SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

PODCAST · news

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

  1. 858

    ኢትዮጵያና ዩናይትድ ስቴትስ መከላከያን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ለመተባበር የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጠ

    የቻይና በኢትዮጵያ ቀጥተኛ ሙዋዕለ ንዋይ ፍሰት ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱ ተነገረ

  2. 857

    Tips to manage financial stress | Fuel in Focus - የፋይናንስ የመንፈስ ሁከትን ሚዛን የማስጠበቂያ ፍንጮች | ትኩረት ነዳጅ ላይ

    Australia's petrol and diesel prices remain under pressure. The RBA’s decision to hike the cash rate this month is adding to the financial strain facing many households. We look at some free and independent support services that are available to help people manage financial stress. - የአውስትራሊያ የነዳጅና ናፍጣ ዋጋዎች ጫናዎች ሳይረግቡ አሉ። የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ጭማሪም አያሌ ቤቶች ላይ ታካይ የፋይናንስ ሸምቀቆውን አጥብቋል። በፋይናንስ ጭንቀት ውስጥ ላሉ ሰዎች ነፃና ገለልተኛ የድጋፍ አገልግሎት የሚቸሩት ላይ ምልከታ አድርገናል።

  3. 856

    " አባቴ እግዚአብሄር ይባርክህ " - በቅርቡ በሞት የተለየው የአቶ ሰሎሞን አዲስ ታምሩ የመጨረሻ የስንብት ቃል እና ሽኝት

    አቶ ሰሎሞን አዲስ ታምሩ ባደረበት ህመም ሳቢያ ሚያዚያ 22 ቀን 2026 ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል ። አቶ ሰለሞን ወደ አውስትራሊያ ለመጀመሪያ የመጡት የአቶ አዲስ ታምሩ ሁለተኛ ልጅ ሲሆን ፤ እናቱ ወ/ሮ ሊሊያን ኒኮላስ የአቦርጅናል ዝርያ ያላቸው ናቸው። የጸሎት እና ሽኝት ስነ ስርአቱም በደብረ ሰላም መድሃኒአለም ሜልበርን ቤተክርስቲያን ተከናውኗል። ስርአተ ቀብሩም ሰኞ ሜይ 21 ቀን 2026 በሜልበርን ተፈጽሟል። በሽኝት ስነስርአቱ ላይ በሜልበርን እና በአውስትራሊያ የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል ። በስፍራው ከተገኙት መካከልም ፤ መላክ ጸሃይ ቀሲስ መንግስቱ ሀይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አህጉረ ስብከት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዲሁም የብሪዝበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ : መላከ አርአያም ቀሲስ ተስፋ ኅሩይ - የሜልበርን ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ : አቶ እሸቱ ሙሉጌታ ፤ ወ/ሮ ተኛኜ ወርቅ ብስራት ፤ ጄሰን አዲስ ታምሩ ( ወንድም ) ፤ ታሻ ፊትዝክላረንስ (ሚስት) ወ/ሮ ቅድስት ደስታ ፤ አቶ አበራ አያሌው እና ወ/ሮ ቆንጂት ጥላሁን የተሰማቸው ህዘን ገልጸዋል።

  4. 855
  5. 854

    " እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ " - ወ/ሮ እመቤት አሰፋ የቅድስት ማርያም የኢትዮጵያውያን ሴቶች ማህበር በሲድኒ

    ወ/ሮ እመቤት አሰፋ የቅድስት ማርያም የኢትዮጵያውያን ሴቶች ማህበር በሲድኒ ፤ የዘንድሮውን የእናቶች ቀን ለየት የሚያደርገው አርአያ የሆኑ እናቶችን ሁለት ከኢትዮጵያውያን እንዲሁም ሁለት ከሱዳን የማህበረሰብ አባላት የእውቅና ሽልማትን ማድረጋችን ነው ብለዋል።

  6. 853

    ጎልጎታ - ለሰዓሊና ገጣሚ ገብረ ክርስቶስ ደስታ

    የግጥም በረከት፤ ከከበደች ተክለአብ - ለገብረ ክርስቶስ ደስታ።

  7. 852

    "ለእኔ ገብረክርስቶስ ደስታ በጣም ሀገራዊም፤ ዘመናዊም ነው። በሥራዎቹ ውስጥ የቀረርቶ፣ ፉከራና የቅኔ መንፈስም ይታየኛል" ከበደች ተክለአብ

