EPISODE · Dec 11, 2025 · 1H
አማራጭ ሀብት ለአፍሪካ ዕድገት፡ ከባህላዊ የኢንቨስትመንት መንገዶች ባሻገር
from The Rising South
“የአማራጭ ሀብቶች ፣ ለምሳሌ የሰው ካፒታል መረጃ ጠቋሚ ምርታማነት፣ የህዝቡ መጠን እና የኢኮኖሚዎ ስፋት—ተቋማዊ ሁኔታዎችንሊቀይሩ/ሊያስተካክሉ ይችላሉ። ስለዚህ፣ አማራጭ ሀብቶች ልክ እንደ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት በተመሳሳይ መንገድ ተጽዕኖ አያድርባቸውም፡፡” ሲሉ የማኔጅመንትና ኢኮኖሚክስ አማካሪ ሳታ አብርሃም (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በአማራጭ ሀብት ላይ ከሚሰሩ ቀደምት ተመራማሪዎች አንዱ ከሆኑት ሳታ አብርሃም (ዶ/ር) ጋር በመሆን ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ወስጥ የግል ሀብት ፣ ቬንቸር ካፒታል ፣ መሰረተ-ልማት ፣ እና ቋሚ ንብረቶች ኢንቨስትመንት ዙሪያ ያለውን ለውጥ እና እውነታ የምንዳስስ ሲሆን፤ በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ደግሞ በመጀመሪያው የአፍሪካ ኅብረት የዲጂታል ግብርና ጉባኤ ላይ ተገኝተን በአፍሪካ ውስጥ በግብርና ሥራ ፈጣራ ላይ ከተሰማሩት ከዶ/ር ኢንግሪድ ኤፓዛኝ፣ ፑሪቲ ኤኮህ-ኦዴቺኩ እና ባላቂስ ሰላውዲን ኢብራሂም ጋር ስለ ዲጂታል ግብርና ያደረግነው ውይይት ተካትቷል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
Embed this episode
NOW PLAYING
አማራጭ ሀብት ለአፍሪካ ዕድገት፡ ከባህላዊ የኢንቨስትመንት መንገዶች ባሻገር
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.