንወያይ
by DW
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።
Episodes
-
በኢትዮጵያ ሰላም ለምን እውን መሆን አልቻለም?
የሰላም ጥሪው ምላሽ ሳያገኝ ይህ ሁሉ የስጋት ድምጽ እየተሰማባለበት ኢትዮጵያ ሌላ አዲስ ዓመት ልትቀበል ቀናት ቀርተዋል። ዛሬም ጥፋተኖች ለፍርድ ተጎጂዎችም ፍትህ ያግኙ የሚለው ጥሪ አላባራም። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ማስፈን ለምን አቃተ? የሕዝቡ ሰቆቃስ ማብቂያው መቼ ነው? ዶቼ ቬለ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ላይ እንግዶች ጋብዞ አወያይቷል።
-
ኢትዮጵያ አሰቃቂ ግፎች ከሚፈጸምበት የግጭት አዙሪት መውጣት ለምን ተሳናት?
በተደራራቢ ግጭቶች ውስጥ ለተፈጸሙ ግፎች ተጠያቂነት ሳይረጋገጥ ኢትዮጵያ ሌላ የጦርነት ሥጋት ተጋርጦባታል። ለበርካታ አስርት ዓመታት ስለ ዴሞክራሲ ቢሰበክም የፖለቲካ ልሒቃኑ አገሪቱን ከግጭት አዙሪት ማላቀቅ አልቻሉም። ለምን? የለየለት ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ማቆም የሚችል ወገን አለ? ወይስ ረፍዷል? በአሜሪካው ኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ ማወር የሕግ ትምህርት ቤት ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ፈንታው፤ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ሐይማኖት አሸናፊ...
-
እንወያይ: ኢትዮጵያ ለዓመታት የጠበቀችው ሀገራዊ ምክክር ወዴት?
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተዋናዮች እና ምሁራን ለበርዓታ ዓመታት እንዲደረግ ሲያሳስቡ የከረመው ሀገራዊ ብሔራዊ ምክክር ዘንድሮ እውን ሆኗል። ውይይት ምክክሩ ሁሉን አላካተተም በሚል ጥያቄዎች ይነሳሉ።
-
ዉይይት፣ የአዲስ አበባ፣ የመቀሌና የአስመራ መሪዎች ዉዝግብ ንሯል፤ቀጥሎስ? ጦርነት ወይስ ሰላም?
የቃላቱ ጦርነት ደግሞ ከመቀሌና አዲስ አበባ አልፎ አስመራና ካርቱም እየደረሰ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ባለፈዉ ሰኔ 30 ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ህወሓት፣ ከኤርትራ (ሻዕቢያ)፣ ከሱዳን (SAF)ና በስም ካልጠቀሷቸዉ ሌሎች ወገኖች ጋር ሆነዉ የኢትዮጵያን ሠላም ለማወክ እያሴሩ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል
-
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ የሐገሪቱን ችግሮች ለማቃለል ይፈይድ ይሆን?
ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንዳዶቹ የፓርቲነት ፍቃድ ላለማጣት ሲሉ ብቻ የሚወዳደ,ሩ እንዳሉ አስታዉቀዋል።የኢትዮጵያን ምርጫ ሒደትና ሁኔታን የሚከታተሉ አስተያየት ሰጪዎች ደግሞ የዘንድሮዉን ምርጫ «ለገዢዉ ፓርቲ ሕጋዊ ዕዉቅና ለመስጠት ያለመ የታይታ» ምርጫ ይሉታል።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን የምርጫዉ የእስካሁን ሒደት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓትንና የሕዝብ ተሳትፎን ያሰፋ በማለት ያወድሱታል
-
እንወያይ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን ጦርነት ዳፋ ለአፍሪቃ ቀንድ
ጉዳቱ በሁሉም ሐገራት ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያን በመሳሰሉ ደሐ የአፍሪቃ ሐገራት ላይ ያሳደረዉ ከፍተኛ ጫና የየሐገራቱን ሕዝብ ኑሮ እያመሰቃቀለዉ ነዉ።የዚያኑ ያክል አንዳድ ተንታኞች እንደሚሉት ጦርነቱና ሥጋቱ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ይጫራል ተብሎ የሚፈራዉን ሌላ ዙር ጦርነት ባያስቀረዉ እንኳን ለጊዜዉም ቢሆን አዳፍኖታል።በየሰበብ አስባቡ ይሰማ የነበረዉ የአዲስ አበባና የአስመራ የዉጊያ ዛቻና ፉከራ ቀንሷል።
-
በኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ተሳትፎ እና ዐበይት ጉዳዮች
በ30 ዓመታት ሴቶች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያላቸው መቀመጫ ከ2% ወደ 40% አድጓል። ምን ፈየደ? በግንቦት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው የኢትዮጵያ ሰባተኛ አጠቃላይ ምርጫ የሴቶች ጉዳዮች ምን ያክል ትኩረት አገኙ? በግጭት ድባብ ውስጥ በሚካሔድ ምርጫ ለእንስቶች ተግዳሮቶች ምንድናቸው? የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሴቶች ክንፍ ሰብሳቢ እጸገነት ተስፋዬ፣ የኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል ሒሮዋቅ ግርማ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና...
