Sovereignty Sources podcast artwork

PODCAST · society

Sovereignty Sources

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

  1. 115

    የፊፋ 2026 የዓለም ዋንጫ ውዝግቦች

    ''እንደኔ አሜሪካ በኢራንና በሶማሊያዊው ዳኛ ላይ የያዘችው አቋም የፖለቲካ አቋም ነው። ለነዚህ ሀገራት ያላት አመለካከት ምን ይመስላል የሚለውን ነገር ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል —ፊፋ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ድጋሚ እንዲፈጠሩ መፍቀድ የለበትም '' ሲል አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ ከሰሞኑ በካናዳ፣ ሜክሲኮና አሜሪካ አማካኝነት እየተሠናዳ የሚገኘው የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውዝግቦችን ከሜዳና ውስጥና ሜዳ ውጪ ክስተቶች ጋር በማጣመር እንወያያለን። አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱና ሌላኛው የስፖርት ጋዜጠኛ ሳምሶን አበበ ሙያዊ ዕይታቸውን አጋርተውናል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  2. 114

    የሳተላይት ቴክኖሎጂን የማጎልበት ሀገራዊ ህልም

    ''የሳተላይት መረጃ በመሠረታዊነት ነገሮች ከመባባሳቸው በፊት ቅድመ እና ወቅታዊ መረጃ ይሰጣል። ለምሳሌ የሳተላይት መረጃን በመጠቀም የሰብል ውድቀትን አስቀድሞ ለመተንበይ ወይም ለመገመት እንችላለን ምክንያቱም ከሳተላይቶች፣ በጣም ትንሽ የሆነ የእርሻ ቦታን መመልከት እና የእያንዳንዱን ሰብል የጤና ሁኔታ በጥልቀት መመርመር ስለሚችሉ ብለዋል -- ኪሩቤል መንበሩ አለሙ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።''ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የሳተላይት ቴክኖሎጂ እና የአየር ንብረት ቁጥጥርን በተመለከተ በኢትዮጵያ ውስጥ ድርቅን፣ ዝናብ እና5 የመሬት መራቆትን ስለመከታተል ኪሩቤል መንበሩ አለሙ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያይተናል።በክፍል ሁለት እንደ ብሪክሱ አዲስ የልማት ባንክ ያሉ ተቋማት የአፍሪካ ባንኮች ስርዓታቸውን በማዘመን በቂ አገልግሎት ላልተዳረሰባቸው ማኅበረሰቦች የፋይናንሺያል ተደራሽነትን ለማስፋት እንዴት እንደሚረዱ ፕላሲዲየስ ካስቱስ (ኢንጂነር) በታንዛኒያ የግል የንግድ ድርጅት ባለቤት ምልከታቸውን አጋርተውናል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  3. 113

    ዓለም ወደ ባለብዝሃ ወገን የፖለቲካ ስርዓት የምታደርገው ፈጣን ጉዞ

    ''ቻይናን፣ ሩሲያና ህንድ የመሳሰሉ ሀገራት የራሳቸውን አሻራ እያስቀመጡ ነው እየመጡ ያሉት፤ ጠንካራ የሚባል ኢኮኖሚ፣ ሰራዊት፣ ዲፕሎማሲ ገንብተዋል። በተለይ ከግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት እየፈጠሩ ነው — የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ ስርዓት ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተለወጠ እንደሆነ ማየት እንችላለን '' ሲሉ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ለስፑትኒክ አፍሪካ  ተናግረዋል።በዛሬው ፕሮግራማችን የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የዓለም ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓትና የወደፊት ዕጣን በተመለከተ በደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ደረጄ መለስ ጋር እንቃኛለን። በክፍል ሁለት የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አገራዊ ፖሊሲዎችን ከአህጉሪቱ የጋራ ፍላጎቶች ጋር የማጣጣም አስፈላጊነትን በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ለሚ ጋር እንዳስሰዋለን።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  4. 112

    ሩሲያ በአፍሪካዊያን ዓይን እንዴት ትታያለች? በሚዲያ የሚነገረው መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር ሲነፃፀር

    '' በምዕራቡ በኩል የሚነገረው ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ እረዳለሁ። አብዛኛው የሚነገረው እውነት የሆነ፣ መሬት ያለው ነገር አይደለም። ዛሬም ያ ነገር ቀጥሏል። ይሻሻላል ተብሎ ቢጠበቅም ያው ነው አሁንም — ያንን ሀገር ፈርጆ ላይ ላዩን ሊጭኑብህ የሚፈልጉት ነገር አለ '' ሲሉ የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪ ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሱበበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ ሩሲያ በአፍሪካዊያን ዓይን እንዴት እንደምትታይ መሰረት በማድረግ የቀደመ የሚዲያ ትርክቶችን መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር በማነፃፀር የቀድሞ የሶቪየት ኅብረት ተማሪ ክብሩ ቸርነት (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በኢራን ጦርነት ሳቢያ ከተፈጠረው የኃይል አቅርቦት ጋር በተገናኘ እንደ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ አፍሪካዊ ፕሮጀክቶች ችግሮችን ለመቋቋም የሚኖራቸውን ፋይዳ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ዳይረክተር ሞገስ መኮንን ጋር ዳሰነዋል፡፡   ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  5. 111

    አፍሪካን ከውጪ ከሚሸመቱ ምግቦች የማላቀቅ ፋይዳዎች

    ''ያሉንን የተፈጥሮ ኃብቶች በአግባቡ እየተጠቀምን አይደለም። የግብርና መሠረተ ልማት ከፍተኛ ምርት ለማውጣት እንደ ጀርባ አጥንት የሚወሰድ ነው — መንግስታት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ቢታወቅም ከውጪ የሚሸመቱ ምግቦችን ለመቀነስ አሁንም ብዙ ነገሮች ይጠበቅባቸዋል '' ሲሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ አብራርተዋል።ሁለት ጉዳዮች በሚቃኙበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ከፍተኛ የተፈጥሮ ኃብት ያላት አፍሪካ ስለምን በከፍተኛ ሁኔታ ከውጪ ተሸምተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምግቦች ጥገኛ ሆነች ደግምስ ቀጣዩ ዘመናት ምን መምሰል አለባቸው ስንል በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በአፍሪካ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት። ከስኬቷ ጀርባ ያለውን ምስጢር እና ሌሎች ሀገራት ሊውስዱ የሚችሉ ተሞክሮዎችን ምሪሺየሳዊ የምህንድስና እና የከተማ ቄየሳ ባለሙያው ቪነሽ ቺንታራም አስረድተውናል።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  6. 110

    የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ነው ?

    ''ዋሽንግተን መሪዎችን በመግደል እና ኃይሏን በመጠቀም ኢራንን በአጭር ግዜ ውስጥ አንበረክካለሁ ብላ አስባ ነበር። በተቃራኒው ኢራን ድብደባዎቹን ተቋቁማ፤ መከላከሏን ቀጠለች እንዲሁም የጦር ሜዳውን ወደ ባሕረ ሰላጤው፣ ወደ አረቦች እና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች አስፋፍታለች። በዚህም አሜሪካ የበላይነቷን አሳያለሁ ብላ ድክመቷን አጋልጣለች ”- የወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም በክፍል አንድ የዓለም አሃዳዊ ዋልታ የኃይል ስርዓት እያከተመ ስለመሆኑ ከጂዮፖለቲካዊ አኳያ ከወራቤ ዩኒቨርስቲ መምህር መሃመድ አዎል ሀጎስ ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል በአፍሪካ ያለውን የጸጥታ እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃገብነት ጉዳይ ከሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰር ጋር ቃኝተነዋል። በመጨረሻው ክፍል ከሚያዝያ 8-9 ፣ 2026 በአዲስ አበባ የተካሄደው የአደጋ ስጋት አስተዳደር አቅምን በተመለከተ ከቻርሎት ኖርማን፣ የጋና ብሔራዊ የአደጋ አስተዳደር ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር ጋር ዳሰነዋል።ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  7. 109

    የሀገር በቀል እውቀት ለብዝሃ ህይወት ጥበቃ

    ዓለም የባዮሎጂካል ብዝሃነት ዓለም አቀፍ ቀንን በፈረንጆቹ ግንቦት 22 ቀን ያከብራል።'' አፍሪካ ለአየር ንብረት ለውጥ የተጋለጠች አህጉር ነች፣ በእርግጥ አንድ ዓይንት  ስነ ምህዳር አይደለም ያላት። ስለዚህ ይህ የሀገር በቀል እውቀት ለብዝሃ ህይወት ይጠቅማል። ብዝሃ ህይወት ስንል ብዙ ዝርያ ያላቸው እንስሳት፣ ዕፅዋትና ደቂቀ ነፍሳትን አንድ ላይ የያዘ ነው ''  - ሲሉ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካን ስነ ኑረቶችና ብዝሃ ህይወትን ለመጠበቅ ሀገር በቀል እውቀቶች ያላቸውን ሚናዎች የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ብዝሃ ህይወት ጥበቃ ዋና ዳይሬክተሩ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ጋር ቆይታን አድርገናል። በክፍል ሁለት አፍሪካ በዓለም አቀፍ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ዕድገት ጉዞ ያላትን ቦታ ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሰርቨር ቁጥጥርና አስተዳደር ባለሙያው ታደሰ ፀሃይነህ ጋር ቃኝተነዋል።   ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  8. 108