    በቅርቡ በሀገረ አሜሪካ - ኦክላሃማ ዩኒቨርሲቲ፤ የአንጋፋው ኢትዮጵያዊ ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የጥበብ ሥራዎችና የሕይወት ዘመን አሻራዎቹ ላይ ያተኮረና የዘከረ ሲፖዚየም ተካሂዷል። የሕይወት ዘመን የጥበብ ሥራዎቹን አንስተው ከዘከሩት ተጠባቢዎች መካከል በሥነ ግጥም፣ ሥነ ቀለም ቅብ፣ ቅርፃ ቅርፅና የንድፍ ሥራዎች ዘርፍ ስመጥርና መምህርት የሆኑት ከበደች ተክለአብ ናቸው።

  8. 851

    "ገብረክርስቶስ ደስታ ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል ተብሎ የሚታመነው የ'ዘመናዊነት' ሥነ ጥበብ አሠራርን ኢትዮጵያ ውስጥ ቀድመው ካነሱት አንዱ በመሆኑ ነው" ከበደች ተክለአብ

    በቅርቡ በሀገረ አሜሪካ - ኦክላሃማ ዩኒቨርሲቲ፤ የአንጋፋው ኢትዮጵያዊ ሰዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ የጥበብ ሥራዎችና የሕይወት ዘመን አሻራዎቹ ላይ ያተኮረና የዘከረ ሲፖዚየም ተካሂዷል። የሕይወት ዘመን የጥበብ ሥራዎቹን አንስተው ከዘከሩት ተጠባቢዎች መካከል በሥነ ግጥም፣ ሥነ ቀለም ቅብ፣ ቅርፃ ቅርፅና የንድፍ ሥራዎች ዘርፍ ስመጥርና መምህርት የሆኑት ከበደች ተክለአብ ናቸው።

  9. 850
  10. 849
  11. 848

    ኢትዮጵያ በሱዳን መንግሥት የተሰነዘረበትን ክስ መሠረተ ቢስ ስትል ውድቅ አደረገች

    በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የተነፈገው የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤልን የክልሉ ፕሬዚደንት አድርጎ መሾሙን አስታወቀ

  12. 847

    "በጎ መሥራት ለራስም፤ ለማኅበረሰብም ጠቃሚ ነው። ሁላችንም መንፈሳችንን ወደ በጎ መንገድ መርተን ምሳሌ እንድንሆን በአደራ መልኩ ለማኅበርሰቡ አሳስባለሁ" ወርቅነህ ባይህ

    አቶ ወርቅነህ ባይህ፤ የኩዊንስላንድ አፍሪካውያን ማኅበረሰባት ምክር ቤት የዓመቱ በጎ ፈቃደኛ ተሸላሚ ሆነዋል። ለሽልማት ስላበቋቸው የረጅም ጊዜያት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶቻቸው አንስተው ይናገራሉ።

  13. 846
  14. 845

    Tips to reduce petrol costs | Fuel in Focus - የነዳጅ ዋጋ አቀናነስ ጥቆማዎች | ትኩረት ነዳጅ ላይ

    Rising fuel prices are putting pressure on household budgets across Australia, and for many people, it’s changing the way they travel. So what can you do to reduce your fuel costs without giving up your daily routine? Here are some simple, practical ways to save money on petrol. - በመላ አውስትራሊያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በነዋሪዎች በጀት ላይ ጫናዎችን አሳድሯል። ለአያሌ ሰዎችም የአጓጓዝ ሁኔታቸውን እንዲቀየሩ ግድ አሰኝቷል። እናም፤ የአዘቦታዊ አጓጓዝዎን ሳይቀይሩ የነዳጅ ወጪዎን ለመቀነስ ምን ማድረግ ይችላሉ? ለነዳጅ የሚውል ገንዘብዎን ለመቆጠብ ጥቂት ቀላል፣ ግብር ላይ ዋይ መንገዶችን እነሆን።

  15. 844

    ሀገራዊው የምክክር ጉባኤ ምርጫው እንደተጠናቀቀ ይጀመራል ተባለ

    በኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለ ስልጣናትና ታዋቂ አርቲስቶች ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ምዝበራ እንደፈፀሙ በኦዲት መረጋገጡን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

