EPISODE · Sep 23, 2025 · 1H
ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኒውክሌር ፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ የመገንባት ውጥን
from Sovereignty Sources
“ለሀገር ልማትና ምጣኔ ሐብት ዕድገት፣ አስተማማኝ ኢነርጂ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህ፣ ሌሎች ምንጮች ላይ ጥገኛ ያልሆነ፣ የተረጋጋና አስተማማኝ የኢነርጂ የኃይል ምንጭ የሚሆን ፓወር ፕላንት መገንባቱ ጠቃሚ ነው '' ሲሉ የኒውክሌር ሶሳይት ኦፍ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እምሻው ዳምጠው ተናግረዋል። የኮይሻ ሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር አባይነህ ጌትነት በበኩላቸው፡ - “ኢትዮጵያ አሁን ላይ ቀጠናው ለማስተሳሰር በብርቱ እየሰራች ናት። እስካሁን ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል እያስገቡ ነው። ወደ ታንዛንያም ለመላክ የስምምነት እና ሌሎች ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ'' ብለዋል። ኢትዮጵያ የህዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት በቅርቡ ስራ እንደምታስጀምር ከሰሞኑ ይፋ አድርጋለች። የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራምም ይህን መረጃን መሠረት አድርጎ በሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ እና የሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ግንባታ ዙሪያ ለመወያየት የኒውክሌር ሶሳይቲ ኦፍ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እምሻው ዳምጠውን እና የኮይሻ ሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር አባይነህ ጌትነትን ጋብዟቸዋል። ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
NOW PLAYING
ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኒውክሌር ፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ የመገንባት ውጥን
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.