PODCAST · society
The Rising South
by ወሰንሰገድ አሰፋ
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።
-
112
የአፍሪካ ሉዓላዊነት በፖሊሲ ነጻነት እና በጤናው ዘርፍ
"አፍሪካውያን መሪዎች በመጨረሻ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ለማን ነው? ለገዛ ዜጎቻቸው ወይስ ለውጭ አጋሮቻቸው? መንግሥታት ለውጭ የፖሊሲ መመሪያዎች፣ ለገንዘብ ድጋፎች ወይም ለአለም አቀፍ ተቀባይነት ቅድሚያ ሲሰጡ፤ የገዛ ዜጎቻቸውን የዕለት ተዕለት ችግሮች የመፍታት ኃላፊነታቸውን የማዳከም አደጋ ውስጥ ይወድቃሉ።" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የለሴጎ ፋውንዴሽን (Lesego Foundation) መሥራች የሆኑት ሱቡሲሶ ማሻባኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ፦ በውጭ ዕርዳታና ድጋፍ ላይ ጥገኛ መሆን በአገር በቀል ተጠያቂነት ላይ የሚያስከትለው ዋጋ ምንድን ነው? የውጭ ጥገኝነት በአስተዳደር፣ በኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ በኢንዱስትሪ ልማት እና በሥራ አጥነት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ከሱቡሲሶ ማሻባኔ ጋር በሰፊው እንወያያለን።በክፍል ሁለት፦ የአፍሪካን የሕክምና ትምህርት እና የጤና ሥርዓትን ከአህጉሪቱ ነባራዊ እውነታዎች ጋር እንዴት ማጣጣም ይቻላል? ስንል በዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ቢሮ የጤና ሥርዓት እና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶ/ር አደልሄድ ኦንያንጎ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
111
የአፍሪካን የእንስሳት ሀብት ማዘመን፡- ከምርታማነት እስከ አህጉራዊ እሴት ሰንሰለት
"እኛ የምንፈልገው የተቀናጀ አህጉራዊ የእንስሳት ሀብት እሴት ሰንሰለትን መፍጠር ነው። ከአምራቹ ጀምሮ እስከ እሴት መጨመር እና ማቀነባበር ድረስ ያሉትን ሂደቶች በሙሉ በመደገፍ፤ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የስጋ እና የወተት ምርቶችን በራሳችን አህጉር ለማምረት የግል ባለሀብቱን ማሳተፍ ይኖርብናል።" ሲሉ በአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ እንስሳት ሀብት ቢሮ (AU-IBAR) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሁያም ሳሊህ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ በቀዳሚነት ከአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ እንስሳት ሀብት ቢሮ (AU-IBAR) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሁያም ሳሊህ ጋር የአፍሪካን የአርብቶ-አደር ማህበረሰብ ኢኮኖሚ ከዕለት-ጉርስ ኑሮ ወደ አህጉራዊ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ሞተርነት ስለማሸጋገር ያደረገነውን ውይይት እናቀርባለን።በሁለተኛው ክፍል ደግሞ በሐምሌ ወር 2026 እ.ኤ.አ የተካሄደው 23ኛው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር አመታዊ ጉባኤ መነሻ አድርገን ከማህበሩ ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና፣ ከከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎቹ አሰፋ አድማሴ (ዶ/ር) እና አቡሌ መሀሪ (ዶ/ር) ጋር፤ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ ዓለም አቀፍ ተፅዕኖዎችን የመቋቋም አቅም፣ የብሪክስ (BRICS) እና የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ዕድሎች በጥልቀት እንወያያለን።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ
-
110
ምርምር ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፦ ያልተነካው እምቅ አቅም
"ምርምርን በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ውስን ሀብት ባለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለልማት 'የአቅም ማባዣ' (force multiplier) አድርጌ እገልጸዋለሁ። ሀብት ውስን በሚሆንበት ጊዜ ዋናው ፈተና የሀብቱ እጥረት ሳይሆን ያንን ያለውን ሀብት ምን ያህል በብቃትና በአግባቡ እየተጠቀምንበት ነው የሚለው ነው። ምርምር እጅግ ወሳኝ የሚሆነውም እዚህ ቦታ ላይ ነው።" ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፋከልቲ ከፍተኛ የምርምር ባለሙያ ሰለሞን አስማረ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም "ዩኒቨርሲቲዎች የሚያሳትሟቸው የምርምር ውጤቶች ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡ ይህ መጣጣም ሲኖር የህብረተሰቡን ችግር በመቅረፍ ረገድ እንዲሁም ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ በሁለቱም በኩል መዋቅራዊ እና አሰራራዊ ለውጥ ያስፈልጋል።" ሲሉ አክለዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን በከፍተኛ የምርምር ባለሙያው ሰለሞን አስማረ አማካኝነት ምርምር ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት ያለውን ፋይዳ፣ በዩኒቨርሲቲዎችና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር የሚቻልባቸውን መንገዶች፣ እንዲሁም የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ሚና እንመለከታለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ፡
-
109
ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሀብት ፈጣሪነት፦ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓትና የዕውቀት ነጻነት
"የትምህርት ሥርዓታችን አሁንም ድረስ የራሳቸውን ሀብት የሚፈጥሩ ሉዓላዊ ዜጎችን ከመቅረጽ ይልቅ በሌሎች ላይ ጥገኞች የሆኑ የሥራ ፈላጊዎችን ስብስብ እያመረተ ይገኛል።... እውነተኛ ነጻነት የሚጀምረው የአፍሪካን የአገሬው ተወላጅ ዕውቀቶች እና ቋንቋዎች ለኢኮኖሚና ለዕውቀት ነጻነት ማዋል ስንችል ነው፡፡" ሲሉ የሌሴጎ ፋውንዴሽን መሥራች ሲቡሲሶ ማሻባኔ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ የአፍሪካ የትምህርት ሥርዓት ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ተላቆ አዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎችን ለማፍራት መከተል ስላለበት የዕውቀት ምንጭ ከደቡብ አፍሪካው የለሴጎ ፋውንዴሽን መሥራች ከሲቡሲሶ ማሻባኔ ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ውይይት ይዘን ቀርበናል። ክፍል ሁለት ደሞ አዲሱ ብሔራዊ የቱሪዝም ፖሊሲና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ለመሳብ ስላለው ዕቅድ፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ ከሰኔ 20 እስከ ሰኔ 24 ፣ 2026 በኢትዮጵያ የቱሪስት አስጎብኝዎች “ኢትዮጵያ በቱሪስት አስጎብኝዎች ዓይን” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ሙዚየም ለዕይታ የቀረበውን 4ኛው የፎቶግራፍ ዐውደ ርዕይን እንዳስሳለን። ዐዉደ ርዕዩ ቱሪዝምን ለማነቃቃት ስላለው ሚና የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ስለሺ ግርማ እና የኢትዮጵያ አስጎብኚዎች ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሄኖክ ጸጋዬ ማብራሪያ ይሰጡናል።
-
108
ከአፍሪካ ሉዓላዊነት እስከ ባለብዙ-ዋልታ ዓለም
"ይህ (በሀገር ውስጥ ምንዛሬ የመገበያየት ሞዴል) አገሮችን በፋይናንስ ማዕቀብ ከሚያስረው ስዊፍት [Swift] የክፍያ ስርዓት ለመውጣት ጥሩና ውጤታማ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ሞዴል የደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ሀብት በምዕራባውያን ኃይሎች እጅ እንዲያዝ እና እንዲወረስ ተጋላጭ ከማድረግ ይልቅ፣ እዚሁ በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ውስጥ ተከማችቶ ለሕዝብ ጥቅም እንዲውል መንገድ ይከፍታል።" ሲሉ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እ.ኤ.አ በግንቦት 19 እና 20 ፣ 2026 ወር አጋማሽ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት ተከትሎ ሞስኮ እና ቤጂንግ የፈረሙት ታሪካዊው የጋራ መግለጫ ለአዲሱ የዓለም የኃይል ሚዛን ምን ትርጉም አለው? የሚለውን የምንቃኝ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ በየዓመቱ ግንቦት 17 የሚከበረውን የአፍሪካ ቀን ለአህጉሪቱ እውነተኛ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ምን አዲስ ጥያቄዎችን እና የቤት ስራዎችን ይዞልን መጥቷል? የሚለውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካና እስያ ጥናት ማዕከል መምህር ጌታቸው ካሳ(ዶ/ር) እና የታሪክ እና ቅርስ ጥበቃ ስርአተ-ትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ ተረፈ ወርቁ ጋር ተወያይተንበታል፡ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
107
ከጂኦፖለቲካ እስከ ጤና ስርዓት፤ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጉዞ
"ቻይናውያን በታሪካቸው... መሬት ለመቀማት ወታደራዊ ካምፖችን ወይም ሰፈሮችን ለመመስረት አልመጡም። ይህንን ያደረገው አንድ የወራሪዎች ቡድን ብቻ ነው—በተለይም እንግሊዞች፤ አሁን ደግሞ አሜሪካውያን ይህንን የብሪታንያን ባህሪ ወርሰውታል።" ሲሉ ኬንያዊው የህግ ባለሙያውና የ2023 ሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ተወካይ አህመድ አብዱልአዚዝ ካዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ በመጀመሪያው ክፍል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔ ቢኖርም እንግሊዝ የቻጎስ ደሴቶችን ለሞሪሸስ አለማስረከቧ በአለም አቀፍ ህግና ሉዓላዊነት ላይ ስለደቀነው ስጋት፤ ከህግ ባለሙያውና ከሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ተወካይ አቶ አህመድ አብዱልአዚዝ ካዲ ጋር ሰፊ ቆይታ አድርገናል። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ የሚያዝያ 28 ቀን 2026 እ.ኤ.አ የተካሄደውን አምስተኛው ዓለም አቀፍ የመድሐኒት አቅራቢዎች ጉባዔን መነሻ አድርገን ኢትዮጵያ በመድኃኒት አቅርቦት ራሷን ለመቻልና ቀጣናዊ ማዕከል ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ በተመለከተ፤ ከኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እና ከኢትዮጵያ መድኃኒትና የህክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ታደሰ ተፈሪ ጋር ያደረግነውን ውይይት እናቀርባለን። በመጨረሻም በአፍሪካ የዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀም እና የፋይናንስ ክፍተቶች ዙሪያ፤ ከአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የመሰረተ ልማትና አጋርነት ምክትል ፕሬዝዳንት ፌሊክስ አሮሜ እና ከሞሪሸስ የግብርናና ምግብ ዋስትና ሚኒስትር ዴኤታ ጊልስ ፋብሪስ ዴቪድ ጋር የነበረንን ቆይታ አካትተናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
106
ከመረጃ-መር ፖሊሲ እስከ ሀገር በቀል ምርት፤ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትንሳኤ
"የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችና አገልግሎቶችን በተመለከተ በህዝቡ ግንዛቤ ላይ ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል። የራሳችንን መለያ (Brand) ውብ ካደረግነው፣ የእኛ ምርት በአለም አቀፍ ገበያ ምርጡ መሆን ይችላል። ሁሉንም ነገር መጀመር ያለብን ሀገራችንን በመውደድ ነው፤ ለሀገራችን ውስጣዊ ፍቅርና ክብር ካለን፣ ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶቻችንን እና አገልግሎቶቻችንን እንዴት ማሳደግ እንዳለብን እናስባለን።" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ምሁርና ተመራማሪ መሀመድ ኢሳ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን፤ በመጀመሪያው ክፍል የአፍሪካ ግብርና እና የፖሊሲ ምርምር የአፍሪካ የግብርና ፖሊሲ ምርምር ተቋማት መረብ (ANAPRI) ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንቶኒ ቻፖቶ፤ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ፣ የምግብ ዋስትና እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የግብርና ስርዓቶች ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ ይሰጣሉ።በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፤ ትኩረታችንን ወደ "Made in Ethiopia" ወይም "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አዙረን በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪና አካዳሚሺያን ከሆኑት ከዶ/ር መሀመድ ኢሳ ጋር፤ የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሂደት፣ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ፋይዳ እና የሀገር በቀል ምርት መለያ (Branding) ስላለው ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ እሴት እንወያያለን።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
105
ከተውሶ መዋቅር ወደ ሉዓላዊ ማዕቀፍ፡ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓት ዳግም ቅርጻ
"አፍሪካ የራሷን የአእምሮ ነጻነት ማረጋገጥ ካለባት፣ የትምህርት ሥርዓቱ በሌላ ሀገር በተቀረጸ የተውሶ መዋቅር ላይ ሳይሆን፣ በራሷ ነባራዊ እውነታዎችና ምኞቶች ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ማዕቀፍ ሆኖ እንደገና መነደፍ አለበት። የአፍሪካን አእምሮ ነጻ ማውጣት ማለት ፊታችንን ከዓለም ማዞር ማለት አይደለም፤ ይልቁንም በዚያ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በገዛ የራሳችን ድምፅና ማንነት መቅረብ መቻል ማለት ነው::" ሲሉ የርቀት ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አደራጀው ምሕረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ ለዲጂታሉ ዘመን የሚመጥን እና ከአውሮፓውያን የተውሶ አስተሳሰብ የወጣ የአገር በቀል ትምህርት ፍልስፍናን በአፍሪካ እንዴት መቅረጽ ይቻላል? የርቀት ትምህርት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለአህጉራዊ የዕውቀት ሉዓላዊነት እንዴት ጥቅም ላይ መዋል አለባቸው? በጉዳዩ ላይ ረዳት ፕሮፌሰር አደራጀው ምሕረት ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል። በክፍል ሁለት የአውሮፓ ሕብረት ሀገራት ለአፍሪካ እና እስያ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎችና ምሁራን የሚጥሉት የቪዛ እገዳ በዓለም አቀፍ የውሳኔ ሰጪነት መድረኮች ላይ እኩል ውክልና እንዳይኖር እያደረገ ያለው እንዴት ነው? ይህስ የአፍሪካን ዕውቀትና አቅም ካለማክበር ጋር ምን ትስስር አለው? ናይጄሪያዊው የማኔጅመንት ባለሙያ አደፖጁ ፎዎካን ጋር ያደረግነውን ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
104
ከረግረጋማ መሬት ኢኮኖሚ እስከ ቡና ወጪ ንግድ ስኬት
"የመንግስት ፖሊሲ በግብርናው ዘርፍ በጎን ከመስፋፋት ይልቅ የተጠናከረ (ምርታማ) ግብርናን መጠቀም አለብን የሚል ነው። የዚህ ግብርና በጎን መስፋፋት ተፅዕኖ ረግረጋማ መሬቶቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እና ከመጠን በላይ እንዲራቆቱ ያደርጋል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ግብርናን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና ከአግሮፎሬስትሪ ስርዓቶች ጋር በማቀናጀት ችግሩን መቆጣጠር ይኖርብናል።" ሲሉ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህርና የዌትላንድስ ኢንተርናሽናል ቀጣናዊ አስተባባሪ መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር)ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ሶስት ቁልፍ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡ክፍል አንድ፦ የኢትዮጵያ ረግረጋማ መሬቶች (Wetlands) ያላቸው ያልተነካ ኢኮኖሚያዊ እሴት ምንድን ነው በሚለው ዙሪያ በጉዳዩ ላይ የዘርፉ ባለሙያ የሆኑት መሐመድ ኢሳ (ዶ/ር) ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡናል። ክፍል ሁለት፦ ኢትዮጵያ በያዝነው 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በቡና ወጪ ንግድ ታሪካዊ የሆነውን 3 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንድታስመዘግብ ያደረጉት ዋና ዋና ስራዎች ምንድን ናቸው? የሚለውን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)ጋር እንዳስሳለን። በመጨረሻው ክፍል በአፍሪካ የሕክምና ትምህርት ሥርዓትን ከውጭ ተጽዕኖ ነጻ በማውጣት ሂድት ከአህጉሪቱ ነባራዊ እውነታዎች ጋር ማጣጣም ለምን አስፈለገ? በሚለው ርዕሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ ጤና ፌደሬሽን ም/ፕ ዶ/ር ግርማ አባቢ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
103
ከአእምሮ ነፃነት እስከ አህጉራዊ የውኃ ሀብት ሉዓላዊነት
"የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የእውቀት ምርትን፣ ታሪካዊ ትውስታን እና ምሁራዊ ነፃነትን መልሶ ከመያዝ ትግል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። የትምህርት ሥርዓቶቻችን እና የታሪክ ትረካዎቻችን ከአሮጌው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ካልወጡ አህጉሪቱ እውነተኛ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አትችልም።" ሲሉ የፓን-አፍሪካን አስተሳሰብ ትምህርት ቤት መስራች እና ዳይሬክተር ናይጄል ስቴዋርት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ «አእምሮን ከቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ማውጣት፦ ትምህርት፣ ታሪክ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ መጻኢ ዕድል» በሚለው ዋና አጀንዳ ላይ ከፓን-አፍሪካን አስተሳሰብ ትምህርት ቤት መስራች እና ዳይሬክተር ከናይጄል ስቴዋርት ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግን ሲሆን፤ የትምህርት ሥርዓቶች ንቃተ-ህሊናን እንደሚቀርጹ ሁሉ የልማት ሥርዓቶችም ነባራዊ እውነታን ይወስናሉ በሚለው መርህ፣ በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ የአፍሪካ የጋራ የውኃ ሀብቶች በጂኦፖለቲካዊ ክፍፍል ምትክ እንዴት የአህጉራዊ ውህደት እና የብልጽግና መሣሪያ መሆን እንደሚችሉ በውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ ከሆኑት ከኢንጂነር ተፈራ በየነ ጋር በዝርዝር ተወያይተንበታል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
102
የምዕራባውያን በበላይነት የተቆጣጠሯቸው የፋይናንስ ተቋማት እና የአዲሱ ዓለም ሥርዓት ፈተናዎች
“በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቶች ላይ የተዘረጋው የምዕራባውያን የበላይነት የሚቀጥለው በተቋማዊ የበላይነት ቅንጅት አማካኝነት ነው። ይህም እንደ የአሜሪካ ዶላር ያሉ የመጠባበቂያ ገንዘቦች ካላቸው መዋቅራዊ ኃይል እና ከዓለም አቀፍ የክፍያ ስልቶች ላይ ካለው ቁጥጥር ጋር የተያያዘ ነው። እነዚህ ስልቶች በአንድ ላይ በመሆን፥ ምዕራባውያን አገራት በመላው ዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የጂኦ-ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ያስችሏቸዋል።” ሲሉ በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የልማት ኢኮኖሚስት ለሄሳ ሞሎይ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ሰርጌ ላቭሮቭ እ.ኤ.አ ከግንቦት 19 እስከ 20 ፣ 2026 በቤጂንግ ያደረጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት መነሻ በማድረግ ሁለቱ ሀገራት በጋራ መግለጫቸው ያመላከቱት ባለብዙ ዋልታ የዓለም ስርዓት አመላካች ነጥቦችና የኢኮኖሚ ትስስር በተግባር ምን ይመስላል? በሚሉት ጉዳዮች ላይ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ምሁር እና ተመራማሪ አስራት ኤርሞሎን (ዶ/ር) አነጋግረናቸዋል፡፡ በክፍል ሁለት፦ ዶላር እንደ ዓለም አቀፍ የመጠባበቂያ ገንዘብ ያለው መዋቅራዊ ኃይል እና ምዕራባውያን በዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓቶች ላይ ያላቸው ፍፁም ቁጥጥር፥ በመላው ዓለም ላይ ከፍተኛ የጂኦ-ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ እንዴት አስችሏቸዋል ስንል በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የልማት ኢኮኖሚስት ለሄሳ ሞሎይ (ዶ/ር) ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
101
የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ለአህጉራዊ ሽግግር
"አብዛኞቹ የቢዝነስ ትምህርት ተቋማት ኢንዱስትሪዎችን ሳያሳትፉ የትምህርት ሥርዓቱን (ካሪኩለሙን) በራሳቸው ብቻ ያዘጋጃሉ። ዩኒቨርሲቲዎች ወይም የአካዳሚክ ተቋማት ተማሪዎቻቸውን በምድር ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ሳያስተዋውቁ እንዲሁ ንድፈ-ሃሳብን ብቻ ያስተምራሉ_ ይህ ሁኔታ እንዲቀየር በትጋት ልንሰራ ይገባናል፡፡" ሲሉ የኢትዮጵያ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታቸን የአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርት ቤቶች የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በትክክል መምራት ይችላሉ? ወይንስ አሁንም ከአካባቢያዊ እውነታዎቻችን የራቁ የውጭ ሀገራትን የትምህርት ሞዴሎች ነው እየተከተልን ያለነው? የሚሉትን ጥያቄዎች እ.ኤ.አ ከግንቦት 13 እስከ 14 ፣2026 በአዲስ አበባ በተካሄደው የAABS (African Association of Business Schools) አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ተገኝተን ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ - የኢትዮጵያ የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ዋና ፀሀፊ፣ ፕ/ር አሊስተር ሞኮኤና — የጆሃንስበርግ ቢዝነስ ስኩል ዲን፣ ፕ/ር ኤቤኔዘር አዳኩ — የGIMPA ቢዝነስ ስኩል (ጋና)፣ ዶ/ር የቱንዴ አኒባባ — የሌጎስ ቢዝነስ ስኩል፣ ዶ/ር ሚሪያም ሙግዋቲ — የሚድላንድስ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ዲን (ዚምባብዌ) እና ዶ/ር ኢትዮጵያ ለገሰ — የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ረዳት ፕሮፌሰር አነጋግረናቸዋል፡፡
-
100
ከአሰላለፍ ነፃነት ወደ ስትራቴጂካዊ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ አዲሱ የውጭ ፖሊሲ አካሄድ
"አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ ግንኙነት ውስጥ ሁለቱንም ወገን ተጠቃሚ የሚያደርግ አካሄድን ሲያስቡ፤ የትኛውንም ሀገር ውይም ቀጠና በፍፁም በዕውር ድንብር ማመን የለባቸውም። በመጀመሪያ ደረጃ አፍሪካውያን ማድረግ ያለባቸው ትልቁ ነገር በመካከላቸው እምነትን መገንባት ነው።" ሲሉ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የአፍሪካ አገራት ጉብኝታቸውን ሐምሌ 30 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ጀምረው ነሐሴ 1 እና 2 2018 በኒጀርና ሞዛምቢክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡ ይህ በአህጉሪቱ ላይ ምን አዲስ የፖለቲካ አንድምታ ይዟል? ከቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የ"አሰላለፍ ነፃነት" (non-alignment) መርህ ወጥታ፣ አፍሪካ ዛሬ ወደምትከተለው ስትራቴጂካዊ ሉዓላዊነት እያደረገችው ያለው ሽግግር በተግባር ምን ማለት ነው? በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ከሆኑት ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) ጋር በመሆን፣ ተለዋዋጩን የአለም የኃይል ሚዛን እና የአፍሪካን አዲስ የዲፕሎማሲ በጥልቀት እንመረምራለን። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ
-
99
የአፍሪካ ኢኮኖሚ ለውጥ፦የአለም ፖለቲካዊ መዋዠቅ ለአፍሪካ ኢንዱስትሪ አዲስ መንገድ እንዴት እየፈጠረ ነው?
"ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ የአፍሪካ ኢኮኖሚ መዋቅር ለምዕራባውያን ተገዢ እንዲሆን ተደርጎ ነው የተቀረጸው። የአሁኑ የዓለም አቀፍ አቅርቦት ሰንሰለት መቋረጥ ግን ወደ ውስጥ እንድንመለከት፣ አምራች እንድንሆን እና በአህጉራዊ የነፃ ንግድ ቀጠና በኩል እርስ በርስ እንድንተሳሰር ትልቅ ዕድል የፈጠረልን 'የመቀስቀሻ ደወል' ነው።" ሲሉ በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በክፍል አንድ፦ የአፍሪካ የንግድ ሪፖርት 2026ን መነሻ በማድረግ የዓለም ፖለቲካዊ መዋዠቅ ለአፍሪካ የኢንዱስትሪ ሽግግርና ለአህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ምን ዓይነት አዳዲስ ዕድሎችን ይዞ መጥቷል? ስንል ከከፍተኛ ተመራማሪው ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል። በክፍል ሁለት፦ የአፍሪካ በጎ አድራጎት ለምን የአህጉሪቱን እውነታ ማንጸባረቅ ተሳነው? በባህላዊ እውነታዎች ላይ ተመስርቶ እንዴት በድጋሚ ሊዋቀር ይችላል? ስንል የሲቪ (SIVI) ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ቴንዳይ ሙሪሳ እና የጋልቫናይዚንግ አፍሪካ ኮንሰልት የልማት አማካሪ ጃኔት ማዊዩ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
98
ከዲጂታል ጥገኝነት ወደ ዲጂታል ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ፈተና
"ለእኔ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማለት ቴክኖሎጂን መግዛት ብቻ አይደለም፤ ቴክኖሎጂውን እንዴት እንደምንጠቀምበት፣ የዜጎችን ዲጂታል ሀብት እንዴት እንደምንጠብቅበት እና ማኅበረሰቡን እንዴት እንደሚያገለግል መቅረጽም ነው። […] አፍሪካ የራሷን የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፍ ካልገነባች በቴክኖሎጂ ዘርፍ የቅኝ ግዛት ሰለባ የመሆን አደጋ አለ።" ሲሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና የቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እስክንድር መስፍን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በተጨማሪም "ገንዘብ ካለህ ቴክኖሎጂን በአንድ ሌሊት መግዛት ትችላለህ፤ ነገር ግን ዲጂታል ብቃት፣ የሰው ኃይል አቅምና ተገቢ የአስተዳደር ሥርዓት ያለ ቴክኖሎጂ በማይበቅል መሬት ላይ ዘር እንደመበተን ነው።" ሲሉ ተናግረዋል፡፡በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ከቴክኖሎጂ አስተዳደር አማካሪ እንዲሁም የCloud Security Alliance Ethiopia Chapter የቦርድ አባል ከሆኑት ከአቶ እስክንድር መስፍን ጋር፣ አፍሪካ ከዲጂታል ጥገኝነት ወጥታ እውነተኛ ዲጂታል ሉዓላዊነትን እንዴት ልትገነባ እንደምትችል በስፋት እንወያያለን።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦
-
97
የጥንታውያን የአፍሪካ መንግስታት ዳግም ውህደት፦ ባህል፣ ስልጣን እና ልማት ከቅኝ ግዛት ድንበሮች ባሻገር
"ወጣቶቻችን እውነተኛ ማንነታቸውን አውቀው እንዲታጠቁ ካደረግን ከ10 እና 20 ዓመታት በኋላ የሚጠፉ አይሆኑም፤ ይልቁንም በባህላቸው እየኮሩ ለዓለም የሚያስተዋውቁ እነሱ ይሆናሉ።" ሲሉ በጋና የባህላዊ መሪ፣ የ'ቴስት ኦፍ አፍሪካ' ተባባሪ መስራች እና የ'ሲስተር ኪንግደም ኔትወርክ' መስራች የሆኑት ቴንጎል ክፕሌማኒ ለስፕትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፤ አፍሪካ ከመደበኛው የመንግስት መዋቅር ባለፈ በጥንታውያን መንግስታቷ እና በባህላዊ እሴቶቿ አማካኝነት ያላትን የአንድነት አቅም እንቃኛለን። በጋና የባህላዊ መሪ፣ የ'ቴስት ኦፍ አፍሪካ' ተባባሪ መስራች እና የ'ሲስተር ኪንግደም ኔትወርክ' መስራች ከሆኑት ከቴንጎል ክፕሌማኒ ጋር በመሆንም፤ የቅኝ ግዛት ድንበሮች ያሻከሩትን የታሪካዊ ትስስር ዳግም ማጠናከር ስለሚቻልባቸው መንገዶች፣ የባህላዊ ተቋማት ለዘመናዊ አስተዳደርና ለኢኮኖሚ ትብብር ያላቸውን ፋይዳ፣ እንዲሁም ባህላዊ ማንነትን ለሰላምና ለቱሪዝም ልማት ስለመጠቀም በዝርዝር እንወያያለን።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፦
-
96
ኢነርጂ፣ ኢንቨስትመንትና የሩሲያ ቴክኖሎጂ፦ የኢትዮጵያ የኑክሌር ጉዞ
"የኑክሌር ኃይል ማመንጫ መገንባት ሀገሪቱ አስተማማኝ እና ቋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭ እንድታገኝ ያስችላታል። […] ይህ አሠራር ደግሞ ድርጅቶችና ፋብሪካዎች ያለምንም መቆራረጥ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር በር ከፋች ነው። እንዲህ ያሉ ፕሮጀክቶችን መተግበር በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የቴክኖሎጂ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ዋነኛ ማሳያ ሊሆን ይችላል::" ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድ ተወካይ ያሮስላቭ ታራሲዩክ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ከብሪክስ አባልነት በኋላ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያና የሩሲያ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ የንግድ ዕድሎችን እና አዳዲስ ሳይንሳዊ ትብብሮችን በጥልቀት እንመረምራለን። በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን የንግድ ተወካይ አቶ ያሮስላቭ ታራሲዩክ ሰፊ ማብራሪያ ይሰጡናል። በክፍል ሁለት ደግሞ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሕ/ተ/ም/ቤት ያጸደቀው የኢትዮ-ሩሲያ የጋራ ባዮሎጂካል ምርምር ማዕከል ስምምነት ለሀገሪቱ የብዝሃ-ሕይወት ጥናት፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለከፍተኛ ትምህርት ዕድገት ምን ፋይዳ አለው ስንል በም/ ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ፈትሂ መህዲ ማብራሪያ ጠይቀናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ይከታተሉ ፡
-
95
ሉዓላዊነት በተግባር፡ ከዓለም አቀፍ አጋርነት እስከ አፍሪካ የጤና ነፃነት
“ከብሪክስ አንጻር ሲታይ፣ ኢትዮጵያንና ጥቂት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ያካተተ ዘርፈ-ብዙ ገጽታ አለው። ይህ ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ራሱ የአፍሪካ-ሩሲያን ግንኙነት ለማጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ ይህም የደቡብ-ደቡብ ትብብር ዋነኛ ምሰሶ ነው። እንዲሁም ይህ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ነው። ይህ ግንኙነት እየሰፋ የመጣ መስክ ያለው ሲሆን፣ ለሁለቱም ወገኖች ማለትም ለሩሲያ ፌዴሬሽን እና ለአፍሪካ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው።” ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው የዓለም ሥርዓት ውስጥ የአፍሪካን ድርሻ የሚዳስስ ጠንካራ የሁለት ክፍል ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል። በክፍል አንድ የፖለቲካ፣ የደህንነት፣ የኢኮኖሚ እና የሰብዓዊ ግንኙነቶችን ትብብር የሚቀርፀውን የሩሲያ–አፍሪካ አጋርነት መድረክ የድርጊት መርሃ ግብር (2023–2026) ከአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር እንመረምራለን። በክፍል ሁለት፡ በአዲስ አበባ (መጋቢት 18–19 ቀን 2018 ዓ.ም) በተካሄደው 62ኛው የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት፣ የአፍሪካን የጤና ስርዓት ከጥገኝነት ለማላቀቅና ራስን ለመቻል የሚደረገውን አስቸኳይ ጥረት ከፕሮፌሰር ጆን ዌሩ፣ የክሊኒካዊ ጉዳዮች ባለሙያ፣ ከዶ/ር ሙባረክ ሸምሱ፣ የህብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስት እንዲሁም ከቤተልሄም በቃሉ፣ የ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪ ጋር እንቃኛለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ
-
94
የብር ምንዛሬ ለውጥ፦ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ላይ ምን ለውጥ አመጣ ?