  16. 843

    #109 Talking about ageing parents (Med) - #109 ዕድሜያቸው እየገፋ ስላሉ ወላጆች መናገር

    Learn English useful for talking about ageing parents and family responsibilities. Practise everyday phrases for describing challenges, offering help, and discussing how to support parents. - ዕድሜያቸው እየገፋ ስላሉ ወላጆችና የቤተሰብ ኃላፊነቶች ለመናገር እንግሊዝኛን መማር ጠቀሜታ አለው። በየዕለቱ ተግዳሮቶችን፣ እርዳታ ልገሳንና ወላጆችን እንደምን ማገዝ እንደሚቻል ገላጭ የሆኑ አባባሎችን ይለማመዱ።

  17. 842

    በኢትዮጵያ በቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሠራተኞችና ኃላፊዎችን በፅኑዕ እሥራት የሚቀጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ

    የትምህርት ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከሁሉም ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚረዳ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

  18. 841

    የፖርት ኧርተር የጅምላ ግድያ 30ኛ ዓመት ዝክረ መታሰቢያ ተከናወነ

    በአውስትራሊያ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን የቪክቶሪያ ክፍለ ሃገር የሌበር መንግሥት የአዋቂና ወጣት ወንዶች ሚኒስትር መሾምን ተከትሎ፤ የፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ የአዋቂና ወጣት ወንዶች ልዑክ ሰየመ

  19. 840
  20. 839

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮችን ምዝገባ እንዲያከናውኑ ከተከፈቱ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል 22ቱ ሕገወጥ ድርጊት በመፈፀማቸው መዝጋቱን አስታወቀ

    የፌዴራል ፖሊስ በቴዲ አፍሮ ጉዳይ ምላሽ ሰጠ፤ የድምፃዊው የቅርብ ወዳጆች የፖሊስን ምላሽ በትክክለኛ መረጃነት አልተቀበሉም

  21. 838

    መብቶቻቸውን ለነፈገቻቸው ሀገር መዋጋት፤ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች የጦር አባላት አገልግሎት ዝክረ መታሰቢያ

    ከአንደኛው የዓለም ጦርነት አንስቶ የአውስትራሊያ ነባር ዜጎች በአውስትራሊያ የመከላከያ ሠራዊት አባልነት አገልግለዋል። ብሔራዊ የዜግነት መብት አልነበራቸውም። ሆኖም ግና ዜግነት የነፈገቻቸው ሀገር በመቶዎች የሚቆጠሩቱን ለወታደራዊ ግዳጅ ባሕር አሻግራ ልካለች።

  22. 837

    "የሐበሻ ማኅበረሰብ መጥቶ ቢያየኝ፤ ቢደግፈኝ ደስ ይለኛል። ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ነገር የሚያገኝበት ትዕይንት ነው" ሶሊያና እርሴ

    ሶሊያና እርሴ፤ ትንፋሽ አስዋጭ፣ የልብ ትርታን ደላቂ፣ ከዮጋም፣ ከጂምናስቲክም ልዩ አካላዊ እጥፋትና ዝርጋታን፣ ልዩ ምትሃት መሰል ክህሎትን ግድ የሚለው፤ ግና ሞገስን ተላብሶ መድረክ ላይ ግዘፍ የሚነሳ Contortionist Extraordinaire ኢትዮጵያዊት ናት። ድንቅ ክህሎቷም ከኤፕሪል 7 እስከ ሜይ 24 በሜልበርን ከተማ Meat Market ከClub Kabarett ጋር ለሕዝብ ዕይታ ይቀርባል። የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላትም ታዳሚዎቿ እንዲሆኑ ትጋብዛለች።

  23. 836

    ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን-እሥራኤል-ዩናይትድ ስቴትስ ተኩስ አቁምን ላልተወሰነ ጊዜ አራዘሙ

    የአውስትራሊያ ፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ ናፍጣ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ከተለያዩ ሀገራት ጋር ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ

  24. 835
  25. 834

    ዩናይድ ስቴትስ የኢራንን መርከብ በቁጥጥሯ ስር አዋለች፤ ኢራን የአፀፋ እርምጃ እወስዳለሁ አለች

    የዋን ኔሽን የሕዝብ አስተያየት ድጋፍ መውረድ ጀመረ፤ ሆኖም ከፌዴራል ተቃዋሚ ቡድኑ ቀድሞ ሔዷል

  26. 833

    የድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን "ቴዲ አፍሮ" ኢቶሪካ አልበም ሬኮርዶችን መስበሩን ቀጥሏል