    የታሪክ ማህተም፦ የሩሲያ 81ኛው የድል በዓል

    ''ራሺያኖች ሉዓላዊነታቸውን በመጠበቅ፣ ራሳቸውን በማስታጠቅ እና በአርበኝነት ረገድ በጣም ጥሩ ናቸው። ባህላቸውም በሚገባ የጎለበተ እና የተብላላ ነው። ስለዚህ አፍሪካዊያን ከእነርሱ ጋር ምንም ዓይነት የቅኝ ግዛት ግንኙነት ከሌላት ራሺያ ብዙ መማር ይችላሉ '' ሲሉ የእዮብዘር ዘውዴ በአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝቀት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የራሺያ 81ኛው የድል ቀንን መሠረት በማድረግ ከፓን አፍሪካኒዝም አንድነት ጋር በማስተሳሰር የዮብዘር ዘውዴ በአዲስ  አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር ጋር በስፋት እንወያያለን። በክፍል ሁለት ከፈረንጆቹ ግንቦት 7 - 8፣ 2026 በአዲስ አበባ ስለተከናወነው የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔን በተመለከተ እውቁ ጋናዊ ዩቱበር ዎዴ ማያ ሀሳቡን ያካፍለናል።  ሙሉውን መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  9. 107

    ህጻናትና ወጣቶችን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ጫናዎች የመጠበቅ ኃላፊነት

    ''አሁን ላይ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለው ነገር አስፈሪ በሚባል ደረጃ እየሄደ ያለ ነው። የተለያዩ ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው። እነዚህ ልጆችም ለማይሆኑ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ — የዲጂታሉ ዓለም ገደብ የለውም። ከስነልቦና፣ ከእውቀታቸውና ራሳቸውን መቆጣጠር ከሚችሉበት በላይ የሆኑ ነገሮችን እየተመለከቱ ለብዙ ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ። ጥፋቱ ከፍተኛ ነው ማለት እንችላለን - '' ሲል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋራው ብሩክ ጫላ ለስፑትኒክ አፍሪካ አፍሪካ ተናግሯል ።ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ዝግጅቱ በክፍል አንድ ታዳጊ አፍሪካውያን ህጻናትን ከሳይበር ጥቃት፣ ብዝበዛ እና ካልተፈለጉ ጫናዎች ስለመከላከል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሜካኒካል ምህንድስና መምህሩና የማኅበራዊ ሚዲያው ተጽዕኖ ፈጣሪና የመረጃ ሰጪ ይዘት ያላቸው ዜናዎችን በቲክቶክ የሚያጋረው ብሩክ ጫላ ዕይታውን ያጋራናል። ክፍል ሁለት እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ እና የዓለም ባንክ ባሉ ተቋማት በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖን በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ ደረጄ መለስ ጋር እንወያያለን። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  10. 106

    ኢራንን እንደ ሀገር ያቆማት ጠንካራ ብሔራዊ ማንነት

    ''መሪዎችን መግደል፣ ዜጎችን መግደል፣ ሁሉም ነገር እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ግፍ ነው። እኛ የምንላችሁን ስሙ፣ እኛ ኃያላን ነን፣ ሁሉንም ነገር ማድረግ እንችላለን ነው የሚሉት። ኢራን በቀጥታ የተፈፀመባት ወረራ ነው -'' ሲሉ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አሌክሳንደር ኃይማኖት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በክፍል አንድ ሰሞነኛው የኢራን - አሜሪካ - እስራኤል ግጭትን መሠረት አድርገን በህገወጥ መንገድ በተለይም በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ስለሚደረጉ የመንግስት ለውጥ ከሀገራት ሉዓላዊነት እና ህጋዊ አንድምታዎች አኳያ በራያ ዩኒቨርሲቲ የሰላም፣ ግጭትና ልማት መምህርና ተመራማሪው ዶ/ር አሌክሳንደር ኃይማኖት ጋር ተወያይተናል።  በክፍል ሁለት ከሩሲያ - ኢትዮጵያ ንግድ ፎረም መነሻነት በሀገራቱ መካከል ያለ የሁለትዮሽ ንግድ ግንኙነትን ከዋሲሁን ፍቅሬ የኢትዮጵያ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሮዝዳነት ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር ዳሰናል።   ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  11. 105

    በባለብዙ ወገን ዓለም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የወደፊት እጣፈንታ

    '' የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለይ ከጎርጎሮሲያኑ 2000 ወዲህ ከፍተኛ ችግሮች እየገጠሙት ይገኛል — የተቋቋመበትን የዓለም አቀፍ ሰላምና ድኅንነትን የማስፈን ተግባር በተቋቋመበት ዓለማ አስጠብቆ እየሄደ ነው ለማለት አዳጋች ነው። ስለዚህ ባለብዘ ወገን ስርዓት እየተፈጠረ ባለበት ዓለም ተገዳዳሪ አየሆኑ የመጡ ሀገራትን ያካተተ፣ ድምፃቸውንም የሚያስተጋባ መሆን አለበት'' - ሲሉ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ ዓለም ከነጠላ የፖለቲካ ስርዓትና አስተዳደር ወደ ባለብዙ ወገን ስርዓት እየተሸጋገረች ባለችበት በዚህ ወቅት የዓለም ሀገራትን በአንድ አቅፎ የያዘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጣይ እጣፈንታ ምን ሊመስል ይችላል የሚለውን ጉዳይ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ጋር ዳሰነዋል።በክፍል ሁለት በቅርብ ወደ ትግበራ የገባው የሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ ወይም ‘ስማርት ፖሊስ ስቴሽን ጉዳይ ኢንስፔክተር አንድነት ሲሳይ፤ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ኦፕሬሽን ዋና ክፍል ኃላፊ አጠቃላይ ቅኝት ያደርጉልናል፡፡  ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  12. 104

    የዩሪ ጋጋሪን ውለታ፡ የመጀመሪያው ጉዞ ወደ ህዋ

    ''ስፔስ ሳይንስን ልዩ የሚያደርገው የማናውቀውን ነገር ለማወቅ ጥረት የምናደርግበት ነው። በዚህ ረገድ የስፔስ ሳይንስ ምርምር መስመር እንዲይዝ ዩሪ ጋጋሪን መሰረት የጣለ ታላቅ ሰው ነው - ሲሉ የዘርፉ ተመራማሪው አለምዬ ማሞ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።" በዛሬው ፕሮግራም በክፍል አንድ በየዓመቱ በጎርጎሮሲያኑ መጋቢት 12 የሚከበረውን የሰው ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዋ የተጓዘበትን ቀንና የህዋ ሳይንስ ጉዳይ ከኢትዮጵያ ኑውክላር አነርጂ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ አብድረዛቅ ኡመር እና የስነ ህዋ ተመራማሪው ዶ/ር አለምዬ ማሞ ጋር ጥልቅ ምልከታ ተከናውኗል። በመካከለኛው ግጭት ሳቢያ በንግድና ፋይናንስ ላይ ተፅዕኖ ቢፈጥሩም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ጫናውን ለመቋቋም የገንዘብ ፖሊሲውን እንደሚያስቀጥል ስለመግለፁ ከባንክ፣ ኢንሹራንስ እና የማርኬቲንግ ባለሙያው አስቻለሁ ታምሩ ጋር የምናደርገው አጭር ቆይታም የፕሮግራማችን ሌላኛው አካል ነው። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  13. 103

    የትንሳዔ በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች

    ''እኛ ፋሲካ የምንለው የክርስቶስ ትንሣኤ በዓል፣ በአጠቃላይ በክርስትና ትውፊት ውስጥ በተለይ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዋና ዋናዎቹ እና እጅግ በጣም አስፈላጊ ከሆኑት በዓላት አንዱ ነው — የመጽሐፈ ሄኖክ እና ኩፋሌ፣ በተለይም ደግሞ የሄኖክ መጽሐፍ፣ ሙሉ ይዘቱ በግዕዝ ቋንቋ፣ በኢትዮጵያ ብቻ ይገኛል። ከጥቂት መቶ ዓመታት በፊት ጄምስ ብሩስ የተባለ አንድ እንግሊዛዊ ተጓዥ የሄኖክን መጽሐፍ ከጣና ሐይቅ አካባቢ በስጦታነት ተቀብሎ ወደ አገሩ ወስዶታል። ለጉብኝቱ እና ለኢትዮጵያ ቆይታው እንደ ስጦታ በወቅቱ ከነበሩት የኢትዮጵያ ንግሥቶች በአንዷ፣ በንግሥት ምንትዋብ ተሰጥቶታል።'' - ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንየነገረ መለኮት ምሁር መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ፈለቀ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው ልዩ የሶቨርኒቲ ሶርስስ ዝግጅታችን፣ የትንሳኤ በዓልን መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶችን እንዲሁም ከምዕራባዊያን የበዓል አከባበር ጋር ያለውን ልዩነት እንግዳችን መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል ፈለቀ ያስረዱናል። ሙሉውን መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  14. 102

    የፀጥታና ደህንነት ጥገኝነት ያስከተለው መዘዝ:- የምዕራባውያን ሚና በመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ

    ''የመካከለኛው ምሥራቅ በተለይም የአረብ ሀገራት የውጭ ግንኙነታቸው፣ ከፀጥታ ጋር የተገናኘው በአሜሪካ ላይ ጥገኛ እንደሆነ እናውቃለን — የአረብ ሀገራት በአንድም በሌላ መንገድ የሚኖራቸው የመልስ ምት ወሳኝ ነገር ነው'' - በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህሩ መሃመድ ሰዒድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ በግጭት ወጥመድ ውስጥ የሚገኙት የአረብ ሀገራትን መነሻ በማድረግ የምዕራባዊያን ተፅዕኖዎችና የድሮን ጦርነቶችን በወልዲያ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት መምህሩ መሃመድ ሰዒድ ጋር እንዳስሳለን። በከፍል ሁለት ስለኢነርጂ እና ኢንዱስትሪያልዜሽን መጎልበት በተለይም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን በሚመለከት በዘርፉ ኤክስፐርት ከሆኑት አበጀ መንገሻ ጋር እንወያያለን። ሙሉውን መረጃው ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  15. 101