“ገንዘቡ እንደ አስፈላጊነቱ ከተለቀቀ ችግሩ የዋጋ ንረትን ያባብሳል። ህዝቡ የዋጋ ንረት መሸከም አይችልም። በተለይ ቋሚ ገቢ ያላቸው።” ሲሉ የዘመን ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር አቶ መሰረት ወንድም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የዘመን ባንክ ዋና የፋይናንስ ኦፊሰር ከሆኑት ከአቶ መሰረት ወንድም ጋር በመሆን የ[ኢትዮጵያ]ብር ምንዛሬ ለውጥ፣ ለገንዘብ ፍሰት፣ ለብድር እና ህዝቡ በፋይናንስ ሴክተሩ ስርዓቱ ላይ ያለው እምነት ላይ ምን ሊፈጥር እንደሚችል የዳሰስን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ የዲጂታል አስተዳደር እና ትራንስፎርሜሽን አማካሪ ከሆኑት ከአቶ እስክንድር ቸርነት ጋር፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስርዓቶች በስተጀርባ ያሉትን እና ብዙ ጊዜ ትኩረት የማይሰጣቸውን መዋቅሮች እንቃኛለን፡፡
-
93
የሰብአዊ እርዳታ ሉዓላዊነት፡- የሀገርን ነፃነትና ክብር የማስጠበቅ ተግባር
"የሰብአዊ እርዳታ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አሁን ላይ ለማንኛውም ሀገር ምርጫ አይደለም፤ በተለይም ስለ ሀገር ክብር፣ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለሚያስብ ሀገር ይህ ጉዳይ የግድ የሚል ተግባር ነው።" ሲሉ የብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለ ሶስት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በመጀመሪያው ክፍል በአርኪኦሎጂ እና በሰው ልጅ አመጣጥ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የፓሊዮአንትሮፖሎጂ ተመራማሪዎች ከሆኑት ከዶ/ር በርሄ አስፋው እና ከዶ/ር ዮናስ በቀለ ጋር በመካከለኛው አዋሽ ስለተገኙ አዳዲስ የሳይንስ ግኝቶች እንወያያለን።በሁለተኛው ክፍል፤ የአፍሪካን የሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የመከላከል አቅም እንዲሁም ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት የመውጣት አስፈላጊነትን በተመለከተ ከብሄራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም ጋር የነበረንን ቆይታ እናቀርባለን።በመጨረሻም አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅማ የምግብ ዋስትናዋን እንዴት ማረጋገጥ ትችላለች? በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ ከአፍሪካ ህብረት የግብርና እና ምግብ ዋስትና ክፍል ተጠባባቂ ሃላፊ ዶ/ር ጃኔት ኤደሜ እና ከAGRA የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር ይሄነው ዘውዴ ጋር ያደረግነውን ውይይት አካትተናል።
-
92
የኢኮኖሚ እና የቅኝ ግዛት ድንበሮች፡- የአፍሪካ ልማት ሁለት ግንባሮች
“የቅኝ ግዛት ድንበሮች ተፈጥሯዊ ድንበሮች አይደሉም… የተፈጠሩት ለአፍሪካ ሕዝቦች ጥቅም አይደለም። [……]እነዚህ የዘፈቀደ ድንበሮች የጎሳ፣ የባህል እና የቋንቋ እውነታዎችን ችላ ብለው የተበጣጠሰ ማንነትን አስከትለዋል።” ሲሉ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው አሰፋ ባልቻ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በክፍል አንድ፣ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ እና የአለም አቀፍ ልማት አማካሪ ሳታ አብራሃም (ዶ/ር ) ጋር በመሆን የአፍሪካን የሥራ ፈጠራ ዘርፍ ዕድሎች እና ተግዳሮቶች የቃኘን ሲሆን፤ በክፍል ሁለት ደግሞ የታሪክ መምህርና ተመራማሪው አሰፋ ባልቻ (ዶ/ር) ጋር በመሆን የሕዝቦቿን ሁኔታ ከግንዛቤ ሳይከቱ የተከለሉት የአፍሪካ ቅኝ ግዛት ድንበሮች አሁንም ድረስ ማህበረሰቦችን እንዴት እየከፋፈሉ እና ግጭትን እያስከተሉ እና እያቀጣጠሉ እንዳሉ በሰፊው ዳስሰነዋል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡
-
91
የአፍሪካ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት፦ ከጥሬ ዕቃ ወደ ማኑፋክቸሪንግ እና የሴንትፒተርስበርግ ጉባዔ ሚና
“ለአፍሪካውያን የመጀመሪያው እና ዋናው ተግባር የገዛ ቤታችንን ማስተካከል ነው። ወደ እነዚህ ዓለም አቀፍ መድረኮች የምንሄደው የምንሸጠውን ነገር ሳንለይና ሳናደራጅ መሆን የለበትም፤ የሌለንን ነገር ለመሸጥ መሞከር ዘበት ነው። በመጀመሪያ የተፈጥሮ ሀብታችንን እና የፋይናንስ መዋቅራችንን በራሳችን ማደራጀት አለብን። ይህንን ካደረግን ወደ መድረኩ የምንመጣው በበላይነት እና በጥንካሬ ነው፤ ያለበለዚያ ግን፣ ውይይቶቹን ስንከታተል እንደምናየው፣ የምንሄደው ሁልጊዜ የእርዳታ እና የችሮታ ልመና ሰነድ ይዘን ብቻ ይሆናል።” ሲሉ በማላዊ ብሔራዊ የፕላኒንግ ኮሚሽን የልማት ኢኮኖሚስት የሆኑት ኦስቲን ቺንግዌንግዌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት መጀመሪያ ክፍል ከሰኔ 03 እስከ ሰኔ 06፣ 2026 እ.ኤ.አ. የሚካሄደውን የሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረምን (SPIEF 2026) እንቃኛለን። የአፍሪካን አንድ ወጥ አህጉራዊ ድምፅ፣ አማራጭ ክፍያዎችንና ማዕቀብን የመቋቋም ዕድሎችን በማላዊ ብሔራዊ የፕላኒንግ ኮሚሽን የልማት ኢኮኖሚስት የሆኑት ኦስቲን ቺንግዌንግዌ ያብራራሉ።በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር አህጉሪቱን ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ማኑፋክቸሪንግና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስለማሻገሩ እንዲሁም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ስለማስከበሩ እና የሴንት ፒተርስበርግዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ሚናን እንቃኛለን ለዚህም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና መምህር ከሆኑት ከ መሐመድ ሙሳን (ዶ/ር) ጋብዘናል።ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
90
81ኛ ዓመት የድል ቀን መታሰቢያ፦ የኢትዮጵያና የሶቪየት ህብረት የጋራ የፀረ-ፋሺዝም ትግል
"የሶቪየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችው ድል የሩሲያውያን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንም ጭምር ነው፤ ምክንያቱም ሁለቱም ሀገራት ለነፃነትና ለሉዓላዊነት ሲሉ ለከፈሉት መስዋዕትነት ትልቅ ማሳያ በመሆኑ ነው።" ሲሉ የታሪክ ተመራማሪውና ደራሲ አቶ ጥላሁን ጣሰው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ "በናዚ ጀርመን ላይ የተገኘው ድል የሁላችንም ድል ነው፤ ለሩሲያውያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካውያን በተለይም ደግሞ ላልተገዛችው ኢትዮጵያ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡" በማለት ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው አክለዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶአችን፤ የሶቪየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን 81ኛ ዓመት መታሰቢያ አስመልክቶ፣ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የታሪክ ቁርኝት እንቃኛለን። በውይይታችንም የታሪክ ተመራማሪውና ደራሲ አቶ ጥላሁን ጣሰው እንዲሁም የአርበኛው ፊታውራሪ ቅጣው አዘነ ልጅ እና እና ታሪክ ወዳዱን የኢንዱስትሪ ኢንጂነሪንግ ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው እንግዶቻችን አድረገናቸዋል።
-
89
ከመገኛነት ወደ ጠንካራ የምርት መለያነት፦ የኢትዮጵያ ስፔሻሊቲ ቡና በአለም አቀፍ መድረክ
"የኢትዮጵያ ቡና ከሰራነው በላይ ፈጣሪ የሰጠን ትልቅ ሀብት ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ቡና ከአለም ቢጠፋ፣ ቡና ከአለም ላይ እንደሚጠፋ ያውቃሉ? ምክንያቱም የቡና ዝርያ ክምችቱና (Genetic Reserve) መሰረቱ ያለው እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።" ሲሉ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ግዛት ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታየው የዋጋ አለመረጋጋት እና በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት የኢትዮጵያን የቡና ኤክስፖርት እንዴት እያስተጓጎለ ይገኛል? ይህስ ለውጭ ምንዛሬ፣ ለኑሮ ሁኔታ እና ለገበያ መረጋጋት ምን ትርጉም አለው? በሚሉ ነጥቦች ላይ የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ከሆኑት አቶ ግዛት ወርቁ ጋር የተወያየን ሲሆን፤ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት (UNHRC) በሩሲያ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ መሰረት አድርገን ጠበቃ እና የህግ አማካሪ ከሆኑት ከአቶ አንዱዓለም በውቀቱ ጋር የሰብአዊ መብቶች ስርዓት ስለተደቀነብት ፈተና ያደረግነውን ውይይት በሁለተኛው የመሰናዶአችን ክፍል አካትተነዋል፡፡
-
88
ታሪካዊናባህላዊ ትስስር፦ ውኃ የአፍሮ-ዲያስፖራ የጋራ ቅርስ
"ውኃ ለአፍሪካ እና ለአፍሮ-ዲያስፖራው ከቀላል የተፈጥሮ ሃብትነት ባለፈ፣ አህጉራትንና ትውልዶችን የሚያገናኝ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ድልድይ ነው። ሳይንስን ከባህል፣ ቴክኖሎጂን ከአካባቢያዊ እውቀት ጋር በማጣመር የአየር ንብረት መረጃ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ እና በግሎባል ሳውዝ አገራት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር ይኖርብናል፡፡" ሲሉ የኢትዮጵያ ኦሽን ኢንስቲትዩት ተባባሪ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኪዳን ኒኪታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛውየራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ "የሰማያዊ ኢኮኖሚዎችን ማስተሳሰር፦ አፍሪካን እና አፍሮ-ዲያስፖራን በውኃ ማገናኘት" በሚል ዋና ርዕስ ዙሪያ የውቅያኖስ ሳይንቲስት እና የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ባዮሎጂስት ከሆኑት ከኪዳን ኒኪታ ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግን ሲሆን፤ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር እና ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን በድጋሚ በባረቁበት በዚህ ወቅት፣ ያልተማከሉ የሳይንስ ግኝቶች፣ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪዎች "Lab in a Bag" እና የደቡብ-ደቡብ ትብብር ምን ያህል ለውጥ እያመጡ እንደሆነ እንቃኛለን። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የሰማያዊ ፣ የአረንጓዴ እና የፈጠራ/የካሮት ኢኮኖሚዎች ትስስር ለአፍሪካ ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ እና ለአካባቢ መላመድ ያለውን ወሳኝ ሚና በዝርዝር ዳሰናል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጃ ያድምጡ ፡