    ኢትዮጵያ የራሷን ሳተላይቶች በሀገር ውስጥ ለመገጣጠምና መሞከር የሚያስችላትን ግዙፍ የማዕከል ግንባታ ከሩስያ የጠፈር ተቋም ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅቷን ማጠናቀቋ ተነገረ

  27. 832

    "የሴቶች ጉዳይ የተወሰኑ ሰዎች ኃላፊነት ብቻ አይደለም። ሁላችንም ለሴቶች ክብር፣ ነፃነት፣ እኩልነትና በዋናነት ለደህንነታቸው መቆም አለብን።" ናዲያ ሞናያ

    በሥርዓተ ትምህርት፣ የሴቶችና መድብለ ባሕል ተኮር የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ምርምራቸውን በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ እያካሔዱ ያሉት ወ/ት ናዲያ ሞናያ፤ ከፊል የምርምር ግኝቶቻቸውንና ፖሊሲ ነክ ጉዳዮችን አንስተው ያስረዳሉ።

  28. 831

    "ግጥም ውስጤ ያለውን ስሜት የምገልፅበት፣ አንባቢን በእኔ ዓለም ውስጥ፣ ስሜቶቼ ውስጥ የምጋብዝበት መድረክ ነው" ናዲያ ሞናያ

    በዩኒቨርሲቲ Exeter የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናዲያ ሞናያ፤ ምርምራቸው ስለሚያተኩርበት ለውጥ የሚያሻቸው የሴቶች ጉዳዮችና የመድብለ ባሕል ፋይዳዎችን አንስተው ያናገራሉ። ከግጥም ሥራዎቻቸው በቅርቡ "I Hugged a Tree" በሚል ርዕስ ለአባታቸው ዝክረ መታሰቢያ ከፃፉት የስንኝ ቋጠሯቸው በቅንጭቡ ያስደምጣሉ።

  29. 830

    "ከመማር ጋር ኃላፊነት አለ፤ የተማሩትን ለሌላው ማስተላለፍ የራስን ኃላፊነት መወጣት ነው። ለሕይወትም ትርጉም አለው።" ናዲያ ሞናያ

    ናዲያ ሞናያ - በሀገረ እንግሊዝ ኤክስተር ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪ ናቸው። ውልደትና ዕድገታቸው አዲስ አበባ ነው። የኢትዮጵያዊት፣ ኤርትራዊትና ጣሊያናዊት ዝንቅ ብሔራዊ ማንነትን አጣምረው ይዘዋል። ሁለት ሀገርኛና አምስት የውጭ ሀገራት ቋንቋዎች ተናጋሪ ናቸው። የውልደት፣ ዕድገትና የትምህርት ሕይወታቸውን ነቅሰው ያጋራሉ።

  30. 829

    በአውስትራሊያ ጅሎንግ በሚገኝው የነዳጅ ማጣሪያ የእሳት አደጋ ተከሰት

    የአውስትራሊያ ከተሞች የራሳቸውን የነዳጅ ክምችት ለርመፍጠር ቅድመ ዝግጅት ጀምረናል አሉ

  31. 828

    Women’s legal services in Australia: Understanding your options - በአውስትራሊያ ለሴቶች ነጻ የህግ አገልግሎት ተቋማት አማራጮች እንዳሉ ይረዱ

    Workplace discrimination, gender-based violence and financial inequality—these are just some of the reasons why women need dedicated legal services. You don’t have to navigate the legal system alone. In Australia, free legal services exist to advocate for vulnerable women in ways that are safe, confidential and culturally appropriate. - ሴቶች የተለየ የህግ ባለሙያዎች እንዲያስፈልጋቸው ከሚያደርጉት ምክንያቶች መካከል ፤ በስራ ቦታ የሚፈጸም መድልዎ ፤ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ፤ በገቢ ላይ የሚደረግ ማበላለጥ የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው ፡፡ በአውስትራሊያ የህግ ተቋማትን ብቻዎትን ማፈላልገ አይጠበቅብዎትም ፡፡ በችግር ላይ ያሉ ሴቶች ደህንነታቸ በተጠበቀ ሁኔታ ፤ ምስጢራቸው እና ባህላቸውን ባገናዘበ መልኩ ነጻ የህግ አገልግሎት አለ፡፡

