PODCAST · news
Ethiopian Refugee Crisis - የአሜሪካ ድምፅ
by VOA
የአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ከአርባ በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ከዩናይትድ ስቴትስ በመላው ዓለም የሚያሠራጭ አገልግሎት ነው፡፡ ቪኦኤ በየሣምንቱ ወደ 1 ሺህ 500 ሰዓት ለሚሆን ጊዜ ዜና፣ መረጃዎችን፣ ትምህርታዊና ባሕላዊ ፕሮግራሞችን በዓለም ዙሪያ ወደ 123 ሚሊየን ለሚሆን ሰው ያደርሣል፡፡ የበለጠ ለማወቅ በ voanews.com ላይ ያግኙን፡፡
Episodes
-
በመቀሌ የሚገኙ ተፈናቃዮች በችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ - ማርች 08, 2022
መቀሌ ከተማ በሚገኘው የተፈናቃይ ማዕከል የሚገኙ ተፈናቃይ ሴቶችን በአሁኑ ጊዜ የሚያገኙት እርዳታ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ለረሃብ መጋለጣቸውን ገልፀዋል።
-
በአማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃይ እናቶች በችግር ላይ መሆናችውን ገለፁ - ማርች 08, 2022
በጦርነትና በግጭት ምክኒያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ሴቶችና እናቶች በችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።
-
መቀሌ ውስጥ የተቸገሩ እናቶችና ህፃናትን ባለሆቴሎች እየረዱ ነው - ጃንዩወሪ 07, 2022
እጅግ የተቸገሩ ነፍሰ ጡሮችና ህፃናትን ለመርዳት እየተደረገ ባለ ጥረት ውስጥ እየተሳተፈ መሆኑን የመቀሌ የሆቴሎችና መኝታ ቤቶች ማኅበር ገልጿል። የኮሚቴውን የአመራር አባል ያነጋገረው ዓለም ፍስሃ ዝርዝሩን በተያያዘው ዘገባ አካትቷል።
-
ያለፈው ሁኔታና መጭ ተስፋ በደሴ ሰው አንደበት - ጃንዩወሪ 07, 2022
በገናው ዋዜማ የደሴ ሰው ስላለፈበትና ስለበዓሉ ምን እንደሚያስብ ቤተሰቦችና ነዋሪዎች ሃሳቦቻቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አካፍለዋል።
-
የተፈናቃዮች ቁጥር ማሻቀቡን መንግሥት አስታወቀ - ሴፕቴምበር 09, 2021
መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የትግራይ ወታደራዊ ኃይል እያለ የሚጠራው አካል ወደ አማራ ክልል ዘልቆ መግባቱን ተከትሎ ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከግማሽ ሚሊዮን መብለጡን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትናና ድጋፍ የሚፈልጉ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
-
ትግራይ ውስጥ እርዳታ ለማፋጠን እየሠሩ መሆኑን ሥራ አስፈፃሚው አስታወቁ - ጁን 19, 2021
በትግራይ ክልል ያለው የሰብዓዊ እርዳታ በፍተሻ ጣቢያዎች የሚያጋጥሙትን መስተጓጎል ለማስተካከል የሚያስችል መመርያው ማውጣቱ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት ገለፀ። መመርያው አስመልክቶ ለእርዳታ ሰጪ ተቋማት ማብራሪያ በዛሬው እለት ተስጥቷል።
-
"በአክሱም ባለው የህክምና አቅርቦት እጥረት ሳቢያ የእናቶች ሞት ከእጥፍ በላይ ጨምሯል" የአክሱም ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል - ጁን 10, 2021
የአሜሪካ ድምጿ ሄዘር መርዶክ ዛሬ በአክሱም የተለያዩ ሆስፒታሎችን ጎብኝታለች። ትግራይ ውስጥ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በተፈጠረው የህክምና አቅርቦት ችግር ምክንያት ሆስፒታሎች ነፍሰ ጡሮችን ማስተናገድ አለመቻላቸውን እና የእናቶች ሞት በእጥፍ መጨመሩን ለኤደን ገረመው ነግራታለች። በሌላ በኩል ሄዘር ሰሞኑን ወደ ሃውዜን ተጉዛ በነበረ ጊዜ የተመለከተቻቸውን የወል መቃብሮችና ያነጋገራቸውን የከተማዪቱን ሰዎች ሃሳቦች ያካተተችበትን ዘገባ በድምጽ ዘገባ ውስጥ ተካቷል፡፡
-
መቀሌ እንዴት ሰነበተች? - ጁን 10, 2021
የአሜሪካ ድምጽ የመሃከለኛው ምስራቅ ዘጋቢ ሄዘር መርዶክ አሁንም በመቀሌ ከተማ ነው የምትገኘው፡፡ ዛሬ ጠዋትም ከአፍሪካ ቀንድ ዘጋቢ ኤደን ገረመው ጋር ተገናኝተው፤ መቀሌ ከተማ ውስጥ ስላለው የባንክ አገልግሎት፣ ስለኮቪድ 19 እንዲሁም በሆስፒታሎቹ ስላለው የመሳሪያ እጥረት የታዘበችውን ገለጻላታለች፡፡ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
-
ትግራይ ውስጥ ተፈናቃዮች ወከባና ድብደባ እንደደረሰባቸው ተናገሩ - ሜይ 28, 2021
በትግራይ ክልል ሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ከተፈናቃዮች ማቆያዎች “በወታደሮች ታፍነው ተወሰዱ” የተባሉ ሰዎች ትናንት ማምሻውን መመለሳቸው ተገለፀ። በኢትዮጵያና ኤርትራ ወታደሮች ታፍነው መወሰዳቸውን እና ድብደባ ተፈጸሞብናል ማለታቸውን ጠቅሶ ሙሉጌታ አፅብሃ ከመቀሌ ያጠናቀረውን ዘገባ አድርሶናል።
-
ትግራይ ውስጥ ህፃናትን ከወላጆች ወይም ከአሳዳጊዎች ጋር ማገናኘት - ሜይ 20, 2021
በትግራይ ክልል በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ከእናት ኣባታቸው የተጠፋፉ ህፃናት የሚያስፈልጋቸው መሰረታዊ ነገሮችን ለማሟላት እየሰራ መሆኑን የዓለም አቀፍ ኢማጅን ዋን ደይ ድርጅት ትግራይ ሥራ አስከያጅ አቶ ሓለፎም ገዛኢ ገልፀዋል፡፡