-
87
የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ዋስትና በኢትዮጵያ፦ ከፖሊሲ ወደ ተግባር
"የምግብ ስርዓት የምንለው ከምርት ጀምሮ እያንዳንዱ ሂደት አልፎ ምግብ የሸማቹ አፍ ውስጥ እስከሚገባ ድረስ ያለውን አጠቃላይ ሰንሰለት ነው።... የአየር ንብረት ለውጥ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ የዕሴት ሰንሰለቱ ላይ ምርታማነትንና ፍጆታን አደጋ ላይ የሚጥሉ መዛባቶችን እየፈጠረ ነው። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የምግብ ሥርዓት መገንባት ማለት ሥርዓቱ እነዚህን አስደንጋጭ ክስተቶች መቋቋም እንዲችል ማድረግ ነው፤ በዚህም የቤተሰብን ኑሮ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በዘላቂነት ማስቀጠል ይቻላል።" ሲሉ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር (ዶ/ር ) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ የአየር ንብረት መዛባት እና የአፈር መጎሳቆል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አነስተኛ አራሾችን ህልውና እየፈተኑ ይገኛሉ። ታዲያ ግብርናን ከምርት መጨመር ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም፣ ዘላቂነት እና ሉአላዊነትን ባገናዘበ መልኩ እንዴት መቅረፅ እንችላለን? የፖሊሲ ማዕቀፎችስ በምድር ላይ ያለውን እውነታ በትክክል እያስተናገዱ ነው? በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ሰላማዊት ገብረእግዚአብሔር (ዶ/ር) ጋር ያደረግነውን ጥልቅ ቆይታ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን መረጃ ያድምጡ ፡
-
86
የአርሶ አደሮች የፈጠራ ክህሎት እና የሀገር በቀል እውቀት ሚና
“እውቀት ፓስፖርት የለውም፤ እውቀት ተግባር (ልምድ) ነው ያለው። አርሶ አደሮቻችን ምርጥ ዘር ሲመርጡ 'ዝርያ ማሻሻል'፣ ዝናብን ሲተነብዩ ደግሞ 'የጥናት ዘዴ' እንበለው፤ ለሥራቸው ሳይንሳዊ ስሙን በመስጠት የሚገባቸውን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል፡፡ ግባችን ጥገኝነት ሳይሆን ክብር፣ ጽናትና ሀገራዊ እራስን መቻል ነው፡፡” ሲሉ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 🔉በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ መሰናዶ፣ በመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት "ከአርሶ አደሮች፣ ለአርሶ አደሮች፣ በአርሶ አደሮች" በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ልዩ አገር አቀፍ ጉባኤ እንቃኛለን። በጉባኤው ላይ አርሶ አደሮች እንደ ተመራማሪ ቀርበው ድንች በከርሰ ምድር የማቆየት ዘዴን እና የቴምር ምርትን በአካባቢያቸው የመመረት ስኬታማ የፈጠራ ስራዎቻቸውን አጋርተዋል።🗣በእንግድነት የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና እና የወሃ ልማት አስተዳደር እና ሃይድሮሎጂ ረ/ፕ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶ/ር ዓለማየሁ አባተ ተገኝተው፣ የአርሶ አደሩን ሀገር በቀል እውቀት ከዘመናዊ ምርምር ጋር በማቀናጀት ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የፖሊሲ አውጪዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት ሰፊ ትንተና ይሰጡናል።
-
85
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ የስትራቴጂካዊ አማራጮች ፍለጋ
“ከውጭ ነዳጅ ጥገኝነት ለመውጣት የተቀናጀ ስትራቴጂ ያስፈልጋል። ትኩረታችንን የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማትን በማዘመን፣ በፀሐይ ኃይል እና በአገር ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ምርት ላይ በማድረግ የኢነርጂ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል።” ሲሉ በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ወስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ጀማል መሀመድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ከነዳጅ ፖለቲካ እስከ ቀጠናዊ ደህንነት፦ ኢትዮጵያ በአዲሱ የዓለም የኃይል አሰላለፍ ውስጥ! በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን ሁለት አንገብጋቢ ጉዳዮችን ከባለሙያዎች ጋር በጥልቀት እንመረምራለን፦ የነዳጅ ጂኦ-ፖለቲካ እና የኢትዮጵያ ፈተና፦ የዓለም የነዳጅ ገበያ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚፈጥረውን ጫና እና ሀገሪቱ የጀመረችው የጋዝ ተሽከርካሪዎች (Natural Gas Conversion) ሽግግር እንደ መፍትሄ ሊታይ ይችላል? የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት (PSI) ከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ጀማል መሀመድ ሰፊ ትንታኔ ይሰጡናል። የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ወታደራዊ ትብብር፦ ሽብርተኝነትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል በኢትዮጵያ እና በታንዛኒያ መካከል እየተገነባ ያለው ወታደራዊ ግንኙነት በቀጠናው የኃይል ሚዛን ላይ ምን ለውጥ ያመጣል? የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኙ አብዱልናስር ምዊታ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን እይታ ያካፍሉናል።
-
84
የሥነ-ምግባር ሉዓላዊነት፦ አፍሪካ የሞራል መሠረቷን ከምዕራባውያን ተፅዕኖ እንዴት ትጠብቅ?
"ሥነ-ምግባር ለአንድ ማህበረሰብ ህልውናው ነው። አፍሪካ የራሷን የሞራል መሠረትና እሴቶች መጠበቅ ካልቻለች፣ በግሎባላይዜሽን ማዕበል ውስጥ ማንነቷን አጥታ የሌሎች እሴቶች ተገዢ ትሆናለች።"ሲሉ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ዶ/ር አባ መዝገቡ ካሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ የዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ ሥነ-ምግባር ዓለም አቀፋዊ ነው ወይስ በባህልና በስልጣን የሚወሰን? የአፍሪካ ማህበረሰቦች የውጭ 'እሴቶችን' እየተቀበሉ ነው ወይስ ያለ ምርጫ እየተጫኑባቸው ነው ? ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤቶች እና የሃይማኖት ተቋማት የሞራል መሸርሸርን ለመከላከል ምን እያደረጉ ነው? ሲል ይጠይቃል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን ዶ/ር አባ መዝገቡ ካሳን ጋብዘናቸዋል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
-
83
ፓን-አፍሪካኒዝምን የማክሸፍ ዘመቻ፦ በሳህል ቀጣና ለአሸባሪዎች መረጃ የሚሰጠው ማን ነው?
'' የተራቀቀ መረጃና ቴክኖሎጂ እየቀረበላቸው ነው፤ የፈረንሳይ ሚናም ይኸው ነው። ፈረንሳይ ለረጅም ጊዜ የጨበጠችውን ነገር በቀላሉ ለመልቀቅ ፍቃደኛ አይደለችም።[...] "እነዚህ ሶስት ሀገራት (ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር) ከሩሲያ ጋር ለመሰለፍ መወሰናቸው በዩክሬን አይን እንደ ጠላት እንዲታዩ አድርጓቸዋል። ፈረንሳይ እነዚህን ሀገራት ኢላማ ለማድረግ ከዩክሬን ጋር የደህንነት መረጃዎችን ስታስተባብር እንደነበር መረጃዎች አሉ። " ሲሉ ፓን አፍሪካኒስትና የቢዝነስና የማህበረሰብ ልማት አማካሪው ካባላ ጆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በምዕራብ አፍሪካ እየተከሰተ ያለውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ሽኩቻ፣ የፈረንሳይና የዩክሬን ሚስጥራዊ ጥምረት እና አዲሱ የፓን-አፍሪካኒዝም ንቅናቄ የገጠመውን ፈተና አስመልክቶ ከእንግዳችን ከፓን አፍሪካኒስት ካባላ ጆን ጋር ሰፊ ውይይት አድርገናል። መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
-
82
የኢትዮጵያ ቡና፣ አበባ እና ወጣቶች፦ የአፍሪካን ልማት እንደገና መመልከት
"በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎች ላይ ባደረግነው ጥናት መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት ለቡና ልማት የምንጠቀምበት አካባቢ ወደ 60% የሚጠጋው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊጠፋ እንደሚችል ደርሰንበታል። አንዱ የመላመጃ መንገድ ደግሞ ቡናን በከፍተኛ ከፍታ ላይ ወደሚገኙ ቦታዎች ማዛወር ሲሆን፣ እነዚህ ከፍተኛ ቦታዎች ግን የደን ሽፋናቸውን ያጡ ናቸው። ስለዚህ የ'አረንጓዴ አሻራ' እና ሌሎች የደን ልማት ተነሳሽነቶች ደኖች እንዲያገግሙ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።" ሲሉ የአካባቢ እና የቡና ደን ፎረም ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ታደሰ ወ/ማርያም (ዶ/ር) ስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በቅድሚያ የአካባቢ እና የቡና ደን ፎረም ዋና ዳይሬክተር ታደሰ ወልደማርያም (ዶ/ር) ጋር በመሆን፤ የኢትዮጵያን ልዩ የቡና ቅርስ እና ያለውን ሥነ-ምህዳራዊ ጠቀሜታ እንመረምራለን፤ በማስከተልም በኢቲ ሀይላንድ ፍሎራ የእርሻ ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት ከእመቤት ተስፋዬ ጋር በመሆን፤ በኢትዮጵያ እያደገ ያለውን የሆርቲካልቸር ዘርፍ እንቃኛለን፤ በመጨረሻም ከራሄል አዊንሱ አላቢላ (ጋና) እና ታቢታ ጆሴፍ (ኬንያ) ጋር በመሆን፤ የአፍሪካን የቅኝ ግዛት እና የዛሬው ወጣቶች ይበልጥ ሉዓላዊና የተባበረ የወደፊት ጊዜን እንዴት እየቀረጹ እንደሆነ እንወያያለን። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
-
81
ከሰንሰለት እስከ ስርአት፡- ያልተቋጨው የባርነት ታሪክ