  32. 827

    በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ቀውስ በጦርነት አይፈታም ፤ መፍትሄው የሰላም ውይይት ነው - አንቶኒዮ ጉተሬዝ

    በሱዳን ከ 21 ሚልዮን በላይ ዜጎች ለጽኑ ረሀብ እና የምግብ እጦት ተጋልጠዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ወኪል አስታወቁ

  33. 826

    በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች መሠረታዊ አቅርቦት ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተባለ

    በኢትዮጵያ ከአንድ ሚሊየን በላይ ከደቡብ ሱዳን ፤ ኬንያ ፤ ኤርትራ እና ሶማሊያ የተፈናቀሉ ስደተኞች እንደሚኖሩ ተገለጠ

  34. 825

    በሺህ የሚቆጠሩ አራናውያን አሜሪካ በሆርሙዝ የጣለችውን ገደብ በቃወም ለሰልፍ ወጡ

    የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ተከትሎ የኡበር አሽከርካሪዎች ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ ዋጋ እንዲያስከፍሉ ደንብ ወጣ

  35. 824

    "ይህ የትንሣኤ በዓል ለሁላችንም የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመሰባሰቢያ፣ ራሳችንን የመጠየቂያ በዓል እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን" ቀሲስ መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ

    መልአከ ፀሐይ መንግሥቱ ኃይሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ የምስራቅ አውስትራሊያ እና ኒውዚላንድ አኅጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የብሪስበን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የበዓለ ትንሣኤን ትርጓሜ ያስረዳሉ። የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

  36. 823

    "እንኳን ለበዓለ ትንሣኤ አደረሳችሁ! እግዚአብሔር ሀገራችንን ኢትዮጵያንና መኖሪያችንን አውስትራሊያን ይባርክ" ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ

    ወንጌላዊ የምሩ ታደሰ፤ በዘፀዓት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አገልጋይ፤ የፋሲካ በዓልን አስመልክተው የ ‘እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን’ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

  37. 822

    "የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብን ሁለቱንም ወላጆች ላጡ ተፈናቃይ ልጆች ላደረጉት ትልቅ አስተዋፅኦ እናመሰግናለን" ወ/ሮ ገነት ቤተ ጌራወርቅ የም/ቤት አባል

    ወ/ሮ ገነት ቤተ ጌራወርቅ፤ በደብረ ብርሃን ከተማ የኤፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና በደብረ ብርሃን መጠለያ ቻይና ካምፕ ተጠላይ እናት ሩቂያ አሕመድ ስለ ተፈናቃዮች ሕይወት፣ በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር አስተባባሪነት ሁለት ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት ስለተደረገላቸው ሰብዓዊ እርዳታ አንስተው ይናገራሉ። ልባዊ ምስጋናቸውንም ያቀርባሉ።

  38. 821

    ለጋሽ እጆች ከደቡብ አውስትራሊያ እስከ ደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች

    የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት ዶ/ር ለገሰ ጋረደው፣ የደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት አቶ ጥላዬ ተከተልና አቶ መሐመድ በያን፤ እንደምን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ከወለጋ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን መጠለያ ካምፖች ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ልገሳቸውን እንደቸሩ ይናገራሉ።

  39. 820

    "የኢትዮጵያን ሙዚቃ ካልነበረበት ወደ ነበረበት ያደረስነው በ60ዎቹ ጊዜ ነው" ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ

    የአደራ ቃል "አውስትራሊያ ላላችሁ ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ከልባችሁ አታውጡ። ምንም ይሁን ምን - እንደ ሀገር የሚሆን ነገር የለም" ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ (ዳግም የቀረበ)

  40. 819

    አንጋፋው ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ፤ ከሀገር ቤት እስከ አሜሪካ

    አንጋፋው ድምፃዊ ተሾመ ምትኩ፤ ገጣሚና ሙዚቃ ቀማሪም ነው። ከሙዚቃ ዓለም አዘላለቁ እስከ ስደት ሕይወቱ አንስቶ ያወጋል። (ዳግም የቀረበ)

