Skip to content
Excerpt : እና ፥ እየዘነበ ነው . . .  episode artwork

Jul 27, 2021 3 min

Excerpt : እና ፥ እየዘነበ ነው . . .

from Sost kilo Hosted by Leoul Zewelde

ብዙ ግዜ እግሮቼን ይዞ የሚያስቀረኝን ማጥ የማቦካው እኔ ራሴው ነኝ ። ለዚህም ነው ድብርቴን ያመጣው ጭጋጉ ይሁን ጭጋጉ የመጣው በኔ ድብርት እርግጠኛ ያልሆንኩት ። በየግዜው የሚነሱብኝን ወጀቦችን እያሳለፍኩ እቆያለሁ - እኖራለሁ ለማለት እንኳ ትንሽ ይከብደኛል ። በአጭሩ ህይወቴ በረከት ርቋት ድንገት የሚወርድ ሲሳይ መጠበቅ ከጀመርኩ ቆየሁ ። ሰማዩ ገና ማስገምገም ሲጀምር ከጀርባዬ ያለውን መጋረጃ ለሁለት ከፍዬ ወደላይ አንጋጠጥኩ - ዳመናው ፅልመት አዝሏል ። አከታትሎ መብረቅ ወረደ ። ሁሌ አይቶ እንደማያውቅ ያስበረግገኛል ። ፀሃፊዬ " ድምፁ እኮ ዘግይቶ ነው የሚደርሰው ፤ መፍራት ያለብህ ብርሃኑን ነው " ስትለኝ ይሰማኛል ። የያዝኳቸውን ወረቀቶች መሳቢያዬ ውስጥ ሸጉጬ ተነሳሁ - ለፊዚክስ የሚሆን ግዜ አልነበረኝም ። መንገዴን ስጀምር . . . ዣንጥላ የያዙትም መኪናም የሚነዳውም ወራሪ እንደመጣ አይነት እኩል ይሮጣሉ ። ሱቆች የበረንዳ መከለያ ላስቲካቸውን ለመወጠር ይታገላሉ ። የነጎድጓዱን እሩምታና የሰውን ሁካታ ሽሽት የጆሮ ማዳመጫዬን ወትፌ ድምፁን እስከ ገደፉ ጨመርኩ ። በፊት እንዲህ ሲዘንብ - በመስኮቴ መስታወት ላይ ተለጥፈው የሚወርዱ ጠብታዎችን አፍዘውኝ ከእውን አለም እሰለባለሁ ። ከቅጠሎች ላይ ተንሸራተው እቁር ረግረግ ላይ ሲያርፉ የሚፈጠረውን ዜማ በተመስጦ አደምጣለሁ ። አፈር ሲርስና ባክቴሪያዎች ሲዋሰቡ ያለውን ሽታ እየማግኩ በአርምሞ አምማለሁ ። የገረጣው አየር በውን የማላውቃትን ቀይ ልጅ ያስናፍቀኛል ። ምኑን እንደማስብ እንጃ ! ብቻ በሌለ ትዝታ ጭ. ል . ጥ እላለሁ ። በስሱ የጀመረው ካፍያ እየባሰና የአስፋልቱ ክፍተቶች በውሃ እየተሞሉ መጡ ። እየበሰበስኩ ቢሆንም ከአረማመዴ የተጨመረም ሆነ የተቀነሰ ፍጥነት የለም ። የለኮስኩት ሲጋራ ከንፈሬ ላይ በስብሶ ሳያልቅ በፊት አሽቀንጥሬ ጣልኩት ። ዛሬ ግን እንዴት እንደሌላው ግዜ ሮጬ አልተጠለልኩም ? ጭራሽ እንዳበደ ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁና ፊቴን አስጥቼ ዝናቡን እንደአመጣጡ መቀበል ጀመርኩ ። ንፋስ በማይረብሽ ፉጨት አብሮኝ ይሽከረከራል ። ጉንጮቼ ላይ የሚያርፉት ደቃቃ ዘለላዎች እየነጠሩ ይወድቃሉ ። መሃል ጎዳና ላይ ጭንቀቴ እንደእድፍ ከላዬ እየታጠበ ሲፈስና ያልጮሁኳቸው እልፍ ፀሎቶቼ ሲመለሱ ተሰማኝ ። ውሃ እንደተጠማ የበረሃ ሜዳ ረሰረስኩ ፤ ስንጥቆቼ ገጥመው ፍቅር ወደውስጤ ሰረገ ። እንደልጓም ቆልፎ አላላውስ ካለኝ ፍርሃት በነፃነት ስጋፈጥ በጭጋግ ውስጥ ስፈካ ተሰማኝ ። መኖር - ወጀቡን ተሳቀህ ስለማሳለፍ ሳይሆን በዝናቡ ውስጥ እንዴት መደነስ እንዳለብህ ስለመማር ነው ! . . . እንዲሉ ።

Episode details come from the podcast's RSS feed.

Embed this episode

Ready to play

Excerpt : እና ፥ እየዘነበ ነው . . .

0:00 3:06

No transcript yet.

Requests help us decide what to transcribe next.

Frequently asked questions

How long is this episode of Sost kilo?

This episode is 3 minutes long.

When was this Sost kilo episode published?

This episode was published on July 27, 2021.

Can I download this Sost kilo episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.