‘‘… እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ የተፈጥሮ ማዕድናት ያሏት አህጉር ፤ አሁንም ድረስ የቅኝ ግዛትና የባዕዳን የንግድ ሥርዓቶችን እንድትከተል መገደዷ በጣም ያሳዝናል።[…]ምክንያቱም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አፍሪካ ገና ከቅኝ ግዛት የኢኮኖሚ ጥቃትና ጭቆና እንዳልነቃች ነው የምትቀሳቀሰው። ይህ ለኔ ከዚሁ አህጉር የሚወጡ ሰዎችን ሌሎች የዓለም ክፍሎችን ለማበልጸግ በጉልበት ሠራተኝነት ከሚጠቀምበት ሥርዓት ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው። ይህ ሥርዓት ዛሬም ድረስ በግልጽ እየተሠራ ነው። ለምሳሌ የተፈጥሮ ማዕድኖቻችን አሁንም ከአህጉሪቱ ተነቅለው ወደ ሌላ አገር ሄደው ይመረታሉ፤ ከዚያም ተመልሰው ለእኛው ይሸጡልናል።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና የአፍሪካ ነፃነትና የጥቁር ሕዝቦች ንቃት -ህሊና አቀንቃኝ ዛንዲሲዌ ራዴቤ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ዓለም በመጋቢት 25 ቀን እ.ኤ.አ የሚዘክረው ዓለም አቀፍ የባርነት እና የአትላንቲክ ባሪያ ንግድ ሰለባዎች መታሰቢያ ቀን ምክንያት አድርገን የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር እና የአፍሪካ ነፃነትና የጥቁር ሕዝቦች ንቃት -ህሊና አቀንቃኝ ዛንዲሲዌ ራዴቤ ጋር ተወያይተናል። ስለ ባርነት የሚተረከውን ታሪክ የሚቀርጸው ማን ነው? እነዚህ ታሪኮችስ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም ላለው የእኩልነት ማጣት፣ ለኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት እና ለስልጣን መዋቅሮች ያላቸው ተጽዕኖስ ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎችን በስፋት ዳስሰናል ። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ ፡
-
80
ሁለት የልማት ግንባሮች፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን መዋጋትና ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት
"አብዛኞቹ ለቲቢ የምንጠቀማቸው መድኃኒቶች ከውጭ የሚገቡ ናቸው። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስወጣናል። ለውጭ ተፅዕኖ ተጋላጭ የሆንነውም ለዚህ ነው። ስለዚህ፣ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን የምናጎለብትበት ዕድል ካገኘን፣ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ የሚያስከትለውን ችግር መቋቋም እንችላለን። ለአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች የራሳቸውን የምርመራ መሣሪያዎችና መድኃኒቶች ማምረት እንዲችሉ አቅማቸውን ማጠናከር ይገባል።" ሲሉ የ 'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በቀዳሚነት መጋቢት 15 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሳንባ ነቀርሳ ቀንን በማሰብ በሩሲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሳንባ ነቀርሳ ዋና አማካሪ ስፔሻሊስት ከሆኑት ከኢሪና ቫሲሊየቫ እንዲሁም የቪ.ኤች.ኤስ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከአቶ እንደአልካቸው ፍቃዱ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የሳንባ ነቀርሳ ከድህነት፣ ከጤና ሥርዓት እና ከማኅበራዊ እውነታዎች ጋር እንዴት እንደሚገናኝ እንቃኛለን፤ በማስከተልም፣ በ10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲ ፍሎራ ኤክስፖ ላይ ተገኝተን ከኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ እና ከአቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ የኢትዮጵያ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ለኢኮኖሚው ያለውን ሚና እንዳስሳለን፡፡ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
79
''ያልተበደረችውን ዕዳ የምትከፍለው አፍሪካ'':-የአየር ንብረት ለውጥ እና 'ዘመናዊ' ተብለው የቀረቡ የግብርና ወጥመዶች
"ዓለም ቀደም ሲል ከነበረው የአስተሳሰብ ዘይቤ በተለየ መንገድ ማሰብ ይኖርበታል። መሰረታዊ ነገሮች መለወጥ አለባቸው፤ ምክንያቱም አሁን ያለው ሁኔታ ፍትሃዊ ያልሆነና ዘላቂነት የሌለው ነው። ስለዚህ፣ የምዕራባውያን ዓለም ለአየር ንብረት ለውጥ ካደረጉት አስተዋጽኦ ጋር የሚመጣጠን በቂ ድጋፍ የማቅረብ ኃላፊነትን ሊወስዱ ይገባል፡፡" ሲሉ የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በክፍል አንድ የአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካን ግብርና እንዴት እየቀየረው እንደሆነና አፍሪካ ለዓለም አቀፉ የጋዝ ልቀት የምታበረክተው አስተዋጽዎ በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ለምን የከፋውን ጫና ለመሸከም እንደተገደደች የግብርና ሳይንቲስት እና ተመራማሪ ከሆኑት ፀደቀ አባተ (ዶ/ር) ጋር ባደረግነው ቆይታ የዳሰስነው ሲሆን፤ በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ ከሆኑት ከዶ/ር ሩት ዳኛቸው ጋር በመሆን፣ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዘንድ እየተስፋፋ የመጣውን የሱስ ተገዥነት እና የአእምሮ ጤና ቀውስ እንፈትሻለን፤ ለዚህም ዝምተኛ የህዝብ ጤና ተግዳሮት መንስኤ የሆኑትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ስርዓታዊ ጫናዎችን በዝርዝር እንመለከታለን።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ
-
78
የአእምሯዊ ንብረት መብት ተጽዕኖ በአፍሪካ ፋርማሲዩቲካልስ ኢንዱስትሪ ላይ
“አብዛኞቹ የተከናወኑት በምዕራባውያን እና በአውሮፓውያን ነው። ስኮቶች፣ እስያውያን እና አፍሪካውያን ደግሞ በማህበረሰብ ፋይናንስ እና መሰረተ ልማቶች ባላቸው ሰፊ ተደራሽነት ምክንያት ኢንቨስት እያደረጉ ነው። ስለዚህ፣ በርካታ ኢንቨስትመንቶች እንዳሉ እስማማለሁ:: እናም ኢንቨስትመንቱ ሊመለስላቸው ይገባል። ነገር ግን፣ ይህ መሆን ያለበት የፈጠራ ስራዎችን እና ምርምርን በማገድ መሆን የለበትም።” ሲሉ የኪሊች ኤስትሮ ባዮቴክ ኃ.የተ.የግ.ማ መስራችና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቀዳሚነት የኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ጋር ስለ አእምሯዊ ንብረት መብት እና መድኃኒት አቅርቦት እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ከመጋቢት 7–9 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተካሄደው የደቡብ አፍሪካ-ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም ላይ ተገኝተን የደቡብ አፍሪካ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ውድድር ሚኒስቴር የኤክስፖርትና ማርኬቲንግ ዋና ዳይሬክተር ዛኔሌ ሳኒን እንዲሁም የሉንየዚ ፋርምስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳምኬሊሲዌ ሲቶሌን በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ አነጋግረናቸዋል።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ
-
77
መረጃ፣ ቋንቋ እና ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የትርክት ትግል
“ከዚህ ቀደም ምዕራባውያን በአካል መጥተው የወረሩን ጊዜያት ነበሩ። የአፍሪካን ሕዝብ በቅኝ ገዝተዋል። ዛሬ ግን ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል። አሁን ደግሞ በመረጃ ቋቶቻቸው አማካኝነት ሊገዙን እየሞከሩ ነው። የማይወክሉንን ነገሮች ሁሉ እየሰበሰቡ ‘የእናንተ ተሞክሮ ይህ ነው’ ይሉናል። ነገር ግን ያ እኛን አይገልጸንም። ለዚህ ነው አፍሪካውያን የራሳችን የሆነ ‘የመረጃ ስብስብ’ እና የራሳችን የሆነ የቋንቋ ማቀነባበሪያ ዘዴ (Language processing) ሊኖረን የሚገባው።” ሲሉ በርቀት እና ኢ-ለርኒንግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አደራጀው ምህረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስለ አፍሪካ ምን ማወቅ እንዳለበት የሚወስነው ማነው? አፍሪካስ የራሷን ታሪክ በየትኛው ቋንቋ ትናገራለች? በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ከዶ/ር አደራጀው ምህረት ጋር ስለ "አልጎሪዝም የበላይነት" እንወያያለን። እንዲሁም በኢትዮጵያ የኩባ ከአምባሳደር ሜይሊን ሱዋሬዝ አልቫሬዝ እና ሌሎችም ጋር በመሆን ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀንን እናከብራለን፤ በኮድ እና በባህል ውስጥ ያለውን "የትርክት ሉዓላዊነት" ትግልም በጥልቀት እንመረምራለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
-
76
ከአፍ መፍቻ ቋንቋ እስከ ፋይናንስ አቅም፦ የአፍሪካ መዋቅራዊ ሽግግር
“የአፍሪካ የዕውቀት ሥርዓቶች አብዛኛውን ጊዜ የሥነ-ምግባር ወጎችን እና የማኅበረሰብ ትውስታዎችን ያካተቱ ነበሩ። እነዚህ ደግሞ በአፍሪካ ወይም በቅኝ ተገዢ አገሮች ላይ በተጫነው በጽሑፍ በሰፈረ ቀጥተኛ ቀኖናዊ (dogmatic) እና ቢሮክራሲያዊ አመክንዮ ሙሉ በሙሉ ተተኩ። […]ስለዚህ፣ ቋንቋ የአስተዳደራዊ ምክንያታዊነት መሣሪያ በመሆን፣ ተለዋዋጭ የነበሩ ማኅበራዊ ሥርዓቶችን ወደ ደረቅ፣ ሕጋዊ እና ቀኖናዊ የፖለቲካ መዋቅሮች ለውጦታል።” ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር አስቻለው ታደሰ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስ እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ ዲን ከሆኑት ከዶ/ር አስቻለው ታደሰ ጋር በመሆን ዓለም አቀፍ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቀንን ስናከብር የቅኝ ግዛት ቋንቋዎች በአፍሪካ የእውቀት ስርዓት እና በማንነት ላይ ያሳረፉትን ዘላቂ ተጽዕኖ እንዳስሳለን። በተጨማሪም ከአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም 2026 የተገኙ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን— ከክላቨር ጋቴቴ፣ ከዶ/ር ጁማ ሙክዋና፣ ከቤንጃሚን ኤቪታ ኦማ እና ከፋቱ ኪንቴህ ጋር በመሆን—ስለ ፋይናንስ ሉዓላዊነት፣ ስለ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ፣ ስለ ወጣቶች ፈጠራ እና አህጉሪቱ ለኢኮኖሚ ነፃነት ስለምታደርገው ጥረት በክፍል ሁለት ዝግጅታችን ዳስሰነዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
-
75
የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት እና የአፍሪካ አህጉራዊ የልማት አማራጮች
