EPISODE · Dec 17, 2025 · 1H
ከስትራተጂ እስከ ሉዓላዊነት የዘለቀው የአፍሪካ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ጉዞ
from Sovereignty Sources
''መሠረታዊው መልዕክት፣ የሠው ሠራሽ አስተውህሎት በአፍሪካ አህጉር ውስጥ በአፍሪካዊያን ለአፍሪካዊያን መገንባት ይኖርበታል የሚል መሆን አለበት — ለአካባቢያው ችግሮችም በሀገር በቀል እውቀቶች ነው መፍትሔ መሠጠት ያለበት። ስለዚህ ሉዓላዊነት የውይይቱ ማዕከላዊ ነጥብ ይሆናል ማለት ነው'' ሲሉ በኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የሠው ሠራሽ አስተውህሎት ባለሙያው ዮናስ ገብረሚካኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።በሁለት ዐበይት ሀሳቦች ዙሪያ በምንወያይበት የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም፣ በመጀመሪያው ክፍል በአፍሪካ አህጉር ተስፋ ሰጪ ምልክቶችን እያሳየ የመጣው የሠው ሠራሽ አስተውሎት ዘርፍ የበለጠ እንዲጎለብት ደግሞ ከስትራቴጂ ወደ ሉዓላዊነት ማሸጋገርን በተመለከተ በኢመርጂንግ ኢንስቲትዩት የሠው ሠራሽ አስተውሎት ባለሙያው ዮናስ ገብረሚካኤል ጋር ተወያይተናል። ደቡብ አፍሪካ በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ ያላትን ቁልፍ ሚና በሚመለከት ከደቡብ አፍሪካ የግብርና ኢኒሼቲቭ ፕሬዝዳንት ቲዮ ደ ጃገር (ዶ/ር) ጋር ያደረገነው ውይይትም በሁለተኛው ክፍል የምንቃኘው የፕሮግራሙ አካል ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
NOW PLAYING
ከስትራተጂ እስከ ሉዓላዊነት የዘለቀው የአፍሪካ የሠው ሰራሽ አስተውህሎት ጉዞ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.