    የኦቲዝም ቀን በኢትዮጵያ፦ ማኅበራዊ መገለልን ድል የነሳው የ24 ዓመታት የጽናት ጉዞ

    "ልጄ 10 ዓመት እስኪሞላት ድረስ እናቴ ከሶፋ ጋር እያሰረችልኝ እኔ መስተንግዶ እሰራ ነበር። 'ከእሷ ጋር አትሁኑ' ተብዬ ለማኅበረሰቡ መጥፎ ምሳሌ ተደርጌ ነበር፤ 'ትምህርት ያቆመችው እንዲህ ዓይነት ልጅ ወልዳ ነው' ይባላል። ጫናው እናቴን እስከመጨረሻው መቃብር ውስጥ እስኪከታት ደርሶ ነበር። [...] መጀመሪያ 'ከእሷ ጋር አትሁኑ' ተብዬ ለማኅበረሰቡ መጥፎ ምሳሌ ተደርጌ ነበር። ዛሬ ግን ልጄ ቦርሳዋን አዝላ ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ እናቴ 'በቃ ልጄ ዛሬ ከበሽታ ድናለች' ብላ ተደሰተች።አሁን ከአሁን በኋላ ምንም እስራት የለብኝም፤ እንደ ልጅነቴ መስራት፣ መማርና የምፈልገውን መሆን እንደምችል አውቄያለሁ።" — ስትል የኦቲዝም ያለባት ልጅ ወላጅ እናት የሺእመቤት ዘለቀ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች ። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በልዩ መሠናዶው በኢትዮጵያ ዛሬ መጋቢት 24 ስለሚከበረው የዓለም የኦቲዝም ቀን ከእሌኒ ዳምጠው፣ የኒያ ፋውንዴሽን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ አዜብ ገ/ስላሴ በማዕከሉ መምህር እንዲሁም የሺዕመቤት ዘለቀ፣ ከኦቲዝም ጋር አብራ የምትኖር ልጅ እናት ጋር ተወያይተናል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  16. 100

    ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ ለመላቀቅ የአፍሪካ ኅብረትን የማጠናከር አንድምታዎች

    ''በአህጉር ደረጃ አፍሪካ በ2063 ልትደርስበትና ልታሳካ በምትችለው ነገር ሀገራቱ አንድ ዓይነትና የጋራ ራዕይ ኖሯቸው ግልፅ በሆነ መርሃ ግብር መተግበር አለባቸው — አፍሪካ አንደ አህጉር መጠንከር ካለባት ሀገራት ያላቸው ራዕይና ግብ አህጉሪቱን ካስቀመጠችው ጋር የተጣጣመ መሆን ይኖርበታል '' ሲሉ በወልድያ ዩኒርቨሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሽሽጉ ዓለሙ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሰፋ ያለ ውይይት በምናደርግበት የዛሬው ሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የልማት ፖሊሲዎችን በማቀናጀት ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ ነፃ የሆነ አውድን ለመፍጠር የአፍሪካ ኅብረትን ስለማጠናከር በወልድያ ዩኒርቨሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ሽሽጉ ዓለሙ ጋር እንቃኛለን።10ኛው የአበባ አትክልት እና ፍራፍሬ ኤክስፖን መሰረት በማድረግ ስለአቮካዶ ምርት የእሴት ሰንሰለት ከካሳሁን አርሰቻ፣ በሲዳማ ኢንዲስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ከፍተኛ ባለሙያ ጋር የተደረገው ቆይታ የፕሮግራማችን ሌላኛው አካል ነው።  ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  17. 99

    የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ትውውቅ በኢትዮጵያ ሙዚቃ

    ''ይህ የሙዚቃ ቴክኖሎጂ በእኛ ሀገር ኢንዱሰትሪ ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ መምጣቱ ዕድል ነው። በእርግጥ በኢትዮጵያ የትውውቅ ደረጃ ላይ ነው ያለው ማለት እንችለላለን — ግን በመምጣቱ ብቻ፣ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በመቀላቀሉ ብቻ አዲስ ዓይነት ድምፅ፣ ቅንብር፣ የሙዚቃ መሣሪያ መሥራት ለናፈቃቸው፤ ከዛም ባለፈ የሚፈራ የነበረው አደጋችና አልፊ የነበረው የመሉ ባንድ ዓይነት ስሜት ያላቸውን ሙዚቃዎችን ለመሥማት ዕድልን የፈጠረ ነው '' ሲል በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ 'ቀሽቲ' እና 'መኖር' አልበሞች የግጥምና ዜማ አዘጋጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ሁለት አንኳር በምንዳስስበት ፕሮግራማችን የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ትውውቅ በኢትዮጵያ ሙዚቃ በተመለከተ በሠው ሠራሽ አስተውህሎት ቴክኖሎጂ እገዛ በራሱ የግጥምና ዜማ ዝግጅት 'ቀሽቲ' እና 'መኖር' የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ከሠራው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ብርሃኑ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት በአፍሪካ የቢዝነስ አውትሶርሲንግ ካምፓኒዎች ያላቸውን ሚና በጋና የቢዝነስ አውትሶርሲንግ አገልግሎቶች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ዴቪድ ጋር ዳሰነዋል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  18. 98

    የሆርሙዝ ሰርጥ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ዓይን ሲቃኝ

    ''የኢነርጂ ዋጋ እየተመነጠቀ ነው፣ ተፅዕኖውንም እያስተዋልን ነው፤ የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ከዓለም ፖለቲካ ትይዩ የሆነ ስርዓት መፍጠር ይኖርባቸዋል — የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ድምፅ የሚሆናቸው ያስፈልጋቸዋል፣ በዚህም የስፑትኒክ አፍሪካ ጥረት የሚደነቅ ነው።'' ሲል ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ቢንያም ካሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል። ሦስት ጉዳዮች በምንዳስስበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ በኢራን ጦርነት የተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ በደቡባዊ ዓለም ሀገራት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖን ከጋዜጠኛ ቢንያም ካሴ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት ስለአፍሪካ ከተሞች ዕድገት በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ቤካ መገርሳ ጋር ተወያይተናል። በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ከኃይል አቅርቦት አጣብቂኝ ውስጥ ሲገባ እንደታላቁ የህዳሴ ግድብ ያሉ ፕሮጀክቶች አማራጭ ምንጭ የመሆናቸውን ሚና በተመለከተ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ጋር ያደረግነው ቆይታም የፕሮግራሙ ሌላኛው አካል ነው።   ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበው ፕሮግራም ያዳምጡ:

  19. 97

    የቅኝ ግዛት ባህልን ለመንቀል ቶጎ ያቀረበችው የአፍሪካ አዲስ ዓመት ሀሳብ

    ''መሠረታዊው ነገር እሪካዊያን ተግባራዊ አንድነት፣ ተምሳሌታዊ አንድነት፣ የፓን አፍሪካኒዝም ወንድማማችነት እንዲሁም ከቅኝ ግዛት ባህል መውጣት ነው በዚህ የቶጎ ጉዳይ ውስጥ እንደ አነሳሽ ሀሳቦች ሆነው የሚታዩት። ደግሞም በተቋም ደረጃ ለምሳሌ ለአፍሪካ ኅብረት ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል - ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዕዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' በክፍል አንድ የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ቶጎ ባህላዊው ቅኝ ግዛትን በመቃወም አፍሪካ የራሷ የዘመን መቁጠሪያ፣ አዲስ ዓመትም ያስፈልጋታል በሚል በይፋ ያቀረበችውን ምክረ ሀሳብን ከተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አውዶች አኳያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዕዮብዘር ዘውዴ ጋር እንወያያለን፡፡ በክፍል ሁለት ደግሞ በክርስትና እና በእስልምና እምነት ዘንድ ያሉትን አበይት አጽዋማት መነሻ አድርገን ስለመረዳዳትና ሃይማኖቶች እንዴት የማህበራዊ እሴት ማጠናከሪያ እንደሚሆኑ በእስልምና ጥናት ተመራማሪ እንድሪስ ሞሃመድ (ዶ/ር) ቃኝተነዋል፡፡  ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  20. 96

    የምዕራቡ ዓለም ሚዲያዎች ዝምታ፦ በኢራን ጉዳይ ላይ ለምን ''መረጃን መደበቅ'' መረጡ?

    ''የምዕራባዊያን ሚዲያዎቹ ህፃናት፣ ሴቶች እንዲሁም አረጋዊያንን ከግምት ሳያስገቡ ነው ከኢራን በኩል ያለን የደኅንነት ስጋት ለማስወገድ በሚመስል ጉዳዩን እየቃኙ ያሉት - ሲሉ በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' በዛሬው የሶርቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን የኢራን ጦርነትነን መሠረት አድርገን የምዕራባዊያን ሚዲያዎች ሚዛን አልባ ዘገባዎች እንዲሁም በአንዳንድ ጉዳዮች የሚያሳዩትን ዝምታ እንቃኛለን። ለዚህም በፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት መምህሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) እና በወሎ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህሩ ኢብራሂም ሰይድ አህመድ ደግሞ ሙያዊ ምልከታቸውን አጋርተውናል። በእንግሊዘኛ የቀረበው ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  21. 95

    የታላቁ አድዋ ድል በጥበባት አውድ ትርክቱ ምን መምሰል ይገባል?