-
እንባ ጠባቂው ስለተፈናቃዮች ተናገሩ - ኤፕሪል 28, 2021
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ እንዲሁም በቤንሻንጉል ካማሼ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ወደ 5መቶ ሺህ የሚጠጋ ሰው መፈናቀሉን የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡
-
ለሰሜን ሸዋ ተፈናቃዮች እርዳታ እየደረሰ ነው - ኤፕሪል 24, 2021
የፌዴራል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉት የነፍስ ደራሽ እርዳታ መስጠቱን ኮሚሽኑ አስታወቀ። በክልሉ 11 ዞኖች ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ከ600ሺ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ያለው ኮሚሽኑ ለሁሉም ድጋፍ እያደረግኩ ነው ብሏል።
-
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጀመረ - ኤፕሪል 07, 2021
በትግራይ ክልል ለሰባት ቀናት ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በአንዳንድ አካባቢዎች መመለስ ጀምሯል።
-
በትግራይ አካባቢዎች መብራት ከጠፋ ሳምንት ሆነው - ኤፕሪል 06, 2021
በትግራይ ክልል አብዛኛው አካባቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ አምስተኛ ቀን ተቆጠረ። የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የመቋረጡ መንግስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን እንዳላወቀው ጠቅሶ ችግሩን ለማወቅ እየጣረ መሆኑን ገልጿል።
-
ዳዳብ እና ካኩማ እንዲዘጋ በመወሰኑ ስደተኞች ተደናግጠዋል - ማርች 25, 2021
የኬንያ ሀገር ዉስጥ ጉዳይ በሀገሪቱ የሚገኙ ሁለቱም የስደተኞች መጠለያዎች በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፎአል። የኬንያ ሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ፍሬድ ማትያንግኢ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ተራድዖ ድርጅት ዳዳብና ካኩማ ካምፖችን እንዲዘጋ ባለፈዉ ማክሰኞ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ስደተኞች በውሳኔው ግራ መጋባታቸዉን ሲገልጹ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከሚመለከታቸዉ ጋር ንግግር ላይ መሆኑን ገልጿል።
-
ዶ/ር ሙሉ ነጋ ስለትግራይ ይናገራሉ - ክፍል ሁለት - ማርች 06, 2021
ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የተካሄደ በትግራይ ልዩ ልዩ ወቅታዊ ር ዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ዘገባ።
-
የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ተጨማሪ ድጋፍ ጠየቀ - ፌብሩወሪ 26, 2021
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ለሚሆን ህዝብ የእለት ደራሽ እርዳታ ለማቅረብ የ107 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ጠይቋል። በኢትዮጵያ የድርጅቱ ተጠሪ የተጎጁውን ህዝብ ፍላጎት ለማሟላት በአሁኑ ወቅት ገንዘቡ እጅግ የሚያስፈልግ መሆኑን አስታውቀዋል።
-
ኢሰመኮ ስለአምነስቲ ሪፖርት - ፌብሩወሪ 26, 2021
አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅት በአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ላይ ተፈጽሟል ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው እንደሆነ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ። ይሁንና ዘገባው የራሱ የሆነ ውስንነት ሊኖረው ይችላል ብለዋል ኮሚሺነሩ። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ በህጉ መሰረት ተገቢ እርምጃ እወስዳለሁ ማለቱን ዘገባው ይጠቅሰል።
-
በተማሪዎች ላይ የተፈፀመ ጥቃት - ፌብሩወሪ 23, 2021
በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ ሥነ ሥርዓታቸውን አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ የነበሩ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አዲመስኖ በምትባል አካባቢ በደረሰ የደፈጣ ጥቃት የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተማሪዎች ተናገሩ፡፡
-
በትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለጹ - ፌብሩወሪ 23, 2021
የኤሌክትሪክ አገልግሎት በትግራይ ክልል በአብዛኛው አካባቢ ከተቋረጠ አንድ ሳምንት ሆኖታል። ዘጋቢያችን ያነጋገራችው አንዳንድ ነዋሪዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ በኑሯቸውና በሥራቸው ላይ ተጽዕኖ እንዳሳደረ አመልክተዋል።
-
ትግራይ ክልል ዛሬ - ፌብሩወሪ 12, 2021