  41. 818

    ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን ጥቃታቸውን ለሁለት ሳምንታ ሲገቱ፤ ኢራን በበኩሏ ለሁለት ሳምንታት የሆርሙዝ ባሕረ ሰላጤ መተላልፊያን እከፍታለሁ አለች

    የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ አባል ፕሬዚደንት ትራምፕን ኮንግረስ ከፕሬዚደንታዊና ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥነት ስልጣናቸው እንዲያነሳቸው ጥሪ አቀረቡ

  42. 817

    ፋና ወጊዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በ84 ዓመታቸው ከእዚህ ዓለም ተለዩ

    የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩና ከ100 በላይ ሰዎችም ለሞት እንዲዳደረጉ ምክንያት ነው ያለውን ተጠርጣሪ ሕገ ወጥ አዘዋዋሪ ትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ

  43. 816

    የአውስትራሊያ የላቀ የጦር ሜዳ ጀብዱ ኒሻን ተሸላሚ በአፍጋኒስታን የጦር ወንጀል ተጠርጣሪነት ለእሥር ተዳረገ

    በወርኃ ማርች በአንድ ወር ውስጥ ብቻ በአውስትራሊያ ታሪክ ከፍተኛውን ሬኮርድ የያዘ የአዲስ ኤክትሪክ መኪና ሽያጭ ተመዘገበ

  44. 815

    የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባኤ መካከለኛው ምሥራቅ 'ሊጋይ' እንደሚችል አሳሰቡ

    አውስትራሊያ ለተጨማሪ አንድ ወር የሚበቃ የነዳጅ አቅርቦት እንዳላት የፌዴራል መንግሥቱ አስታወቀ

  45. 814

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለአንድ ወር ሲያካሒድ የቆየውን የምርጫ ምዝገባ ለሁለት ሳምንታት አራዘመ

    ኢትዮጵያ በቡድን 20 ማዕቀፍ ስር ከቻይና ያለባትን ዕዳ መልሶ ለማዋቀር ከቻይና መንግሥት ጋር መግባባት ላይ መድረሷ ተነገረ

  46. 813

    የመኪና መንዳት ስልጠና ለለማጆች መጀመር ያለበት ከወላጆች፣ ወዳጆች ወይስ ባለሙያ አስልጣኞች?

    "አንዱ ዓላማችን ማኅበረሰቡን ማገልገል ነውና በአቅም ውስንነት የመንጃ ፈቃድ ለሌላቸው አንዲት ሴትና አንድ ወንድ ነፃ የመኪና መንዳት ስልጠና እንሰጣለን" ያሉት አቶ ግዛቸው መኮንን፤ የፍቅር ለማጅ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ ማሰልጠኛቸው የምሥረታ ዓላማና የአገልግሎት ዘርፎች ይናገራሉ።

  47. 812

    "ማኅበራዊ አንቂ መሆን አለብን፤ ሀገራችን ውስጥ ብዙ የሚሠሩ ማኅበራዊ ነገሮች አሉ" ሶስና ወጋየሁ

    ለወ/ሮ ሶስና ወጋየሁ፤ የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት መሥራችና የኢትዮ - ሰርከስ ኢንተርቴይንመንት ዳይሬክተር፤ ላቋቋመችው የጋሞ ሰርከስ ትምህርት ቤት በሜልበርን- አውስትራሊያ ሚሊኒየም ሃውስ የማኅበረሰብ ማዕከል የተካሔደ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ድጋፍ።

  48. 811
  49. 810

    ጠ/ሚ አንቶኒ አልባኒዚ ዛሬ ከምሽቱ 7:00 pm የመካከለኛ ምሥራቅ ጦርነትን አስመልክተው ለመላ አውስትራሊያውያን በሬዲዮና ቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ንግግር ሊያደርጉ ነው

    ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የዩናይትድ ስቴትስ፣ እሥራኤል፣ ኢራን ጦርነት ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት ጊዜያት ውስጥ ሊያከትም እንደሚችል አመላከቱ

  50. 809

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ በረራዎችን በከፊል ማስጀመሩን አስታወቀ

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ እንዳለ ገለጠ

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።

HOSTED BY

SBS

Produced by SBS Audio

CATEGORIES

URL copied to clipboard!