    ''አድዋ ተራ ጦርነት አይደለም፤ ሰብዓዊነትን ገልጿል።  የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን የመላ ጥቁር መገለጫም ነው — በጥበባት አውድ ከተመለከትነው በሚገባው ከፍታ ልክ መተረክና መተንተን ይኖርበታል።'' ሲሉ የቪዢዋል አርቲስት፣ ሰዓሊ እና ቀራፂ በቀለ መኮንን (ፕ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ  የታላቁ አድዋ ድል በጥበባት አውድ ሊኖረው የሚገባን ትርክት መሠረት አድርገን ከቪዢዋል አርቲስት፣ ሰዓሊ እና ቀራፂ በቀለ መኮንን (ፕ/ር) ጋር ተወያይተናል። 🇮🇷 በክፍል ሁለት ደግሞ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ ኾሚኒ ግድያን ከዓለም አቀፍ ህግ ጥሰት አኳያ ከመኪ ኤልሞግራቢ፣  ሱዳናዊው የቀጠናዊ  ግንኙነቶች፣ የዲፕሎማሲና የዓለም ፖለቲካ ተንታኝ ጋር ተመልክተነዋል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  22. 94

    የሩሲያ 10 ኢምባሲዎችን በአፍሪካ ዳግም የመክፈት እቅዷ ለተጠናከረ ወዳጅነት

    ''የአፍሪካና የሩሲያ ግንኙነት ዘመን ተሻጋሪ ነው። ሩሲያ ካደጉ ደግሞ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ ሀገራት አንዷ ናት። ለምሳሌ ድምፅን በምድፅ የመሻር አቅሟን ማንሳት ይቻላል። ስለዚህ ከእንዲች ያለች ሀገር ጋር ወዳጅነት መፍጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው - ሩሲያ በቀጣይ ዓመታት ወደ አስር የሚጠጉ ኢምባሲዎችን በአፍሪካ ለመክፈት ማቀዷ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነትን የሚጨምር ነው'' ሲሉ የአፍሪካ ፖሊሲ ጥናት ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው መርሃ ግብራችን በክፍል አንድ ሩሲያ በአፍሪካ አህጉር አስር ኢምባሲዎችን ዳግም ለመክፈት የገለፀችበትን ዕቅዷን መሠረት አድርገን የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ እንዴት የዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ እንደሚያጎለብት እና ዕድሎችን እንዲፈጥሩ እንደሚያስላቸው ከፖሊሲ ጥናት ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። በክፍል ሁለት ደግሞ ስለመረጃ ሉዓላዊነት እና የሠው ሠራሽ አስተውህሎት አስተዳደር ከኮምፒውተር ሰርቨር ቁጥጥር አስተዳደር ባለሙያው ታደሰ ፀሃይነህ ጋር እንቃኛለን። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  23. 93

    የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በአዲስ አበባ

    ''የኔልሰን ማንዴላ ሙዚየም በአዲስ አበባ ሲከፈት ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች፣ አንደኛው እሳቸው በነበሩባቸው ጊዜያት ያረፉባቸው ክፍሎች፣ የተጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣ የሥልጠና ቦታና የወሰዷቸውን የስልጠና ዓይነቶች ያካተተ ነው — የአሁኑ ትውልድ እንደ አደዋ ካሉ የትናንት የአባቶቻችን ታሪክ ብዙ ተምሮ፣ ይህ መነሻ ሆኖ ለነገው ትውልድ ደግሞ ስንቅ ሆኖ መተላለፍ አለበት።'' ሲሉ ኮማንደር አሳቤ ባይሳ፣ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሎጀስቲክ መምሪያ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ኃላፊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በአዲስ አበባ ኮልፌ የቀድሞው የፈጥኖ ደራሽ ግቢ ውስጥ በዘመናዊ መልክ የታደሰውና ስለተገነባው የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም ኮማንደር አሳቤ ባይሳ፣ ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሎጀስቲክ መምሪያ በሎጀስቲክ መምሪያ የንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ኃላፊ ሀሳባቸውን ያጋሩናል። በክፍል ሁለት የግብርና ዘርፍ በገንዘብ መደገፍን መሠረት አድርገን ገበሬዎች ሥራቸውን ለማስፋፋትና ለማጎልበት ከፋይናንስ ተቋማት ብድር ለመውሰድ ስለሚጠየቁት የንብረት መያዣ መሥፈርቶች ጉዳይ በዘርፉ ከዩኒቨርሲቲ መምህርነት እስከ የዓለም የምግብና የግብርና ድርጅት (ፋኦ) ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋሟት የሠሩት ወርቅነህ ወዳጆ አበበ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ: 

  24. 92

    ሂፕ -ሆፕ (Hip hop) በሀገርኛ፡- የራስ ማንነትን በመገንባት ከውጭ ተፅዕኖ መላቀቅ

    ''የራሳችን ማንነትና መገለጫ ያለው ሙዚቃ ነው የሚያስፈልገን። ለዚህ ደግሞ አስገራሚ ሀገር በቀል እውቀት፣ ባህልና ጥበብ ያላቸው ሰዎች አሉ። በውጩ ዓለም እየተሳደቡ የራፕ ሙዚቃ የሚዘፍኑ አሉ፣ ስለዚህ እኛ እርሱን በፍፁም አናበረታታም — ጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ኢትዮ ጃዝን እንደፈጠረ ሁሉ፣ እኛም ኢትዮጵያዊ ቀለም ያለው የጥቁር ምት (Black Note) መፍጠር ነው ዓላማችን። አሁን ላይ ሙዚቃዎችን ስንሰራ ጥንታዊ መሠረቶች የሆኑት ቀርቶ፣ ፉከራና ሽለላን ለማካተት እንሞክራለን'' ሲሉ የሙዚቃ አቀናባሪዉ እና ፕሮዲውሰሩ ሁንአንተ ሙሉ (ሁኔ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንወያይበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የኢትዮጵያ የሂፕ- ሆፕ ሙዚቃ ጠንካራ ሀገራዊ መሠረት በመጣል እንዴት ከምዕራባዊያን ተፅዕኖ መላቀቅና የራሱን ዘውግ መፍጠር እንደሚችል የሙዚቃ አቀናባሪ እና ፕሮዲውሰርና ሁንአንተ ሙሉ(ሁኔ) ጋር ተወያይተናል። በክፍል 2 ደግሞ ድንበር ተሻጋሪ ትብብር እና ፈጣራን መሠረት በማድረግ በደቡባዊ  ዓለም ሀገራት ውስጥ የሠው ሠራሽ አስተውሎት ምርምርና ትግበራን በሚመለከት የቴክኖሎጂ እና ሠው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያ ሥርጉት አለሙ ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  25. 91

    ከሩሲያ ለአፍሪካ ወጣቶች የተመቻቸ የትምህርት ዕድል

    ''ከሩሲያ የነፃ የትምህረት ዕድል ማግኘቴ እንደ አፍሪካዊ ብሎም ኢትዮጵያዊ ሴት እጅግ የሚያኮራኝ ነው። ሁላችንም ለማግኘት የምንመኘው ዕድል ነው። ሩሲያ በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ተማሪዎችን እየመረጠች ዕድል መሥጠቷ፣ የትምህርት ሥርዓት ላይና አዕምሮ ላይ መሥራቷ በጣም ትልቅና ወሳኝ ነገር ነው።'' ስትል በሩሲያ የከፍተኛ ትምህረት ነፃ ዕድል ተጠቃሚዋ ምህረት በፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግራለች። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳሥሥበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ትምህርት በህብረተሰብ ዘንድ የሚያሳድረውን ማኅበራዊ ተፅዕኖ መሠረት አድርገን የቤተሰብ ደረጃን ለማሻሻል የማኅብረሰብ ልማትንም ለማጎልበት ሴቶችን ማስተማር ስለሚያበረክተው ቁልፍ ሚናን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለረጅም ዓመታት በማስተማር ያሳለፉት ሳምሶን ገብረ ህይወት ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት ሩሲያ ለአፍሪካዊያን ተማሪዎች ለረጅም አመታት እየፈጠረች ስላለችው እድል የሩሲያ የከፍተኛ ትምህርት ባለዕድል ወጣት ተማሪዎች መካከል ከምህረት በፍቃዱ፣ ናዖል መርጊያ እና ሳሙኤል ብርሃኑ ጋር እንወያያለን። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  26. 90

    የ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ አንድምታዎች

    ''አፍሪካ ቀጣይዋ የልማት፣ ሽግግር እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ መሻሻል የፍልሚያ ሥፍራ ናት። አህጉሪቱ ይህን ህልም ለማሳካት በምን ዓይነት መልኩ ቢሆን የተፈጥሮ ኃብቶች ያስፈልጓታል'' ሲሉ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄነሪ ኦሪየም ኦኬሎ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሦስት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔን መሠረት አድርገን ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ከኡጋንዳው ሄነሪ ኦሪየም ኦኬሎ፣ ከሪፐብሊክ ኦፍ ጊኒው ሞሪሳንዳ ኩያቴ እና ከቱኒዚያው ሞሃመድ አሊ ናፍቲ ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ማቀላጠፍ እንዲሁም የአፍሪካ ኅብረት 2063 አጀንዳን በሚመለከት የምጣኔ ሐብት ባለሙያውና የፓን አፍሪካ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ገና፣ የአፍሬግዚም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ፕሬዝዳንት ጂዮርጅ ኢሎምቢ እና አባስ ሚዬዘን ከጋና የንግድና ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጋር ሰፋ ያለ ዳሰሳ አድርገናል። የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ለባህልና ጥበባት ምን ዓይነት ሚና ይጫወት ስንል ከሩዋንዳዊው መምህርና በኢትዮጵያ የስዋህሊ ማኅበረሰብ አባሉ ፊትሶ ሀሩን ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  27. 89