"በቅርቡ በኢራን የታዩትን ክስተቶች፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ በከፈቱት ጥቃት፣ እንዲሁም ትንሽ ቀደም ብሎ በቬንዙዌላ የሆነውን ስንመለከት፤ እነዚህ ክስተቶች ዓለም አቀፋዊውን መዋቅር እየቀየረ ያለ አዲስ ሥርዓት መኖሩን ይነግሩናል። አሁን ባለንበት ሁኔታም የኃይል ፖለቲካ ከሕግ የበላይነት በላይ እየገነነ መጥቷል። በዚህ ሂደት ውስጥ ደግሞ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት የደቡባዊ ዓለም ሀገራት ያላደጉና በማደግ ላይ ያሉ አገራት ናቸው።" ሲሉ የልማት ኢኮኖሚስቱ እንዳልካቸው ስሜ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል ከልማት ኢኮኖሚስቱ እንዳልካቸው ስሜ (ዶ/ር) ጋር በመሆን ዓለም አቀፋዊ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች—በተለይም በኢራን ዙሪያ ያለው አለመረጋጋት—በአፍሪካ የኢነርጂ ገበያ፣ የንግድ መስመሮች እና የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ላይ ምን ተፅዕኖ ያሳድራሉ? የሚሉትን ጥያቄዎች የምንዳስስ ሲሆን፤ በክፍል ሁለት፦ የ2025 የዓለም አቀፍ የረሃብ መረጃ ጠቋሚ ግኝቶችን የአፍሪካ ህብረት ግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ሰማያዊ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ከሆኑት ከሙሴ ቪላካቲ እና በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ተመራማሪ ከሆኑት ደሳለኝ ቤኛ (ዶ/ር) ጋር ዳስሰነዋል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
-
74
"ሩሲያ የዲሞክራሲያችን ጋሻ ናት" — ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፋውስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ ከየካቲት 26 እስከ የካቲት 27 ፣ 2018 ዓ.ም በሩሲያ ሞስኮ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። "የሉዓላዊነት መርሆዎችን እና የሰላም ጥረቶችን እንደግፋለን። የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ሕዝቧ አስቸጋሪ ጊዜያትን ያሳለፉ በመሆኑ፣ በዓለም ላይ ሰላም እንዲሰፍን ትፈልጋለች። ለዚያ ግብ ደግሞ መሥራት ይኖርብናል። ወደ ውይይት እና ድርድር ጠረጴዛ መቅረብ እና ከፍተኛ የሰው ሕይወት መጥፋትና የመሠረተ ልማት ውድመት እያስከተሉ ያሉ ጥቃቶችን በቀጥታ መፍታት አስፈላጊ መሆኑን እናምናለን።" ሲሉ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፋውስቲን አርካንጅ ቱዋዴራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፋውስቲን-አርቻንጅ ቱዋዴራ ስለ ቀጠናው ሰላም እና ስለ ሩሲያ ድጋፍ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ያደረጉት ልዩ ቆይታ፣ በእስራኤል፣ አሜሪካ እና ኢራን መካከል ስላለው ፍጥጫ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኙ ሞሃመድ ሲራጅ የሚሰጡት ሰፊ ማብራሪያ። የሀገርን ሉዓላዊነት ያስከበረው ታሪካዊው የካራማራ ድል ለኢትዮጵያ አንድነት ያለውን ፋይዳ የቆሮማሽ ማህበር ሰብሳቢ አቶ ደቻሳ አንገቻ ጋር ያደረግነው ውይይት ተካትተዋል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
-
73
ሉዓላዊነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፦ በታለመ ግድያ የታወከው የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም
“ ከ1945 ጀምሮ ለዓለም መረጋጋት መሠረት የነበሩት ዘርፈ-ብዙ ሥርዓቶችና ስምምነቶች እየፈራረሱ ባሉበት ዓለም ውስጥ እንገኛለን። እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ የፈጸሙት ድርጊት በምንም መመዘኛ በሕግ የተደገፈ አይደለም፤ ይልቁንም የተባበሩት መንግሥታትን ቻርተር የጣሰ፣[...] ዲፕሎማሲን ለወታደራዊ ጥቃት እንደ መሸፈኛ መጠቀም፣ ለወደፊት ዓለም አቀፍ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነውን እምነት ለዘለቄታው ያጠፋዋል።” ሲሉ በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ተመራማሪ እና ተንታኝ የሆኑት ራሺድ አብዲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ ስለመጣው ውጥረት በአፍሪካ ቀንድ እና በመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ተመራማሪ እና ተንታኝ ራሺድ አብዲ ጋር በመሆን ስለ ዓለም አቀፍ ሕግ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመጀመሪያው ክፍል በሰፊው እንዳስሳለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የሚዲያ ባለሙያ እና የድምፅ ተዋናይ ኮስሞ ሚለር ጋር ስለ ቋንቋ፣ ስለ ቅኝ ግዛት እና ስለ አፍሪካ ልማት ጥልቅ እንዲሁም የጂኦፖለቲካ ጉዳዮችን ከባህላዊ ሉዓላዊነት ጋር አጣምረን እንዳስሳለን።ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
72
ከባዕድ ትርክት ወደ አፍሪካዊ እውነት፦ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ የአንድ ዓመት ጉዞ
“አፍሪካውያን የራሳቸውን ታሪክ በራሳቸው መንገድ እና አተራረክ ዘዬ ማቅረብ አለባቸው የሚል ትልቅ የፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ አለ። […] ያ ትግል ረጅም ዓመት ሄዷል፣ ግን ያን ያህል ውጤታማ መሆን አልቻለም። ውጤታማ እንዳይሆን ያደረገው ትልቁ ምክንያት የመረጃ ክፍተት ነው። መረጃ ደግሞ ኃይል መሆኑን የምታውቀው ቢያንስ የራስህ ባይሆን እንኳን አንተ የምትቆጣጠረው ሚዲያ ወይም በአንተ መጫወቻ ሜዳ ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን ነው።” ሲል በስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮ አዘጋጅ እና አቅራቢ የሆነው ዐብይ ሀብታሙ ተናግሯል። በዚህኛው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍቶ ስርጭት የጀመረበትን 1ኛ ዓመት አስመልክቶ የመጀመሪያው ዓመት የሥራ መልኮቻችን ላይ ቅኝት አድርገናል። ለዚህም በኢትዮጵያ የስፑትኒክ አፍሪካ አዘጋጅ እና አቅራቢ ከዐብይ ሀብታሙ እና ዘላለም ደምሴ ጋር ቆይታ አድርገናል። “እንደ ስፑትኒክ ያሉ ትልቅ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን፣ ተሰሚነት ያላቸው መገናኛ ብዙሃን በቋንቋችንም፣ በእንግሊዝኛውም ደግሞ ስራ መጀመራቸው አፍሪካውያን ስለ አፍሪካ፣ ስለ ራሳችን ያለንን ግምት ከመቀየር አንጻር በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።” ሲል በስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቢሮአዘጋጅ እና አቅራቢ የሆነው ዘላለም ደምሴ አክሏል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
-
71
የአፍሪካ ድምፅ በአፍሪካዊያን፦ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ !
“ስፑትኒክን በተመለከተ ፣ እኛ አማራጭን ብቻ ነው የምናቀርበው። የተለየ የዕይታ ነጥብ እያቀረብን ነው፤ እንዲሁም ለደቡባዊው ዓለም አገራት ድምፅ ለመስጠት እየሞከርን ነው። ስለዚህ፣ እኛ ምንም ዓይነት ነገር በማንም ላይ እየጫንን አይደለም። እኛ ያልተነገሩትን ነገሮች እየተናገርን ነው፤ አድማጮቻችን እና አንባቢዎቻችን ደግሞ የራሳቸውን መደምደሚያ እንዲያሳርፉ እንጋብዛለን። ስለዚህ፣ ለደቡባዊው ዓለም አገራት በመገናኛ ብዙኃን ዓለም ውስጥ እንዲህ ዓይነት አማራጭ ማግኘታቸው ትልቅ ዕድል ነው።" ሲሉ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ አሌክሳንደር ሺፒን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍቶ ስርጭት የጀመረበትን 1ኛ ዓመት አስመልክቶ የመጀምሪያው ዓመት የሥራ ሂድት እና አጠቃላይ መልኮችን አስመልክቶ የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ አሌክሳንደር ሺፒን፣ ማኔጂንግ ኤዲተር ፀጋዬ ወንደሰን እንዲሁም አዘጋጅ እና አቅራቢ ከሆነችው ኤደን ተሾመ ጋር ቆይታ አድርገናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
70
የዓድዋ ድል፦ የኢትዮጵያዊያንን የትብብር አቅም የገለጠ የአፍሪካዊያን ኩራት
ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ክብርና ችሎታ ምልክት ሆኗል።[...]ፓን አፍሪካኒስቶች ማንሰራራት የቻሉት የ1896 እ.ኤ.አ የአድዋ ድልን ተከትሎ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያን እንደ ማረጋገጫ ወስደው፣ አፍሪካውያን የአውሮፓን የበላይነትና ቅኝ ግዛት መቋቋም እንደሚችሉ ተመልክተዋል። ሲሉ በወሎ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ባልቻ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ለ130ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለውን የዓድዋ ድል በዓል መነሻ አድርገን ሉዓላዊነትን በሶስት መልኩ ቃኝተነዋል። በቀዳሚነት ኢትዮጵያ በዓድዋ የተቀዳጀችውን ድል መነሻ አድርገን ለአፍሪካ ስላለው ትርጓሜ በወሎ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር አሰፋ ባልቻ ጋር በሰፊው ዳስሰናል። በሁለተኝዉ ክፍል የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት መገለጫ ስለሆነዉ ቋንቋና ሉዓላዊነትም የሚዲያ ባለሙያ እና የድምፅ ተዋናይ ኮስሞ ሚለር ጋር በሁለተኛው ክፍል ቆይታ አድርገናል። በመጨረሻም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ትኩረታችንን አድርገን ከ'ኤአይ' የሚሰጠንን መረጃ ማን ይወስናል ስንል ስንል ለ21ኛው መቶ ክፍለዘመን የአፍሪካ የትርክት መልክ አማራጭ ሀሳቦችን ከዲጂታል አስተዳደርና ትራንስፎርሜሽን ባለሙያው እስክንድር ቸርነት ጋር ፈትሸናልን። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
69
የቤተሰብ ዕቅድ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ከእርዳታ ጥገኝነት ነጻ የማድረግ ጅምር በኢትዮጵያ
“የጤናውን ሴክተር ስንመለከት ጤና ብቻውን በአንድ የሚቆም።[…] የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ 'Health in All Policies' ነው የሚለው። የጤና ፖሊሲዎች በሁሉም ፖሊሲዎች ውስጥ መኖር አለባቸው። ምክንያቱም ግብርና ብንለው፣ ትምህርት ብንል፣ ሁሉም ብንላቸው የጤና ፖሊሲ ከሌላቸው ሙሉ አይሆኑም፤ ምክንያቱም ዋናው ጤና ስለሆነ ማለት ነው።” ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በመጀመሪያው ክፍል በጤና ሚኒስቴር የስነ-ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ እቅድ፣ የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ፕሮግራም ኃላፊ ከሆኑት ዶ/ር አለማየሁ ሁንዱማ ጋር በመሆን መንግስት ከመደበኛ ብሄራዊ በጀቱ ወደ 14 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለፕሮግራሙ በመመደብ ከእርዳታ ጥገኝነት ነጻ የሆነ የጤና ስርዓትን እውን የማድረግ ሂደት እንመለከታለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች እድገት እና እየጨመረ ስለመጣው የቤት ፍላጎት ጉዳይ በሪል ሰቴት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ የማርኬቲንግ ባለሙያ እና አማካሪ ከሆኑት ኢንጂነር ቸርነት መንግስቴ ጋር ያደረግነውን ውይይት አካትተናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
