PODCAST · fiction
Sost kilo
by Leoul Zewelde
Stories.https://linktr.ee/sostkilo
Episodes
-
የራህባን ጭስ
#Spotify #Sostkilo #shortstory
-
ሮዛ ሮዚና
ሮማናት – ናሽናል ካፌ . . . ሮዝ አገሯ ያለ ካፌ ስትቀጥረኝም ሆነ ቀጥራኝ ስትቆይ ለመጀመሪያ ግዜ ነው ። እንደደረስኩ ወፍራም የማሽን ቡና አዝዤ እሱን እየጠጣሁ ጥበቃዬን ጀመርኩ ። ካፌው ውስጥ ዝንቦች እንዳያስቸግሩ በሚል በየጠረጴዛው የሊም ቅጠል ተነጥፏል ። ውስጥ የሚተራመሰውን ሰው ...
-
የመንታ እናት ፖለቲካ !
የ መ ን ታ ፡ እ ና ት ፡ ፖ ለ ቲ ካ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ለማበጠር ጀምራው ከነበር ፀጉሯ ውስጥ እጇን ወትፋ "ዋ………ይ"ብላ ጮኸች ። እሪታዋ ርዝመቱ በመሃል ቅላፄዋ እስኪለዋወጥ ነበር ። ጩኸቷን ተከትሎ ቤቱ ውስጥ ፀውታ (*ፀጥታ + ክውታ) ሰፈነ ። የድንገት ጩኸቷ ከሷ በፊት ሲርገበገቡ የነበሩ ሁለት የመንትዬ እንጥሎችን አርግቧል ። ሣራ ያለግዜ የመጣችባት ፅጌዋ(*ፔሬዷ) ምቾት ነስታት ድምፅ የሚባል ነገር መስማት አስጠልቷታል። አንዴ አግና በለቀቀችው...
-
የአላውያን ሣልዮን | Good Friday
Leoul Zewelde የሮም ወታደሮች እየተዟዟሩ ሶስቱ ዛይሎኖች ላይ ቅናዋት ሲወቅሩ ይታየናል በሩቅ … ከካህናት ዕሠይ ፤ ካይሁድ ጉርምርምታ አልፎ የሚረብሽ የአንዲት ሴት ስቅስቅታ ይሠማናል ከሩቅ … ለተጓዥ አላውያን መንፈቅ ትርዒት ፥ ከሩቅ ለምናየው …የአርብ መንገድ አድክሞን ከመስቀሉ ጀርባ ተጋርደን ለቆምነው … ክርስትና ርዕዮት ነው !
-
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3 | Part II
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች - Message 3 | Part II
-
ዛሬ ፥ ጨረቃዋን አይተሻታል ? ... ፩. አዲስ አበባ ፥ ካምፕ አስመራ
ያልተላኩ አምስት ቴክስቶች ፤ Message 3
-
ኪ ሣ ኬ ሣ ፥ አ ዱ ሬ ን ፡ ቢ ኔ ሳ
ራቢራ ሱራ ነኝ ። ቢራዬን እንደትኩስ ሻይ ...
-
የእውነት እውነት ፥ እወድሻለሁ !
ውብትሽን ከሩቅ ለሚያይ 'ፍዝ' ነው ። ሎሚ እንዳቤዠው ሻይ ፥ ካልቀመሱት የአይን ስህተት ነው ። ይሄን ብዥታ እንደሀቅ ተቀብለው ፥ ይገፉሻል ። ለእኔ ግን ፥ ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም ! የእውነት ነው ። ከማታውቂው አገር ብትኮምሪ ፥ የቤትሽ የመጨረሻ ሰካራም ፥ እኔ ነው ምሆነው ። ትተሽ ብታዘምሪ ፥ ጭራ ልጌ አጅባለው ። ለእኔ ? ጣዕምሽን አውልዬ ለማውቀው ፥ ለሰው ብዬ አይደለም ! ከሰው መጥቶ አይደለም !…
more -
ሽ ፍ ደ ት ፡ በ አ ይ ን ፡ ይ ገ ባ ል ...
የተንጣለለው አስፋልት በሚረግፈው የዳመና ቡትርፍ እየታጠበ ነው ። አቶ 'ሀ' ( ይቅርታ ፤ ስሙን ስለማላውቀው ነው) ጭር ባለው ጎዳና እየተዘነበበት ወደቤቱ ያቀናል ። ተበታትኖ የሚወርደው የጨፈጨፍ ናዳ ሲያርፍ ይዘልና ሌላ ቀድሞ የወረደ ጨፍ እየያዘ ወደዳር ይንቆረቆራል ። ተርታውን ያቀረቀሩት የመንገድ ዳር መብራቶች ገና ሳይመሽ በስህተት ብርሃናቸውን ወልተዋል ...