    አማራጭ የክፍያ ስርዓት ፣ የፋይናንስ ሉዓላዊነት የእዳ ጫና እፎይታ ለአፍሪካ፡- አፍሪካ ህብረት ጉባኤ 2026

    ''አፍሪካ በፋይናንስ ስርዓቶችና ምህንድስና ረገድ በታሪክ ኢፍትሃዊነትን እየተጋፈጠች ነው። ከምዕራባዊያን ሀገራት ጋር ሲነፃፀሩ የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማቶች እየተበደሩ ያሉት በከፍተኛ መጠን ነው'' ሲሉ የሌሴቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኒ ምፖትጁዋና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። 48ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እ.ኤ.አ ከየካቲት 11 እስከ 12 በአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ተደርጓል።  የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ አእና ሌሎች ጉዳዪች ላይ እንደመወያየቱ ፣ በክፍል አንድ የሌሴቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሌጆኒ ምፖትጁዋና፣ ከኬንያ የካቢኔ ጽ/ቤት ዋይክሊፍ ሙሣሊያ ሙዳቫዲ ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአንጎላ አምባሳደር ፍራንሲስ ዦዜ ዳ ክሩዝ እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሃፊ ጂያን ክሪሶስቶም ንጋቢቴሲንዝ (ዶ/ር) ሀሳቦቻቸውን አጋርተውናል። በክፍል ሁለት የምሥራቅ አፍሪካ ምጣኔ ሀብትን መሠረት አድርገን ከኢኮኖሚስቱ ድንቅነህ ገብሬ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  28. 88

    የብሪክስ መሥፋፋት ሚዛናዊ ዓለምን እንዴት ይፈጥራል ?

    ''ስትራተጂካዊ ጠቀሜታ ያለው ብሪክስ አሁን ላይ ያቀፋቸው አባል ሀገራት ውስን ቢሆኑም ቁጥራቸው የበለጠ እየጨመረ ሲመጣ የዓለም ፖለቲካ ሚዛንን ለማስጠበቅ አቅሙን ያሳድጋል —ቡድኑ አማራጭ የፋይናንስ ልማትን ይፈጥራል። በዚህ ረገድ አዲሱ የልማት ባንክን ማንሳት ይቻላል'' ሲሉ ታምራት ተስፋዬ፣ የዓለም ወጣቶች ኮንፍረንስ አምባሳደር እንዲሁም በኢትዮጵያ የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና በሩሲያ የሩድን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ድግሪ የኢኮሎጂ ተማሪ ለስፑትኒክ አፍራካ ተናግረዋል።በክፍል አንድ የብሪክስ መሥፋፋት መሠረት አድርገን አዳዲስ አባላት ለዓለም ኃይል ሚዛን መጠበቅ ያላቸውን ሚና ከታምራት ተስፋዬ፣ የዓለም ወጣቶች ኮንፍረንስ አምባሳደር እንዲሁም በኢትዮጵያ የብሪክስ ተማሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና በሩሲያ የሩድን ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ድግሪ የኢኮሎጂ ተማሪ ጋር ቃኝተነዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ 22ኛው የአፍሪካ የፋይን ኮፊ ጉባዔንና ኤግዚቢሽንን መሠረት በማድረግየኢትዮጵያ ቡና ማንነትን በተመለከተ ከምንጩ እስከ ዓለም አቀፍ ሉዓላዊነት ድረስ ያለውን አሻራ የግል ዘርፍ ኢንቨስተሩ ፈለቀ ታደሰ እና ከጂማ ገበሬዎች ሁለገብ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ወንደወሰን በዛብህ ጋር ቆይታን አድርገናል። ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  29. 87

    የአፈር ብዝሃ ህይወት፡ ከእግራችን ሥር የሚገኘው ውዱ የተፈጥሮ ኃብት ከምግብ ዋስትና አኳያ ሲቃኝ

    ''አፈር ውዱ የተፈጥሮ ኃብት ነው። ህይወትም በምድራችን ላይ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው። በዚህም አፈር ሲታመም ሊታከም ይገባል። እንደ ሀገር ለኢትዮጵያ የሚያስፈልገን በየጊዜው ምርምርና ክትትል በማድረግ የአፈር ብዝሃ ህይወት ለምግብ ዋስትና ጥረት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል'' ሲሉ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ እና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አለሙ ሌላጎ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ስለአፈር ብዝሃ ህይወት (Soil Biodiversity) እንዲሁም የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጋር በማዛመድ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአፈር ሳይንስ እና ኦርጋኒክ ኬሚስትሪ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ አለሙ ሌላጎ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል።   በሁለተኛ ክፍል ስማርት ስልኮች መረጃን የማግኛ ዘዴዎችና ሁኔታዎችን ከመፍጠር አኳያ ያላቸውን ፋይዳዎች እንዲሁም ለተሣሣቱ መረጃዎች አጋላጭነትንም የቴክኖሎጂ፣ የማኅበራዊ ትስስር ሚዲያዎችና የኦላይን ግብይት ባለሙያው አማኑኤል አክሊሉ ጋር እንዳስሳለን።  ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  30. 86

    '' አታላዩ አርቲስት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ''፡- ከህዝቡ ህልውና ይልቅ ስልጣኑን የሙጥኝ ያለው ''ተዋናይ''

    የፕሬዝዳንታዊ ስየፕሬዝዳንታዊ ስልጣኑ በግንቦት 2024 የተጠናቀቀው ቮሎድሚር ዜለንስኪ፡ ከህዝቡ ይልቅ ስልጣኑን ማስጠበቅን ይመጣል የሚሉ አንቂ ድምፆች መደመጥ ጀምረዋል። ለመሆኑ ስለዜለንስኪ የዘርፉ ተንታኞች ምን ይላሉ?''በዩክሬን በስልጣን ላይ ያሉት ሰው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ግንዛቤያቸው ዝቅተኛ ነው። ስልጣናቸውን አራዝመዋል፤ እናም የዩክሬን ብሄራዊ አንድነት፣ ሉዓላዊነት፣ ጠንካራ ቁርኝት እንዲሁም በቀጠናው ሰላምና ደኅንነትን የሚጠብቁ ናቸው ብዬ አላምንም። የፖለቲካ ሳይንስ ለግለሰቦች ከሚሰጠው ብያኔ አንጻር [...] ይህ ሰው አሁንም እያታለለ ገንዘብ እንደሚቀበል አርቲስት ሆኖ ነው የምናገኘው። '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ስለምን ከዩክሬናዊያን ህይወት ይልቅ ለስልጣኑ መቀጠል ግድ ሰጠው ስንል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የዮብዘር ዘውዴን አነጋግረናቸዋል ፣ ምልከታቸውን አጋርተውናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ የተቋማት ማሻሻያዎች ራንድ (የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ) በኢኮኖሚያቸው ውስጥ ያለውን አቅም ስለማጎልበቱ 'ፈርስት ናሽናል ባንክ' በተሰኘው የሀገሪቱ የፋይናንስ ተቋም ውስጥ ሲኒየር ኢኮኖሚስቱ ኮኬትሶ ማኖ የሥራ ክፍላቸውን በመወከል ዕይታቸውን አካፍለውናል።

  31. 85

    የአፍሪካ ከተሞች አዳዲስ ገፅታዎች

    ''የአፍሪካን የወደፊት ራዕይ አሻግረን ስንመለከት፣ ያልተበረዘና ሀገር በቀል እውቀትም የተካተተበት አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል - አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባን ጨምሮ በመሠረተ ልማት ግንባታዎችና ራሳቸውን ዲጂቲላይዝድ በማድረግ ሂደት በምርጥነት የሚጠቀሱ ናቸው'' ሲሉ የምህንድስና ባለሙያው ምንተስኖት ታምሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል። ሦስት ጉዳዮችን በምንቃኝበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የአፍሪካ ከተሞች በመሠረተ ልማቶች ዲጂታላይዝ በማድረግ አዳዲስ ገፅታዎች እንዲይዙ የሚደረገውን ጥረት ከምህንድስና ባለሙያው ምንተስኖት ታምሩ ጋር ቃኝተነዋል። በክፍል ሁለት በኮንስትራክሽን ዘርፍ ህንድ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትብብርና እንደ ብሪክስ አባልነቷ ያላትን ሚናን በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩመር ሬይ ጋር ዳሰነዋል። በሦስተኛው ክፍል ደግሞ በአፍሪካ ለተሰጥዖዎች የሚሰጥ ዝቅተኛ ዋጋን በማሰወገድ ረገድ አህጉሪቷ እንዴት መትጋት እንዳለባት ናይጄሪያዊው የፊልም ባለሙያና የፓን አፍሪካ አቀንቃኝ ጆንቦስኮል ፖል አሞጎር ሀሳባቸውን አጋርተውናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  32. 84

