EPISODE · Jan 22, 2026 · 1H
አፍሪካ በወደቦች እና በኃይል መካከል፦ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ያለ ልማት እና ዲፕሎማሲ
from The Rising South
“ሩሲያ እ.ኤ.አ. እስከ 2027 ድረስ በአፍሪካ ውስጥ የኤምባሲዎቿን ቁጥር ወደ 49 አካባቢ ለማድረስ እየሠራች ነው። የሩሲያ ተዓማኒነትን በተመለከተ ከቅኝ ግዛት ታሪክ ነፃ መሆኗ ትልቁ ዲፕሎማሲያዊ ሀብት ታሪኳ ነው። እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ ወይም ቤልጂየም ሳይሆን፣ የአፍሪካን ግዛቶች በቅኝ ግዛት አልገዙም። [...]ይህ ታሪክ ወደ “የእኩልነት አጋርነት” ትረካ የተቀየረ መሆኑ ነው፤ ይህም በተፈጥሮ ሀብታቸው፣ በወደፊት እጣ ፈንታቸው፣ በታሪካቸውና በውርሳቸው ላይ ሙሉ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለሚጥሩ አገራት ትልቅ ትርጉም የሚሰጥ ነው።” ሲሉ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ መሀመድ ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ባለ ሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የጂቡቲን ኢኮኖሚያዊ እይታ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ እና ኢኮኖሚስት ከሆኑት ከ ቆስጠንጢኖስ በርሄተስፋ(ዶ/ር) ጋር የተወያየን ሲሆን፤ በተጨማሪም፣ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዓመታዊ ጋዜጣዊ መግለጫን መሠረት በማድረግ፣ የአፍሪካን ሁኔታ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም አቀፋዊ ምልከታ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ከሆኑት መሐመድ ኢብራሂም ጋር ዳስሰነዋል፡፡በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
NOW PLAYING
አፍሪካ በወደቦች እና በኃይል መካከል፦ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም ውስጥ ያለ ልማት እና ዲፕሎማሲ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.