-
ኦቾሎኒ - አለንጋና ምስር | 1985 ሆላንድ
ለአዳም ረታ - የልደት ማስታወሻ
-
አስኩቲን በትኩሱ:)
የችኮላ ሥራ ሲገጥመኝ ትዝ የምትለኝ ነገር ነች። ቄራ ላይ የሆነ ነው ፥ ያው እንደጨዋታ ። አስኩቲ የሚባል እሳት ሞተረኛ ...
-
ከ ሀ - ፐ ስንት ኪሎሜትር ነው ?
Excerpt : ድምቡሎ ጎዳና | Short story.
-
አንቺ የወደድሽው ፥ እኔ የማልሆነው •••
ጀግና የወደድሽ ሰሞን ፤ ጀግና አሳድዳለው ። ጎሽ ገድዬ ኮልባ ሎቲ እቀርፃለው ። ከነብር ገላ ላይ ለአንገት በርኖስ እላጫለሁ •••
-
ብዥ
በመሃል እራት አለመብላቴ ትዝ ብሎኝ ደሞ በባዶ ሆዴ ተከዝኩ ። ችግሮቼ በጣም ስለሚወዱኝ ብቻዬን አይተውኝም ፥ አንዱ እንኳ ሲሄድ አንዱን ተክቶ ነው ....
-
ዝንየት ሦስት : ተፃብዖ (ሰማያዊና ቀይ ኮላዥ)
ይሄኔ ነው ትርዒቱ የተለኮሰው ። መጀመሪያ የበረንዳው አምፖል ላምባ እንደጨረሰ ኩራዝ ጥር ጥር ሲል ቆይቶ ዚግዛጉ እስኪታይ ድረስ ከሰመ ። ተደፍቶ በስንፍናዬ ያልወለወልኩት ውሃን ወለሉ ሲመጠውና ጠቦ ጠቦ ሲጠፋ አየሁ ። በድንጋጤ እግሮቼን ወንበሬ ላይ ሰበሰብኩ ። የግቢያችን መታጠፊያ ሾላ ዛፍ ላይ የተከመሩ ወፎች ተበተኑ ። እነሱን ተከትለው የዛፉ ፍሬዎች ሿ ብለው ረገፉ ....
-
ዝንየት ሁለት - ምርጫ ቀረበልኝ ፤ ከእውነት እና ፍቅር ?
በሩ ሁለቴ ተንኳኳ ። ስከፍት የበሩን የውጭ ማዕዘን ተደግፋ ቆማለች ። ሰላምታ ሳትሰጠኝ አልፋኝ ገባችና ዘግቼው ወደሷ እስክዞር ጠብቃ " አርግዣለሁ " አለቺኝ ። ደንግጬ አየኌት ....
-
ዝንየት አንድ ፤ EP01
የለበሰችው እጅጌ ሙሉ ፒትልስ ወልቆ ምኔ እርቃኗን እንደቀረች አታውቅም ። የተጨመታተረው አንሶላው ሀሩር ገላዋን እየነካ ሲቆጠቁጣት ገልፍፋ ጣለችው ....
-
ለምን ግን ትልቅ ሆነ ?
ከትናንት ወዲያ ማታ ለት እናቴ እሪሪ ብላ እያለቀሰች ገረፈቺኝ ፤ እያነቡ እስክስታ ነገር ። ከደቂቃ በፊት ( ደብተሬ ላይ ጭረት እስካይና እስክጠይቃት) አገር ጎረቤት ሰላም ነው ብለን ስለ ሙሉ ቁጥሮች ተካፋይ ስታስረዳኝ ነበር ። ድንገት ተነስታ ጫማዋን አውልቃ አናት አናቴን እየጠፈጠች ብላ ለአገላጋዮቼ ታሳጣኛለች ፤ ሁለተኛ በደል ። ባህሪዋ ለማንም ግራ የሚገባ አይነት ነው ። እስኪ ልፈትናት ብዬ ሁለት ቀን የሚያስቅ ቀልድ ባወራት ራሱ ትንሽ ፈገግ ሳትል ወደ…
more -
#saynotowar
... ረጅም የስደት ሰልፍ ፥ ሰሌን አናቷ ላይ ጠቅልላ የምትጓዝ እናት ፥ የታረዙ ብላቴኖች ፥ የተደፈሩ መበለት ፥ የተገፈፉ ክብሮች ፥ የከተማ ምሽጎች ፥ የተበሳሱ መስኮቶች ፥ የሚነዱ ቲያትር ቤቶች ፥ ከሰማይ የሚዘንቡ አረሮች ፥ በየቀጠናው የተማገዱ ጎረምሶች ፥ ባንጋ የቀላቸው አናቶች ፥ የሰቀቀን እሪታዎች ፥ ጆፌ የሚዞረው አንገት ፥ የልጁን ሬሳ የሚያናግር አባት ፥ ረጅም የእሾህ አጥር ፥ የስጋት ድንኳኖች ፥ ፈንጂ ዶሿቸው የሚደሁ ገላዎች ፥ እሳት አከፋፋይ…
more -
ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል !
ሲመሽ – ፊት ላይ የሚለሰልስ ብርትኳናማ የፀሃይ ጨረር ሲፈናጠቅ – ከመስጂድ ሚናር የመግሪብ አዛን ሲሰማ – ህዝቤ ስራ ያንዠረገገው ሚስቶ ፊቱን ይዞ ወደቤቱ ሰከም ሰከም ሲል – የትራፊክና የፍሬቻ መብራቶች መድመቅ ሲጀምሩ – የእራት ወጥ ጢሶች ከየኩሽናው ወደሰማይ ሲወጡ . . . ሲመሽ ፤ ሲመሽ . . . ትዝ ይለኛል . . . !
-
ቻው ፡ ቻው | ጉራማይሌ መፅሐፍ
እንደዛ ነው የሚያደርጉት ፤ ይሄዳሉ ። ምንም ሳይሉህ ይሄዳሉ ። እንደጨረቃ ሙላታቸው ይጎድላል - ይገምሳል - ይቀጥኑ ይቀጥኑና - በሆነ ቀን ቀና ስትል የሉም ። ለመከተያ እንኳ ዳና ሳይተውልህ - ልክ እንደ ወቅቶች ፤ እንዳምናዎች ፤ እንደትናንቶች ... ሄድን ሳይሉ ፥ ፍውው …! በዳ'ባድመ መሐል ጥለውህ ሄደውም እንዳልረሣሀቸው ማወቅ ይፈልጋሉ ። ይሄ መሻት እያደር ሲሞረሙራቸው ረፈዶ ከባቸ በኋላ 'ቻው' ይሉሃል ። ከሄዱ ከምናምን አመታት በኋላ አተኩሰው…
more -
የተሸጠ ነብሥ ፥ አይመለስም•••
ነብሴን በገዙኝ ማግስት የፀሓይን ሞት አረዱኝ ። በከባድ ምጥ ማለፏን እንደሰማሁ በዛለ ጀምበር ወደ ለቅሶው ሄድኩ። መቃብሯ የጀበል ቓፍ (*የምድር ጠርዝ) ኮረብቶች ላይ ነው ።ለቀሥተኛው እየተነዳዳ ወደ ቀብሩ ይግተለተላል። እንደህፃን እግር እየተከተልኩ መጓዝ ጀመርኩ። በገፍ ከሚጋዘዉ ለቀስተኛ እንባ የሚወጣኝ አንድ እኔ ነኝ ። ሌሎቹ የአይን መቅደሳቸው ተገልብጦ ከነጩ መቃድ የጠለሸ ደም ይፈሳል ። ዶቃ ብሌናቸው በቦታው የለም ። ወዮታቸውን ባልሰማም ከደረታቸው የሚነሳ...
-
የመጨረሻዋ እራት
የተለያየነው የተገናኘን 'ለት ነው ። እንዲህ እልህ ፍቅራችንን ሳይወርስ በፊት አንዳችን የአንዳችን ደቅ ነበርን ። አሁን በነብስም በስጋም ተለያይተናል ። ሰው ስለይ ጎበዝ እንደሆንኩ እነግራት ነበር ። የትናንት እንጥፍጣፊ ውስጤ አላስቀርም ። ክፉንም ደግ ጠጠር እንደሞላው አቁፋዳ እንዲረሳ አድርጌ ከባህር እሰደዋለው ። አሁንም የሆነው እንደዛ ነው ። ታሪካችን እንደተቋጠረ ቁልቁል ሰምጧል ። ትናንት ሲመሽ እንደሁሌው ጣቶቼን ይዛ አልፀለየችም ። ይልቁን አይኖቼ…
more -
ባለኮኮቡ ፓስቲኒ !