    የአፍሪካ ፀሃይን እንደአማራጭ የኃይል ምንጭ የመጠቀም ጅምሮች

    ''ሞሮኮ በፀሃይ ኃይል ዘርፍ በአፍሪካ የምትመራ ሀገር ናት። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በንፅፅር ወደኃላ ካሉ ሀገራት መካከል ነው የምትመደበው። ይሁንና ከሶላር ፓነል ኃይል ለመጨመር አበረታች እቅዶች አሉ። ለምሳሌ የመተሃራ ፓነል ፕሮጀክት አለ፣ ወደ 500 ሜጋ ዋት እንዲያመነጩ የታቀዱ ከ8 በላይ ፕሮጀክቶች አሉ'' ሲሉ ንዋይመድህን አበራ (ዶ/ር)፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።  ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የኃይል አቅም መጠንን ለማስፋፋት የፀሃይ ኃይልን እንደ አማራጭ ምንጭ መጠቀምን ጉዳይ ከንዋይመድህን አበራ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊዚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጋር ቃኝተነዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ለአፍሪካ ውኃ መፍትሔዎችን ለመፍጠር የውኃ መሠረተ ልማትን በገንዘብ መደገፍ(ፋይናንስ) ማድረግ በተመለከተ በመሬትና ውኃ ኃብት ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ጠና አላምረው (ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  33. 83

    የሴቶች አስተዋፅዖ በኢትዮጽያ የከተማ ግብርና ዘርፍ

    ''ከሌማት ትሩፋት ጋር በተያያዘ ባለሃብቶች እንዲደግፉ በማድረግ ሴቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ምንም የሌላት እናት ቢያንስ 5 ዶሮዎች ከነቤታቸው ይሰጣታል፤ ከዛ በመነሳት በመቶዎችና ሺዎች ደረጃ የደረሱ አሉ '' ሲሉ በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናና አርሶ አደር ኮሚሽን ባለሙያ በለጠች ተሠማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንቃኝበት በዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ማዕቀፍ ስር በአፍሪካ አህጉር የቴክኖሎጂካል ኮሚኒኬሽን ምን ይመሥላል በሚለው ጉዳይ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ባለሙያው ልንገረው ጌቴ ጋር ተወያይተናል።  በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ሴቶች በከተማ ግብርና ዘርፍ ያላቸውን ጉልህ አስተዋፅዖና እንቅስቃሴን በዘርፉ ከተሠማሩ ወጣት ሴት ገበሬዎች መካከል የወይንሸት ፎሻ እና በአዲስ አበባ የከተማ ግብርናና አርሶ አደር ኮሚሽን ባለሙያ በለጠች ተሠማ ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  34. 82

    የውኃ ቴክኖሎጂ ትብብር ለጠንካራ ቀጠናዊ ልማት

    ''ሀገራት ውኃን በተመለከተ የጋራ ፕሮጀክቶች ሊኖራቸው ይገባል፤ አንድ ሀገር ለሚያለማው ፕሮጀክት ሌሎቹ ትብብር መፍጠር ይኖርባቸዋል። ፕሮጀክቶች ወንድማማችነትና ጠንካራ የትብብር መንፈስ ሊፈጥሩ ይገባል። በዚህ ረገድ ተቋማትን ማሻሻልና የመረጃ አያያዛቸውን ማጠናከር ያስፈልጋል —ውኃን መሠረት ያደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ከተመለከትን የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ - ሲሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጂነር ታምሩ ተሠማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።'' ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በቀጠናዊ አጋርነቶቾ የውኃ ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን መደገፍ ስለሚቻልባቸው ሁኔታዎች በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምሩ ተሠማ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። በክፍል ሁለት ደግሞ በትብብርና ጠንካራ አጋርነት መንገድ የአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለመፍጠር አህጉሪቱ ያሏትን አቅሞች መጠቀምን በተመለከተ ከተማ ቱፋ፣ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ የፕላንና የመንግስት ኢንቨስትመንት ዴስክ ኃላፊ ሙያዊ ሀሳቦችን አጋርተውልናል።  ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

  35. 81

    የአሜሪካ በመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ ተሳትፎ ትናንትና ዛሬ ሲቃኝ

    ''የአሜሪካ ዓላማ ቀጠናው እንዳይረጋጋ በማድረግ ፍላጎታቸውን ማሳካት ነው። ኢራቅን ለአብነት ብንወስድ፣ አውዳሚ የጦር መሣሪያ አለ በሚል ሽፋን ጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት ሀገርን ያለምንም ማስረጃ በሴራ ንድፈ ሀሳብ አውድመዋል። በዚህም በራሷ የሚደገፉ የሽብር ኃይላትም ተፈልፍለዋል'' ሲሉ በአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው ምሥራቅ ጂዮፖለቲካ ተንታኙ መሃመድ ንጉስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ አሜሪካ በተለያዪ ጊዜያት በመካከለኛው ምሥራቅ ባደረጋቻቸው ወታደራዊ ጣልቃ ገብነቶች ምክንያት የተፈጠሩ ቀውሶች በተመለከተ  ከ ጂዮግራፈር፣ ካርቶግራፈር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው ምሥራቅ ጂዮፖለቲካ ተንታኙ መሃመድ ንጉስ ጋር ተወያይተናል። በክፍል ሁለት ደግሞ በአቶሚክ ስኬል ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ ቋት (hub) የማድረግ እንቅስቃሴን በኢትዮጵያ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የናኖ ቴክኖሎጂ እና ተያያዥ ዘርፎች መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  36. 80

    የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ ከአፍሪካ ንግድና ምጣኔ ሐብት አኳያ ሲቃኝ

    ''ብሪክስ እንደ አላማ አድርጎ ከተነሳው መካከል የፋይናንስ፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ንፁህ የአየር ከባቢ መፍጠርና የዲጂታል ሥራዎች ማስፋፋት ይገኙበታል። እኛ አፍሪካዊያን ነገሮችን በብስለት መምራትና መጠቀም ከቻልን ከብሪክስ የልማት ባንክ ብዙ መጠቀም እንችላለን። የልማት ባንኩ ከቀደመው የምዕራባዊያን የኢኮኖሚ ጫናም እንድወጣም የሚያስችል ነው '' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶ/ር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ በንግድ እና ኢኮኖሚ ላይ ያለው በጎ ተፅዕኖ በተመለከተ ከአሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ የምጣኔ ሀብትና ተያያዥ ጉዳዮች ባለሙያ እንዲሁም በሩሲያ፣ ቅዱስ ፒተርስበርግ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል እጩ ዶክተር ጋር ተወያይተናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ጉዳይን በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድቤት ፊት ስለማቅረብ ከያዛቸው ውድነህ የኢንቫይሮመንታል ጂዮግራፈር፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና አዳፕቲሽን ባለሙያ፣ መምህርና ተመራማሪ ጋር ቃኝተነዋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  37. 79

    የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ለተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መሥፋፋት

    ''የንፁህ ኢነርጂ ልማት ጉዳዮች ያለ ግል ዘርፉ ተሳትፎ እውን ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት እጅግ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ — መንግስታት፣ የግል ዘርፎች እንደ ቴክኖሎጂና ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያውሉ ማነቃቃት ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ ቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮች ለውይይት በሚቀርቡበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስሰ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ የመንግስትና የግል አጋርነት የተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መስፋፋት እንዲፈጠር የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ በተመለከተ ከቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ጋር ቃኝተነዋል። የህግ መሠረት የሌላቸው የውጭ ጣልቃብነቶችን ለማስወገድ አፍሪካ የተቀናጀ ዲፕሎማሲን እንደ መሣሪያ መጠቀም የምትችልበት አግባብን በሚመለከት ኡጋንዳዊው የዓለም አቀፍ ቢዝነስ አክስፐርቱ ዙብሪ ሉጂያና ምልከታቸውን አጋርተውናል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ

  38. 78

    የወንዝ ዳርቻ ልማት አዲሱ የከተማ ገፅታ በኢትዮጵያ

    ''የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ከተማን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። በሁሉም ከተሞች ውስጥ ቢበረታታ መልካም ነው እላለሁ -  ሲሉ ሺቲ ጋተው(ዶ/ር) ፣ የብዝሃ ህይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።'' ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የግብርና እሴት ሰንሰለት፣ ክምችት እና የድህረ ክምችት ብክነት ቅነሳን በተመለከተ ከእንግዳችን አዲሱ ፍቃዱ (ዶ/ር)፣ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር ጋር ሠፋ ባለ መልኩ እንዳስሳለን።   በሁለተኛው ክፍል የከተሞች ወንዝ ዳርቻ ልማት እና የከተሜነት መነቃቃትን መሠረት ያደረገ ውይይት ከዶ/ር ሺቲ ጋተው፣ የብዝሃ ህይወት ምርምርና ጥበቃ ማዕከል ዳይሬክተር ጋር እናከናወናለን።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  39. 77

    የማዕድን ሀብቶችን በአፍሪካ:- የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት የማድረግ እንቅስቃሴ

    ''ወርቅ በአሁኑ ሰዓት ለምጣኔ ሀብት ዕድገት ቀዳሚ ቦታ የሚሠጠው የማዕድን ዓይነት — አንድ ሀገር ብቻዋን ማደግ አትችልም። ቢያንስ የቴክኖሎጂ ሽግግር መውሰድ ይኖርባታል። በዚህም ከአደጉ ሀገራት ጋር ትብብር መፍጠር የሚጠበቅ ነው። በዚህ ረገድ ከራሺያ ጋር ያለን ግንኙነት ለዘመናት የዘለቀ በመሆኑ በጥሩ መልኩ ነው የሚታየኝ '' ሲሉ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የጂኦሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ አየለ (ዶ/ር) ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የማዕድን ኃብት ዘርፍ በአፍሪካ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን ለመፍጠርና ለማፋጠን ስለሚያበረክተው አስተዋጽዖ በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የጂኦሳይንስ ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ አየለ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። ጤናማ ብዝሃ ህይወትን ለመፍጠር አካባቢን እንደ ጠንካራ መሠረት ማድረግ በሚመለከት ደግሞ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፋኖሴ መኮንን ጋር በክፍል ሁለት እንወያያለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  40. 76