-
68
ዓለምአቀፍ የሬዲዮ ቀን፦ ከሬዲዮ ሞስኮ እስከ ስፑትኒክ የሩሲያ የመረጃ ተደራሽነት በአፍሪካ
ዛሬ አለምዓቀፉ የሬዲዮ ቀን በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። ስፑትኒክ አፍሪካም በአዲስ አበባ ማህበረሰብ ሬዲዮ 99.4 ኢትዮጵያን ፣ አፍሪካን እና መላው ዓለምን የሚዳስሱ ዝግጅቶችን በአማርኛና በእንግሊዝኛ እያቀረበ ይገኛል። ‘’ [...]ስፑትኒክ አፍሪካ በኢትዮጵያ በከፈተው ቢሮ ኢትዮጵያን እና አፍሪካን የሚመጥኑ ጠንካራ ይዘቶችን እየሰራ ነው።[...] የስፑትኒክ ጋዜጠኞችን በደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጥናት ምርምርን ሲያቀርቡ አግኝቻቸው ነበር። ይህ የሩስያን ቀናነትና አብሮ የመስራት ፍላጎት የሚያሳይ ነው።” ሲሉ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዛሬ የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀንን መነሻ በማድረግ ፣ ከሬዲዮ ሞስኮ አእስከ ስፑትኒክ በሚል ርዐእስ አእለቱን አእዘክራለን። ሬዲዮ ከሌሎች የመገናኛ አዉታሮች የተለዩ የሚያደርጉትን ባህሪያትና ስፑትኒክ አፍሪካ በአዲስ አበባ የቅርንጫፍ ቢሮውን መክፈቱ በመረጃ ፍሰት ላይ የሚኖረውን ሚናም እንዳስሳለን።ለዚህም አንጋፋዎቹን ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ባለሙያዎች ተፈሪ ዓለሙ እና ጥበቡ በለጠ ጋር በተጨማሪም ስለ ሬዲዮ ሞስኮ ትዝታቸውን ካካፈሉን ከአቶ ማሞ መንገሻ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
-
67
የኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የመገንባት እቅድ
“ለዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ስንጠቀምባቸው የቆዩትን መረጃዎች (Data) የሀገር በቀል ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም የ-AI ሞዴሎች የሚቀረጹት በሰለጠኑበት መረጃ ልክ ነው። ያ መረጃ በብዛት የመነጨው ከሰሜናዊው የዓለም ክፍል ስለሆነ፣ የሚያንጸባርቀው የእነሱን ማንነት እንጂ የእኛን አይደለም። ስለዚህ በራሳችን መረጃዎች የተደራጀ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሊኖረን ይገባል።” ሲሉ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ የሆኑት ረዳት ፕ/ር አደራጀው ምህረት ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ከሆኑት ከረዳት ፕ/ር አደራጀው ምህረት ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ልዩ የሆነ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም ያላትን እቅድ የምንመለከት ሲሆን፤ በሁለተኛው ክፍልም የ2026ቱ የTenDX አዲስ አበባ ጉባኤ ላይ ተገኝተን ስለ ዲጂታል የክፍያ ስርዓቶች፣ ዲጂታል መታወቂያ እና ፓን-አፍሪካዊ የፋይናንስ መሠረተ ልማቶች በካምፓስ ፕላስ ቴክኖሎጂስ የመካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ም/ል ፕሬዝዳንት እና ም/ል ማኔጂንግ ዳ/ር የሆኑትን አዲል አህመድን እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ የባለድርሻ አካላት ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑትን ሳሚናስ ሰይፉን አነጋግረናቸዋል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
66
የባህል ኃይል፦ ባሕላዊ አመራር፣ ፋሽን እና የአፍሪካ የወደፊት ጉዞ
“የዓለም አቀፍ ሕግ፣ በምዕራባውያን ወገን ሕጎች የሚጥሱትን እንዲታሰሩ የሚያደርግ ነው። አንድ አፍሪካዊ መሪ በፖለቲካዊ መልኩ የአፍሪካን መንገድ ለመከተል ከወሰነ፣ ኢላማ ይደረጋል። በአንተ ላይ መጥፎ የሆኑ ስሞችን በመለጠፍ መገናኛ ብዙኃንን ተጠቅመው ሕዝቡ አንተን በመጥፎ ዓይን እንዲመለከትህ ማድረግ ይጀምራሉ። ይህንንም በአንተ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ ትክክለኛ እንደሆነ ለማስመስል ይጠቀሙበታል። እስካሁንም ያለው አካሄድ ያው ነው።” ሲሉ በጋና ባሕላዊ መሪ እና የ‘ዘ ቴስት ኦፍ አፍሪካ’ ተባባሪ መስራች የሆኑት ቴንጎል ኬፕሌማኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ በጋና ባሕላዊ መሪ እና የ‘ዘ ቴስት ኦፍ አፍሪካ’ ተባባሪ መስራች እና የ‘ካልቸራል ዋንነስ ፌስቲቫል’ አዘጋጅ ቴንጎል ኬፕሌማኒ ጋር በመሆን — በፍጥነት እየተለወጠ ባለው ዓለም ውስጥ የአፍሪካ ወጎች እንዴት አግባብነታቸውን ጠብቀው ሊቀጥሉ እንደሚችሉ እንወያያለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ የ‘አፍሪካ ሞዛይክ’ የፋሽን መድረክን አስታከን ከቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ እና ከታዋቂው ሙዚቀኛና አርቲስት ስለሺ ደምሴ (ጋሼ አበራ ሞላ) ጋር ስለ ባህል ዲፕሎማሲ እና ተያያዥ ጉዳዮች ያደረግነውን ቆይታ አካትተናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
65
የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና የደቡባዊው ዓለም የቴክኖሎጂ ሽግግር
"[ኢትዮጵያ] በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር እንደመሆኗ፣ በአንድ [በጅቡቲ] ወደብ ላይ ጥገኛ መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ አሁን ፍላጎታችንና ጥቅማችን በጣም የተለያየ ነው። በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ወደቦችን መጠቀም፣ መመልከት ወይም መፈለግ እጅግ አስፈላጊ ነው።" ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር የሆኑት አቶ በላይ በየነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በርበራን ከጎበኘ በኋላ፣ የኢትዮጵያን እየተለወጠ የመጣውን የባህር ላይ እና የጂኦ-ፖለቲካ ስትራቴጂ እንመረምራለን። ለዚህም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ አፍሪካ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ መምህር ከሆኑት ከአቶ በላይ በየነ ጋር በዝርዝር እንቃኛለን። በሁለተኛው ክፍል ደግሞ፣ በደቡባዊው ዓለም ወስጥ በመካሄድ ላይ ስላለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (ኢ- ሞቢሊቲ) አብዮት እንዳስሳለን። ለዚህም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የመካኒካል፣ ኬሚካል እና ማቴሪያል ሳይንስ ምህንድስና ኮሌጅ ዲን ከሆኑት ከዶ/ር ሽመልስ ለማ ጋር ቆይታ አድርገናል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
64
ከቅኝ ግዛት እስከ ስልታዊ አጋርነት፡- በዲፕሎማሲው መስክ የቀጠሉ ሁነቶች
የደቡባዊው ዓለም ሀገራት ከምንጊዜውም በላይ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ማጠናከር የግድ የሚላቸው ጊዜ ላይ ደርሰዋል፡፡ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት የማእድን ሀብታቸውን ሲሉ በታዳጊ ሀገራት ላይ ቀጥተኛና ህገወጥ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት መፈጸም ቀጥለዋል፡፡ “ይህ የተመድ ድክመት ነው። ምክንያቱም እነዚህ አገራት በሙሉ፣ ድሃም ይሁኑ ሀብታም፣ ነፃ አገራት ናቸው። አሜሪካ በእነዚህ አገራት ላይ ጥቃት መፈጸም የለባትም። ይህ የኢምፔሪያሊዝም መገለጫ ነው። በመሆኑም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአንድነት ሊቆም እና በነፃና ሉዓላዊ አገራት ላይ የሚፈጸመውን የጥቃት ድርጊት መቃወም አለበት።” ሲሉ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነት ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ዱጋሳ ሙሉጌታ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህ ባለ ሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ ከዶ/ር ዱጋሳ ሙሉጌታ ጋር በመሆን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የ2026 ዓመታዊ ጋዜጣዊ ማብራሪያቸውን መነሻ አድርገን ሞስኮን ወደ ደቡባዊ ዓለም /Global South/ እያደረገች ያለውን ከፍተኛ ትኩረት እንወያያለን። የቢትኮይን ባለሙያ ከሆነው ቃል ካሳ ጋር የቢትኮይን (Bitcoin) ኢንቨስትመንትን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያን ዲጂታልፋይናንስ ትኩረት መነሻ አድርገን ፣ አማራጩ እውነተኛ የፋይናንስ ሉዓላዊነትን ሊያመጣ ይችላልን? የውጭ ምንዛሪ እጥረትንስ ይቀርፋል? በሚሉት ነጥቦች ዙሪያ ያደረግነውን ውይይት በሁለተኛው የዝግጅት ክፍላች ዳስሰነዋል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
-
63
የሉዓላዊነት ጉዞ፦ ኢትዮጵያ በጤና፣ በምግብ እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች እያመጣች ያለችው አዲስ ለውጥ
"የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድኃኒት ባለሥልጣን የደረጃ ሶስት (Maturity Level 3) እውቅናን ማግኘቱ ለሀገሪቱ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው፣ እንዲሁም ለእኛ እንደ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ጨዋታ ቀያሪ ትልቅ ክስተት ነው።[...]የምስክር ወረቀቱን በቀላሉ በመጠቀም በኢትዮጵያ የተመረተን ማንኛውንም ምርት በመላው አፍሪካ አልፎም ከዚያ በላይ ማሰራጨት እንችላለን።" ሲሉ 'ፋርማኮሎጂስት' እና የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በቀዳሚነት ፋርማኮሎጂስት እና የኢትዮጵያ የፋርማሲ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ከዶ/ር ዳንኤል ዋክቶሌ ጋር በኢትዮጵያ የመድኃኒት ዘርፍ መንግስት የገበያውን መጠን እስከ 2030 ድረስ ወደ $3.6 ቢሊዮን ለማሳደግ የሰነቀውን ዕቅድ እንቃኛለን። በመቀጠል የኢትዮጵያን የስንዴ ምርት እድገት ከከፍተኛ የግብርና ተመራማሪዉ ጸደቀ አባተ (ዶ/ር) ጋር እናነሳለን።በመጨረሻም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ከፍተኛ የአቪየሽን ባለሙያ ከሆኑት ከአቶ እንዳለ ተሾመ ጋር ሆነን ቦይንግ ስለ አፍሪካ አቪየሽን ዕድገት ያስቀመጠውን ትንበያ እና የኢትዮጵያ ልዩ ሚና እንመረምራለን። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
Loading similar podcasts...