የዛሬ ሃያ ዓመት ገደማ ፤ በሆነ በማይታወሰኝ ቀን ከእንቅልፌ ተነስቼ ስንገላጀጅ የግንፍል ሾርባ ሽታ አፍንጫዬን ሰርስሮ ገባ ። ቅንድቦቼን በፍትጊያ አላቅቄ አነፈነፍኩ ' የፈጣሪ ያለህ ፓስቲኒ ነው ። ' ከስጋ ቀጥሎ የምር የምጠላውና - የሚጠላኝ መብል ፓስቲኒ ነው ። የዶሮ መረቅ ቢገባበትማ ራሴን ሲጥ አርጌ የማጠፋ ይመስለኛል ። ሰባት ዓመቴን ልደፍን የቀሩኝ ቀናት ቢሆንም ዛሬም እናቴ ያለሱ ቁርስ ያለ አይመስላትም ። አሰራሩ ቀላል ሆኖ ይሁን ቶሎ ስለሚደርስ እንጃ...
-
It's Christmas •••
ፅድ አናት ላይ - ሽልም የኮኮብ ዕድ ሳይ - በዝንፍንፍ ቅርንጫፍ የተጥመለመለ ሲባጎ ብልጭ - ድርግም ሲል - የአበርክቶ ሙዳይ ዙሪያው ሲከመር - ዜማ ሲናኝ ፥ በዓመቱ ኦሜጋ ሁሉም ወደልጅነቱ ሲሰበሰብ - በቀለም ያሸበረቁ ህፃናት ተሰብስበው ሲዘምሩ - ኩርሽም ከረሜላዎች አፋቸው ላይ እየሟሟ ሲወልል - ሞሳነት ፍፅምና መሆኑን አምነው ፥ አዛውንቶች በልጆች ሲመረቁ ፥ የበረዶ ጥጥ ብናኞችን አሳበው መላዕክት ሰብ'ን ሲስሙ - የከተማው ካቴድራሎች ስንጉሱ ብስራት ሲደውሉ…
more -
አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ፣ ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ?
Leoul zewelde | Podcaster : Yeab Dems ምክንያት ይሰጡት እንጂ ፥ ሞት አይቀርም ። ተዘጋጅተው አይጠብቁት ነገር ደግLምክንያትዳ እንጂ ሙሽራ አይደለም ። በጦርነት ግፎች እንደሚሞት ሁሉ በሰላም ውስጥ ተኹኖም ይሞታል ። በረሃብ አረንቋ እንደሚሞት ፥ በጥጋብና አለቅጥ ውፍረትም ይሞታል ። ኤሊያሶች አይደለን አንዳናርግ ፥ ሮሙለስ አይደለን አንሠወርም ። ለማን እንደራራው - ለማን እንደሳሳው ይተወናል ? በአንድ ወቅት የሸዋረጋ ምኒሊክ ፥ የንጉሥ…
more -
የ አ ረ መ ኔ ፡ ክ ር ስ ት ያ ኖ ች ፡ ዘ ር ፡ ማ ጥ ፋ ት
በመካከለኛው ዘመን ፥ አውሮጳ ግሪጎሪ ፱ኛ የተባለ ድመት ጠል ጳጳስ ትቀባለች ። ይህ እብሪተኛ ሰው በትረ ሙሴውን በጨበጠ ማግስት በፀሊም ድመቶች ላይ የዘር ማጥፋት (*Pogrom) አወጀ ። ይሄ አሰቃቂ የእልቂት አዋጅ በድመታውያን ታሪክ በክርስትያኖች የተፈፀመባቸው ትልቁ በደል ነው ። ነገሩ የሆነው እንዲህ ነው ። ተራማጅ እንደሆነ በአንደበቱ የሚናገረው ጳጳስ የጵጵስና ማዕረጉን ያገኘው በልጅ እግሩ በሰማንያ ዕድሜው ነበር ። መንበሩን እንደተቀበለም እረፍት አጥቶ...