    ታላላቅ ሩሲያዊያን ጸሃፊዎች ሲታወሱ፡- ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ

    ''የሩሲያዊያን ስነፅሁፎች ጭፍን ጥላቻን አያንፀባርቁም፤ ይልቁን የማኅበረሰቡን ባህል፣ ወግና ታሪክ የሚያንፀባርቁ ናቸው - ከታላላቅ ፀሃፊዎች መካከል የአንቶን ቼክሆቭ ሥራዎች በዓለም ላይ ምርጥ 50 ተውኔቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። በዚህም በሥራዎቹ በትልቅ ደረጃ የሚገለፅ ነው - ሲል'' ከቼክሆቭ ሥራዎች ውስጥ አራቱን ወደ አማርኛ ቋንቋ የተረጎመው ተዋናይ ሳምሶን ብሬ ለግሃር ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድቷል። በመጀመሪያው የፕሮግራሙ ክፍል የታላላቅ ራሺያውያን ፀሃፊዎችን ዘመን ተሻጋሪ አሻራን መሠረት በማድረግ ከአሌክሳንደር ፑሽኪን እስከ አንቶን ቼክሆቭ ያሉ ታላላቅ የስነ ፅሁፍ ሰብዕናዎችን ከተርጓሚ፣ ተዋናይና በጥብቅና ሙያ ላይ ከሚገኘው ሳምሶን ብሬ ለግሃር ጋር እንዳስሳለን።  በሁለተኛው ክፍል ደግሞ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲሁም በደቡብ - ደቡብ ትብብር ውስጥ ያላትን ሚና  በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪው አበራ ኤልያስ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  41. 75

    የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከየት ወዴት?

    የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታዎች አእየተደረጉ ነው35ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር በሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ነው። አጋጣሚውን ተጠቅመን ስለኢትዮጵያ እግርኳስ መጠየቅ ወደድናል፡፡ ''የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጎል የማይገባበት ሊግ ነበር የሆነ ጊዜ፤ ስታዲየም አካባቢ በነፃነት ተከራይህ መኖር ትችል ነበር ጎል ስለማይገባ፣ ጩኸት ስለማይኖረው። የዚህን ያህል ነፃነት ነበረው '' ሲል ኢትዮጵያዊው የእግር ኳስ ጋዜጠኛ አያናው ወልደ ሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡ በዚህኛው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው የአፍሪካ አህጉር እግር ኳስ ዕድገትና እንቅስቃሴን መሠረት አድርጎ የአህጉሪቱ የእግር ኳስ ዕድገት፣ ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ የውጭ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች በኢትዮጵያ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ከፓን አፍሪካ ፉትቦል ፀሐፊው ኦምና ታደለ፣ የእግር ኳስ ጋዜጠኛው አያናው ወልደሚካኤል እና የእግር ኳስ ተንታኙ ልዑል ታደሰ ጋር በጥልቀት ተወያይቷል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  42. 74

    ትምህርት፣ ክህሎት እና ፈጠራ፡- ለኢኮኖሚ ዕድገት ምን ሚና አላቸው ?

    '' በአፍሪካ ጠንካራ ምጣኔ ሀብት መፍጠር ያስፈልጋል። ለዚህም ኢንዱስትሪውን ማጎልበት፣ ፈጠራዎችን ማስፋፋት በተጨማሪም በእውቀትና ክህሎት መደገፍ ተገቢ ነው - ለአንድ አካል የሚተው ባለመሆኑ የግል ዘርፉንም ያካተተ ትብብርና አጋርነት መፈጠር አለበት። ፖሊሲዎችን መከለስና በሁሉም ዘርፎች ውስጥ ማሻሻያዎችን ማፋጠን ያስፈልጋል'' ሲሉ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በአፍሪካ ጠንካራ የምጣኔ ሐብት ዕድገትን ለመፍጠር የሠው ኃይልን እንደ መሠረት መጠቀምን በተመለከተ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲስ መምህሩ ፍራፊስ ሀይሉ (ዶ/ር) ጋር ቃኝተነዋል። የምሥራቅ አፍሪካ ቀንድ የወደፊት ጂዮፖለቲካ ሁኔታ እና ቀጠናዊ ትስስርን በሚመለከት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ህግ መምህሩ አበራ ለሚ ጋር ያደረግነው ቆይታ ደግሞ በክፍል ሁለት እንዳስሰዋለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  43. 73

    ቬኔዙዌላ፡- የፖለቲካ ጣልቃገብነት እና የሉዓላዊነት ጥሰት ማሳያ

    ''ቬኔዙዌላ አሁን ላይ የውጭ ጣልቃገብነት ተጠቂ ሀገር ናት። [...] በውስጥ አንድነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ፍትህ መጠየቅ ይኖርባታል - የተፈጠረው ነገር ከቬንዙዌላ ባሻገር ለሌሎች ሉዓላዊ ሀገራት በሙሉ የማንቂያ ደውል ነው '' ሲሉ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄብሶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አጋርተዋል። ሁለት ዐበይት ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ የፖለቲካ ጣልቃገብነትን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን በተመለከተ ሰሞነኛው የቬኔዝዌላን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ አበራ ሄብሶ ጋር ተወያይተናል።በሁለተኛው ክፍል ደግሞ አፍሪካዊያን ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት ከሚልኩት ገንዘብ ባሻገር ያላቸው ሚናን በሚመለከት ከናይጄሪያ ሌበር ኮንግረስ ኮምራድ ኢቼ አሱዚ ምልከታቸውን አጋርተውናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  44. 72

    ብሔራዊ የልማት ዕቅድ ከዓለም አቀፍ የባንክ አሰራሮች አንጻር ዕድሎችና ተግዳሮቶች

    ''ሀገር ሊያድግና ሊለወጥ የሚችለው በውስጥ አቅም ነው፤ በብድርና ድጋፍ ብቻ የተለወጠ ሀገር የለም። ስለዚህ የውስጥ አቅምን በሚገባ አውጥቶ መጠቀም ያስፈልጋል '' ሲሉ በባንክ ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግና ብራንዲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አሰቻለሁ ታምሩ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በብሔራዊ ልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ከዓለም አቀፍ የባንኪንግ ልምዶች እንዴት ማዛመድ ይቻላል የሚለውን ጉዳይ በባንኪንግ ዘርፍ በተለይም በማርኬቲንግና ብራንዲንግ የረጅም ዓመታት ልምድ ያካበቱት አሰቻለሁ ታምሩ ጋር ቃኝተናቸዋል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የአዝዕርቶችን አቅም በማሳደግ፣ ምርታማነትን በመጨመር እና የስርዓተ ምግብ ጥራቶችን ማሳደግ በተመለከተ ከአግሮኖሚስቱና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የደጋ ፍራፍሬና አትክልት ምርምር ማዕከል ዳይሬከተር ዘነበ መኮንን(ዶ/ር) ጋር ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  45. 71

    ባለሁለት ስለቱ ማኅበራዊ ሚዲያ፡ መልካም ዕድሎቹና አሉታዊ ተፅዕኖዎቹ

    ''ቴክኖሎጂ ወደፊት እያደገ ሲመጣ የራሱን መልካም ገፅታዎችን ይፈጥራል። ለምሳሌ ሰዎች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ባሉበት ቦታ የመማር ፍጥነታቸውን ጨምሮላቸዋል። በአንፃሩ ወጣቶች የበሰለ የማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ክህሎት ባለማዳበራቸው ከፍተኛ ቀውስ ሲፈጥሩ ይስተዋላሉ'' ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀምና አመራር የረጅም ዓመታት ልምድ ካላቸው አቶ አማኑኤል አክሊሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በሁለት መልክ የሚታየው የማኅበራዊ ሚዲያን በተመለከተ መልካም ዕድሎቹንና አሉታዊ ተፅዕኖዎቹን ከሌሎች ተያያዥ ዝርዝር ሀሳቦች ጋር በማጣመር በማኅበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀምና አመራር የረጅም ዓመታት ልምድ ካላቸው አቶ አማኑኤል አክሊሉ ጋር እንወያያለን። በክፍል ሁለት ደግሞ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት፣ የርቀት ሥራዎች እና የዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪነት ጉዳይን ከሠው ሠራሽ አስተውህሎት ባለሙያው ልንገረው ጌቴ ጋር ቃኝተነዋል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ :

  46. 70

    የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ ክፍተት በቴክኖሎጂ፣ ጥናትና ምርምር የመቅረፍ ተስፋ

    ''እያንዳንዱ የጤና ቴክኖሎጂ የራሱ ሳይንሳዊ የውጤታማነት መለኪያ አለው። ለአብነትም የመመርመሪያ መሣሪያዎችን መውሰድ እንችላለን —ሀገራችን ራሷን በክትባት አቅም ማብቃት ይኖርባታል፣ እኛም እንደተመራማሪ ክትባቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት አለብን '' ሲሉ በዘርፉ የረጅም ዓመታት ተመራማሪው ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ በምርምር፣ አዲስ ሀሳብ በማፍለቅ እንዲሁም ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎችን በመተግበር በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና ተያያዥ ሀገር አቀፍ ችግሮችን መቅረፍ ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች በዘርፉ የረጅም ዓመታት ተመራማሪው ዶ/ር ሞላልኝ ቢተው ጋር ዳሰናል። በክፍል ሁለት ደግሞ ታህሳስ 1፣ 2025 በመላው ዓለም የተከበረውን የኤች አይ ቪ ቀንን መነሻ በማድረግ የጤና አጠባበቅ ስርዓትና ተደራሽነትን በአቤት ሆስፒታል የድንገተኛና የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስቱ ዶ/ር ፀጋዬ ገብረ አናንያ ጋር ቃኝተነዋል።

  47. 69

    ፕሬዝዳንት ትራምፕ ደቡብ አፍሪካን በቀጣዩ የቡድን 20 ጉባዔ ለሞን አንጋብዝም አሉ? ፖለቲካ መር ወይስ የህግ መሠረት ያለው ጉዳይ?

