EPISODE · Dec 9, 2025 · 1H
ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት፡ ለምዕራባዊያን የወገነው ማንነቱ ሲገለጥ
from Sovereignty Sources
''የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ገለልተኛ አይደለም። የፍርድ ቤቱ ፍልስፍናም ያለምንም ማቅማማት የአውሮፓውያን ነው — በተግባር ሲፈተሽ የምዕራቡን የህግ ፍልስፍልና ነው በሥራ ላይ የሚያውለው። የቅኝ ግዛት አሻራ፣ የምጣኔ ሐብት ብዝበዛ ያሉ ስር መሠረቶችን የሚዘነጋ ነው፣ በዚህ የተነሳ ፍትህን ማስፈን ተስኖታል'' - ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮ አንትሮፖሎጂ መምህሩ መሃመድ አወል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን የዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከአውሮፓዊ መሠረቱ ባሻገር በዓለም ላይ ለሚፈፀሙ ኢ - ፍትህና እና መድሎዎች መፍትሄ ለመስጠት እንዴት ዓለም አቀፍ ዕይታ የለውም በሚለው ጉዳይ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዮ አንትሮፖሎጂ መምህሩ መሃመድ አወል ሀጎስ ሀሳባቸውን ያጋሩናል። አፍሪካ ከውጪ ጣልቃ ገብነት በመላቀቅ አስተማማኝ ልማትን ለማጎልበት ሰላምና ደኅንነትን የሚፈጥር ፖሊሲና ልምምድ ሊኖር እንደሚገባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦኢንቫይሮመንታል መምህሩ ያዛቸው ውድነህ ጋር ያደረግነው ቆይታም የፕሮግራማችን ሌላኛው አካል ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
ዓለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት፡ ለምዕራባዊያን የወገነው ማንነቱ ሲገለጥ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.