-
የክብ መጨረሻ | Book: ጉራማይሌ
የክብ መጨረሻ ፥ መጀመሪያው ነው ።
-
ያን ቀን ባታቆላምጪኝሥ? | ያልተላኩ አምስት መልዕክቶች ፥ መልዕክት - 2
ያ ን ፡ ቀ ን ፥ ባ ታ ቆ ላ ም ጪ ኝ ስ ? [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ከወፍራም ብርጭቆ ላይ እያበረደች የምትቀምሰው ወተት የከንፈሯን ዳር በስልባቦት ይኩላል ። የአፏን ወተት ለመግፈፍ እጄን ሰድጄ ግልፋፊውን በጣቴ አስቀረሁ ። ያስቀረሁትን ቀመስኩ ። የላስኩትን ኬሚስትሪ ጣዕም ለማስረዳት ይቸግራል ። ሀይድሮጅን ደርድረው በቦንድ ቢስሉት ዘርፉ ከአሮጌ ዋርካ ይገዝፋል። ቤሎንዥ ፥ ዛሬ ንጋት ላይ ከፓሪስ-ቻርል የገባች ነው ። ስለሚደክም ፥ ችላ የምትመጣም...
-
ች ግ ራ ች ን ፡ ም ን ፡ ነ በ ር ?
ሌላ ያልነገርኩሽ ፥ የልደትሽ ቀን አበባ ገዝቼ ነበር ። አዎ ! እኔ ። የሚገርምሽ ባገሩ እንደጠፋ ሁሉ የትናየት ሄጄ መሰለሽ ? መጨረሻ ላይ ወሰን ምናምን እሚሉት ሰፈር ትንሽዬ ኪዮስክ ውስጥ ትልቅ መቀስ የያዘች ሻጭ አየሁ ፤ ፈንታቸው መርገፍ የሆኑ ቅጠሎችን እየከረከመች። እንዲሁ ልጅ ሳለሁ ፥ ከትምህርት መልስ ሙሽራ የሚሉትን አበባ ከሰው አፀድ ቀጥፌ ወደቤቴ እሮጥልሻለሁ ። ቤት ልደርስ 'ከባቢ እጄ ከአበባው ተሻሽቶ ኖሮ ፥ ወየበ ። ከቆረጡት ኋላ ቶሎ የሚሞት…
more -
Intala mootii
አባት ሆይ … ! ፀልዬ አላውቅም - ብዙ እንዳትታዘበኝ ፤ ዛሬን ብቻ… ጆሮ ዳባ ሳትል … ለሥጋዬ ውሉድ ፥ አንዲት ማቲ ዋጀኝ ። 'ሴት' ሆና የማምናት ፤ ካለ ሚስት አለናት ፥ አባት 'ምሆናት ። አንዲት ልዕልት ማቲ ሳይጋሩኝ የምወዳት - ሳትጋራ የምትወደኝ አቤቱ - በረቂዮትህ ዋጀኝ ። ጡት ብነሳ እንደማልጋ ላም ባላግት ፥ ወተት ባላደማም ጀባ'ኝ እንጂ ፥ እንደ'ዶሮ ጭሬ አፀድቃታለው ህይወቴ የሷ መንግስት ነው ። አባት ሆይ … ፀልዬ አላውቅም - ብዙ እንዳትታዘበኝ…
more -
ዝ ም ታ ህ ን ፡ ማ ረ ኝ
በያንዳንዱ የእምነት ክሬ እንደሹራብ ተተርትሬ እንዳልጣፍ እንዳልሰፋ ሆኛለው የቀረኝ ጨርቅ ከቅዳጄ ያነሰ ነው ። የሲዖል መልህቅ ከግሬ ታስሯል እፍግ ሰንሰለቱ እሄድኩት ድረስ ይረዝማል ቁርጭሚቴ ካልቦ ያለረፍት ይንቋቋል ህልው ምልክቴ ጠፍረ ባርያ ሆኗል ። * * * ቀደም . . .በሌት ግርማ ታውሬ ስቀይርህ ሳፈስህ ከደምስሬ በፋኑዔል ክንፍ ሰበዝ ደምቀለም ነክሬ ነብሴን ላውሬ ስቤዥ ዝም ብለኸኛል ! በካሚዮን ከሚንቦገቦገው በጥፍሮቹ ምድርን ቧጦ ከከበበው አይሆኑ ውዬ...
-
Excerpt : እና ፥ እየዘነበ ነው . . .