    ''ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀጣይ በሀገራቸው በሚካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ጉባዔ ደቡብ አፍሪካን እንደማይጋብዙ መናገራቸው ወደፊት የቡድኑን አቃፊነትና ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው - የፕሬዝዳንቱ ንግግርን ተከትሎ በርካታ ሀገራት አጋርነታቸውን ለደቡብ አፍሪካ አሳይተዋል '' ሲሉ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው ፕሮግራሙ በክፍል አንድ፣ በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ የተደረገውን የቡድን 20 ሀገራት ጉባዔን ተከትሎ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀጣዩ ጉባዔ ደቡብ አፍሪካን እንደማይጋብዙ መናገራቸውን በተመለከተ ከዓለም አቀፍ ህግና የሞራል መመዘኛዎች አኳያ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህሩ ጃራ ሳሙኤል ጋር ቆይታን አድርገናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በኢትዮጵያ እየጨመረ የመጣው የመንገድ ትሪፊክ አደጋ በተመለከተ በአውቶሞቲቭ ሙያ የረጅም ዓመት ልምድ ያላቸው ፋሲል አስራት ጋር ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  48. 68

    የኢትዮጵያ 2029 የአፍሪካ ዋንጫ ማሰናዳት ጥያቄ፦ ከእግርኳስ የሚሻገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትሩፋቶቹ

    ''ሀገራችን እንደ አፍሪካ ዋንጫ ያሉ ትልልቅ ውድድሮችን ማዘጋጀት ከቻለች የሚያስገኙላት በረከቶች በርካታ ናቸው - ኢትዮጵያ አንድ ወቅት እንደ ክቡር ይድነቃቸው ተሰማ ዓይነት ህይወቱን ለእግር ኳስ የሠጠ ታላቅ የአግር ኳስ መሪ የነበራት ሀገር ናት'' ሲል የስፖርት ጋዜጠኛው ዮናስ አዘዘ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሁለት ጉዳዮችን በምንዳስስበት ፕሮግራማችን በክፍል አንድ ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችው ይፋዊ ጥያቄ በእግር ኳስ አውድ ከሚገለፁ ጥቅሞች ባሻገር የሚያስገኝላትን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያውና ሌሎች ተያያዥ ጥቅሞችን ከስፖርት ጋዜጠኛው ዮናስ አዘዘ ጋር ቃኝተነዋል። በሉዋንዳ አንጎላ የተካሄደውን 4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታዎችን በተመለከተ በሥፍራው ተገኝቶ ከተከታተለው ሌላኛው የስፖርት ጋዜጠኛ ፉአድ ኢንድሪስ ጋር በክፍል ሁለት ተወያይተናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

  49. 67

    የናኖ ቴክኖሎጂ ትሩፋት፡ ለንጹህ የኃይል ምንጭና ቀጠናዊ ትስስር

    ''የፀሃይ ብርሃንን ተጠቅም የኃይል ምንጭን ለመፍጠር ናኖ ቴክኖሎጂ ጉልህ አስተዋፅዖ አለው። በተጨማሪም የካርበን ልቀትን ለመቆጣጠር የናኖ ቁሶች ጠቃሚ እንደመሆናቸው በሀገራችን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በሚደረግ ትብብር በፕሮጀክት ጀረጃ እየተሰራበት ነው '' ሲሉ በባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ተቋም የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሶቨርኒቲ ሶርስስ በዛሬው መርሃ ግብሩ በክፍል አንድ የነገን ዋስትና ለማረጋገጥ፣ ቀጠናዊ ትብብርና ለማሳደግ የጋራ ችግሮችን ለመቅረፍ ንፁህ ኢነርጂ እና አካባቢን ከብክለት ለማንጻት ናኖ ቴክኖሎጂ ስላለው ፋይዳ የናኖ ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሪ የሥራ ኃላፊ ወንድማገኝ ማሞን (ዶ/ር) በእንግድነት ጋብዘናቸዋል። የምርምር ግኝቶችን ወደ ገበያ በማውጣት የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ትግበራዎችን ማረጋገጥ እንዲሁም ከብሪክስ አባላት ጋር ትብብርን መፍጠርን በተመለከተ ከቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን ኮመርሻላይዜሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኡስማን ኡመርን ጋር የተደረገው ቆይታም ሌላኛው ጉዳያችን ነው።  ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

  50. 66

    አፍሪካ፡ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ውስጥ እያደገ ያለ አህጉር

    የአፍሪካ ሩሲያ ግንኙነት የእኩልነት መርህን መሰረት ያደርገ ነው '' ሉዓላዊ ትብብር የአፍሪካን ሉዓላዊነት እንደሚያመጣ ማየት ትችላላችሁ። ይህ የጌታና አሽከር ወይም የፈረስና ጋላቢ ግንኙነት አይደለም። የጋራ እሴቶች ባላቸው ህዝቦች መካከል ያለ ግንኙነት ነው። እነዚህ የጋራ እሴቶች ሉዓላዊ አፍሪካን ለመፍጠር እንዲሁም ሉዓላዊ የሩሲያ ፌዴሬሽንን ለማበረታታት የምንጠቀምባቸው ናቸው'' ሲሉ የዙምባቡዌ የውጭ ግንኙነትና ዓለምአቀፍ ንግድ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙሩዊራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።ሶስት አንኳር ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በክፍል አንድ አፍሪካ በባለ ብዙ ወገን ዓለም ያላት ሚናን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እ.ኤ.አ ታህሳስ 19፣ 2025 ባደረጉት የዓመቱ ማጠቃለያ ንግግር ስለአፍሪካ ካነሷቸው ሀሳቦች ጋር በማጣመር በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ጋር እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ ከታህሳስ 19 - 20፣ 2025 በካይሮ፣ ግብፅ የተደረገውን 2ኛው የሩሲያ - አፍሪካ የሚኒስትሮች ጉባዔን የደቡብ ሱዳን የዉጭ ግንኙነትና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር መንዴይ ሲማያ ኩምባ እና የዛምቢያ የዉጭ ግንኙነትና ዓለማአቀፍ ትብብር ሚኒስትር ሙላምቦ ሄምቤን አነጋግረናቸዋል። ፀረ - ቅኝ ግዛትና ተያያዥ ጉዳዮችን ከዓለም የፖለቲካና ፍልስፍና ተንታኙ ጋብርዔል አሱኮ ጋር በሶስተኛው ክፍል ቃኝተነዋል። ''የአፍሪካ ሀገራት በምጣኔ ሐብት ዕድገት፣ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች መሻሻል እያሳዩ ነው። ሉዓላዊነት አስፈላጊ ነገር ነው — እንደ ራሲያ እና ቻይና ያሉ ሀገራት ብሪክስም እየጎለበተ መምጣታቱ ባለአንድ ወገኑን ዓለም የመታደስ ግዴታ ውስጥ እያስገባው ነው ''ሲሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናቶች ረዳት ፕሮፌሰሩ ሙከረም ሚፍታህ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን  ያዳምጡ:

Type above to search every episode's transcript for a word or phrase. Matches are scoped to this podcast.

Searching…

We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.

No matches for "" in this podcast's transcripts.

Showing of matches

No topics indexed yet for this podcast.

Loading reviews...

ABOUT THIS SHOW

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

HOSTED BY

ዐቢይ ሀብታሙ

CATEGORIES

Frequently Asked Questions

How many episodes does Sovereignty Sources have?

Sovereignty Sources currently has 50 episodes available on PodParley. New episodes are automatically indexed when they're published to the podcast feed.

What is Sovereignty Sources about?

ዓለም በሉላዊነት ምክንያት ስትተሳሰር ፤ ፕሮግራሙም አፍሪካ ባላት እምቅ የተፈጥሮ ኃብት፣ በማደግ ላይ ባለው የሕዝብ ቁጥሯ ፣ በወጣት ኃይሏ እና በአህጉሪቱ ባሉ አዳዲስ ግኝቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች  ያላትን የመወዳደር አቅምና ጥቅም በሰፊው ይዳስሳል፡፡ እንኳን ወደ 'ሶቨርኒቲ ሶርስ' ፕሮግራም በደህና መጡ፣

How often does Sovereignty Sources release new episodes?

Sovereignty Sources has 50 episodes. Check the episode list to see recent publication dates and frequency.

Where can I listen to Sovereignty Sources?

You can listen to Sovereignty Sources on PodParley by clicking any episode. We provide an embedded audio player for direct listening, and you can also subscribe via your preferred podcast app using the RSS feed.

Who hosts Sovereignty Sources?

Sovereignty Sources is created and hosted by ዐቢይ ሀብታሙ.
URL copied to clipboard!