በትግራይ ክልል የተለየያዩ አካባቢዎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የመዝጋትና የትራንስፖርት አገልግሎት የማቋረጥ ተቃውሞ በዛሬ ዕለት ቀጥሎ ውሏል። በተቃውሞው ወቅት የሰው ሕይወት ማለፉንም የዐይን እማኞች ገልፀዋል። በመቀሌ ከተማ ደግሞ ተቃውሞው ለሦስት ቀናት ከተደረገ በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ መደበኛ ሥራ መገባት ተጀምሯል።
-
የዴቪድ ቢስሌ እና የፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ የትግራይ ግብኝት - ፌብሩወሪ 09, 2021
ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴናየመንግሥታቱ ድርጅት የዓለም የምግብ መርኃግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሌ ትናንት ትግራይ ክልልን ጎብኝተዋል።
-
በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት ጀመረ - ጃንዩወሪ 27, 2021
በትግራይ ክልል ከትናንት ከሰዓት ጀምሮ የተቋረጠው የስልክ አገልግሎት ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደገና መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ አስታውቀዋል።
-
ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በተካሄደው ውጊያ እንዲሳተፉ ተደርገዋል ስለተባሉ የሶማሊያ ወታደሮች - ጃንዩወሪ 27, 2021
ለሥልጠና ወደኤርትራ የተላኩ የሶማሊያ ወታደሮች በሚስጥር በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል በተካሄደው ውጊያ እንዲሳተፉ ተደርገዋል፤ ብዙዎችም ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡ በሀገራቸው የምክር ቤት አባላት ተጠይቀዋል።
-
የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል እንዲወጡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳሰበ - ጃንዩወሪ 27, 2021
የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አሳሰበ።
-
የዓለም የጤና ድርጅት በትግራዩ ግጭት ወረርሽኝ ሊስፋፋ ይችላል አለ - ጃንዩወሪ 25, 2021
የዓለም ጤና ድርጅት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ፣ በፌደራሉ መንግሥትና በህወሃት መካከል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ የተቋረጠው የጤና አገልግሎት፣ አደገኛ ወደ ሆኑ ተላላፊ በሽታዎች መስፋፋት ሊያመራ እንደሚችል አስጠንቀቋል፡፡
-
በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ጉዳይ - ጃንዩወሪ 25, 2021
የኢፌዴሪ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን (UNHCR) ጋር በመሆን በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን ጎብኝተዋል።
-
ከትግራይና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለተፈናቀሉ ድጋፍ ተደረገ - ጃንዩወሪ 15, 2021
የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በትግራይና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ለተፈናቀሉ ዜጎች በቂ ድጋፍ እያደረግኩ ነው ብሏል።
-
ጀነራል ብርሃኑ በሱዳን ጉዳይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር - ጃንዩወሪ 15, 2021
በሱዳን መንግሥት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ወገኖች የሦስተኛ ወገን አጀንዳ ለማስፈጸም እየሰሩ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።
-
በትግራይ ክልል መድኃኒት ለማቅረብ እንደተቸገረ የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ - ጃንዩወሪ 14, 2021
በትግራይ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት መድኃኒት ለማቅረብ የፀጥታ ችግር እንቅፋት እደሆነበት የክልሉ የጤና ቢሮ አስታውቋል። የቢሮውን የመድኃኒት ክፍል አስተባባሪ አቶ ገብረእግዚያብሔር ገብረጊዮርጊስን ያነጋገራቸው መቀሌ የሚገኘው ዘጋቢያችን ጠቁሟል።
-
የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነሯ ስለ ትግራይ ስጋታቸውን ገለፁ - ዲሴምበር 24, 2020
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባከሌት፣ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች በክፍተኛ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አስጠንቅቀዋል፡፡ በሰፊው እየተፈጸሙ መሆናቸው ከሚነገረው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከልም፣ አንዳንዶቹ የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
Loading similar podcasts...