-
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት ያባባሰው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ የተደረገው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ውጥረት አባብሶታል። በሁመራ፣ አዲረመፅ፣ ኮረም፣ ጠለምት እና ራያ አላማጣ ምርጫ ክልሎች “ከትግራይ ክልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ እንዲደረግ” የፌዴሬሽን ምክር ቤት መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳወቀው የካቲት 16 ቀን 2018 ነው። ዶይቼ ቬለ የሕግ ባለሙያዎቹን አቶ አምደገብርኤል አድማሱ እና አቶ አወት…
more -
እንወያይ: የአፍሪቃ ሕብረት ግጭቶችን ለማስቆም ለምን ተሳነው?
ከተመሠረተ 63 ዓመታትን ያስቆጠረው የአፍሪቃ አህጉራዊ ተቋም የአፍሪቃ ሕብረት በአባል ሃገራት ውስጥ ለሚካሄዱ ግጭቶችን ማስቆም ባለመቻሉ እየተተቸ ነው። ተቋሙ ራዕይ በነበራቸው የቀድሞ መሪዎች የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ተብሎ ሲቋቋም አፍሪቃ እንደ አንድ ተባብራ ሰላም አንድነቷን ለመጠበቅ እንደነበር ይታሰባል። አፍሪቃ ውስጥ እጅግ በርካታ ግጭት ጦርነቶች በሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እያደረሱ መሆኑ ይታያል። ሚሊዮኖችም ለስደትና ለመፈናቀል በመዳረጋቸው...
-
ባለሙያዎች ከዓመታት በኋላ ወደ ነጠላ አሐዝ ስለወረደው የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ምን ይላሉ?
የዋጋ ግሽበት ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ነጠላ አሐዝ ዝቅ እንዳለ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት አስታውቋል። የዋጋ ግሽበት የከዓመት ዓመት ዕድገት በህዳር ወር ከነበረበት 10.9 በመቶ በታኅሳስ ወደ 9.7 በመቶ ዝቅ ብሏል። የዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወደ 9.7% ዝቅ እንዳለ የተገለጸው ሸማቾች በኑሮ ውድነት በሚፈተኑበት ወቅት ነው። ለመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ገዥ “እጅግ የሚያስደምም” ያሉት ነጠላ አሐዝ የዋጋ ግሽበት በባለሙያዎች እንዴት ይታያል?