ብዙ ግዜ እግሮቼን ይዞ የሚያስቀረኝን ማጥ የማቦካው እኔ ራሴው ነኝ ። ለዚህም ነው ድብርቴን ያመጣው ጭጋጉ ይሁን ጭጋጉ የመጣው በኔ ድብርት እርግጠኛ ያልሆንኩት ። በየግዜው የሚነሱብኝን ወጀቦችን እያሳለፍኩ እቆያለሁ - እኖራለሁ ለማለት እንኳ ትንሽ ይከብደኛል ። በአጭሩ ህይወቴ በረከት ርቋት ድንገት የሚወርድ ሲሳይ መጠበቅ ከጀመርኩ ቆየሁ ። ሰማዩ ገና ማስገምገም ሲጀምር ከጀርባዬ ያለውን መጋረጃ ለሁለት ከፍዬ ወደላይ አንጋጠጥኩ - ዳመናው ፅልመት አዝሏል ።…
more -
'ወድሃለሁ ስትይ - ስሜቱን ግን ታውቂዋለሽ ?
. . . ምልዓተዓለም ፀጥ እንደሚል ፤ ልቤ የምር እንደምትታፈን ፤ እግሬ እንደሚቀዳደም ፤ ብሌኖቼ እንደሚሰፉ ፤ ሳይታዘዝ ጉንጬ እንደሚፈግግ ፤ እየሄድኩ መቆም እንደሚያምረኝ ፤ እየቆምኩ መሄድ እንደሚያሰኘኝ ። ዝለል ዝለል እንደሚለኝ ፤ ሸራ ጫማዬን ፈትቼ እንደማስር ፤ ስልኬን አውጥቼ ሳልደውል መልሼ እንደምከተው ፤ ሽቶሽ ከየትም እንደሚሸተኝ ፤ የት መሄዱን ሳላውቅ ታክሲ እንደምሳፈር ፤ በውጥንቅጥ መሀል አንቺን ብቻ እንደማስብ ፤ የምጠላው ሙዚቃ እንደሚመስጠኝ ፤...
-
ለመውደቅ ግን ተሥፋ አለኝ •
አንድ ልጇ ዱርዬ ሆኖ እንዳሸነፋት እናት … በካር ማህፀኗ ሌላ ዘር ሳይዝ … እሱኑ ስትል አሳድጋ… ሲያፄም ግዜ ከእጇ እንደወጣ… ደምላቧ ከንትቶ የምትኖርለት ሌላ ምክንያት እንዳጣች … ብዙ ብዙ ሄዶ እግዜርን ከቦታው እንዳጣ ቄስ … እድሜውን ሙሉ የቀራቸው መፃህፍት እርባን እንዳጡበት … ረፍዶ ከመመለስና ፣ ተሳስቶም ከመሄድ ምርጫ እንዳጣ … በሁለት የቂጡ ጉንጮች ሁለት ወንበር ላይ እንደተቀመጠ … … ተሥፋ አጥቻለው … አሳዳሪው አረጀህ ብሎ እንዳባረረው ውሻ ። እድሜ...
-
ጭንቀቴ መች ገባሽ
…ጭንቀቴ… ድር እንዳጠመደው ዝንብ ነው ። ሸረሪቷ ካሁን አሁን መጣች እያለ እንደሚሳቀቅ … ክንፉን እያማታ… የትም እንደማይፈናፈን… …ጭንቀቴ…ለወር ታህል ቋጥራ እንደሚሾትልባት ነብሰጡር ነው ። ማህፀኗ አልረጋ እንዳላት … ዘጠኝ ወር ርቆ … የምልጃዋን ማርያም … ማርያም እንደምትል … ጭንቀቴ…ከእናት አባቱ ጥል አምልጦ እንደወጣ ህፃን ነው ። … የሚሮጥ መድረሻ የሌለው… ልጋጉን እየሳበ በለንባዳ አፉ እንደሚያለቅስ … …ጭንቀቴ … ፈረሰኞች በሌት መጥተው ጎተራውን...
-
•••ሥትናፍቂኝ
ስ ት ና ፍ ቂ ኝ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ስትናፍቂኝ … ባሏ ለዕድሜ ይፍታሕ ወህኒ እንደተወረወረባት ሴት ነው ። መልሳ ላታገኘው ነገር እሁድን እየጠበቀች እንደምትጠይቀው … ስትናፍቂኝ … ሲዖል ተኮራምቶ ገነትን እንደሚያልም ሠይጣን ነው ። ምህረት ሱሚ ሆኖበት በልቡ ማብከሪያ እንደሚለምን ። ጥፍሮቹን ቢከረክም'ም ርህራሄ ተነፍጎት ምናልባትን እንደያዘ… ስትናፍቂኝ … በምናብሽ የሚሄድ አስፋልት ሣይና በዛ ላይ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዝ ከንቱ ደሞ አስቢ ።…
more
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
Loading similar podcasts...