-
ዉይይት፣ የትራምፕ አስተዳደር ርምጃ፣ የዓለም ሕግና ሥርዓት እንዴትነት
የትራምፕ መስተዳድር የቬኑሱዌላን መሪ ማገት ብቻ ሳይሆን የነዳጅ ሐብቷንም ተቆጣጥሯል።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ማዱሮን ከማሳገታቸዉ በፊት የየመን ሁቲዎችን፣ የሶማሊያ፣ የኢራቅ፣ የሶሪያና የናጄሪያ ሸማቂዎችን አጠፋለሁ በሚል ሐገራቱን በተደጋጋሚ ደብድበዋል።እስራኤልን አግዘዉ ኢራንን ደብድበዋልም።
-
ዉይይት፣ የኢትዮጵያ የምርጫ ዝግጅት፣ የተቃዋሚዎች ሥጋትና የሰላም ጥያቄ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ባንፃሩ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች በሰጡት መልስና ማብራሪያ «ምርጫ ለማድረግ መንግሥት በቂ አቅም አለዉ፤ምርጫ እንኳን ዘንድሮ ባለፈዉም ምርጫ አድርገናል እየተዋጋን።» ብለዋል።በግጭት፣ ዉጥረት፣ ተቃርኖና ዉዝግ መሐል ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ሊደረግ ይችላል? ምርጫ ማድረግ ወይም አለማድረጉስ የኢትዮጵያን ዉስብስብ ችግሮች ለማቃለል ይጠቅማል? እንዴት? በዉይይታችን የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸዉ።
-
ውጥረት ያነገሰው የሰሞንኛው የህወሓት ታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና ያስከተለው ስጋት
የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፕሪቶሪያ-ደቡብ አፍሪቃ ላይ ግጭትን የማቆም ስምምነት ከተፈራረሙ ባለፈዉ ጥቅምት 23 ሶስኛ ዓመቱን አስቆጥሯል። ሶስቱ ዓመታቱ ብዙዎች እንደሚሉት ሁለቱ ኃይላት በስምምነታቸው መሰረት ግዴታቸውን ያልተወጡበት ወይም ሊወጡ ያልፈለጉበት ሰላምም ግጭት ያልነበረበት ሆኖ ነው ያለፈው።
-
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እና ብር ወዴት እያመሩ ነው?
የውጭ ምንዛሪ ግብይት በአቅርቦት እና ፍላጎት እንዲወሰን ከተደረገ ወዲህ ኢትዮጵያ ከሸቀጦች የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ዕድገት ቢያሳይም ብር እየተዳከመ ነው። የወርቅ ኤክስፖርት መሻሻል ብር እንዲረጋጋ ሊያደርግ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ተስፋ አድርጓል። የፕራግማ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መርዕድ ብሥራት፣ የፋይናንስ ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ እና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ የተሳተፉበት ውይይት…
more -
እንወያይ፣ ሥር የሰደደዉ የኢትዮጵያዉያን ክፍፍል መፍትሔ አለዉ ይሆን?
1983 ወታደራዊ ሥርዓት ተወገደ።ኤርትራ ነፃ ወጣች።በ1960ዎቹ መልስ አላገኘም የተባለዉ የብሔር-ብሔረሰቦች ጥያቄ መልስ አገኘ ተባለ።በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፈ,ደራሊዝም መመሥረቱም ታዋጀ።ጦርነቱ ግን ቀጠለ።ክፍፍሉም ከብሔሮች ወይም ጎሳዎች አልፎ ወደ ንዑስ-ብሔሮች፣ ከዚያም እስከ ጎጥ ቀጥሎ ዛሬ ያንድ ብሔር ወይም ጎሳ አባላት የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች እየተቧደኑ ወይም በተናጥል ይጋጫሉ፣ ይገዳደላሉም።
-
ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ምን ምን ዐበይት ጉዳዮች ተከሰቱ?
አሮጌውን 2017 ዓመት ተሰናብተን አዲሱን ዓመት መቁጠር ከጀመርን እነሆ ሦስተኛ ቀናችን ። በ2017 ኢትዮጵያ ውስጥ በዋናነት ምን ተከሰተ? የዕለቱ እንወያይ መሰናዶ ባሳለፍነው ዓመት የተከሰቱ ዐበይት ጉዳዮችን የምንቃኝበት ነው።
-
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የተጣለበት ተስፋ እና የተገተረው ድርድር
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በመጪው ማክሰኞ ይመረቃል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ከምትዋሰንበት ድንበር በ30 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኘው ግድብ የግንባታ ሒደቱ 14 ዓመታት ገደማ የወሰደ ነው። የኃይል ማመንጫው 13 ተርባይኖች ተገጥመውለታል። በግድቡ የተገጠሙ ተርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ በድምሩ 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ። በግድቡ የተፈጠረው ሰው…
more
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
በሣምንቱ በተከሰቱ በዋናነት የኢትዮጵያ እንደ አስፈላጊነቱ የዓለም ዐበይት ፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ዶይቼ ቬለ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን በመጋበዝ ውይይት ይካሔዳል። በውይይቱ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ይጋበዛሉ። በየሣምንቱ እሁድ የሚተላለፈውን የዶይቼ ቬለ የውይይት መሰናዶ በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ።
HOSTED BY
DW
CATEGORIES
Loading similar podcasts...