ሉዓላዊነት በተግባር፡ ከዓለም አቀፍ አጋርነት እስከ አፍሪካ የጤና ነፃነት episode artwork

EPISODE · Jun 23, 2026 · 1H

ሉዓላዊነት በተግባር፡ ከዓለም አቀፍ አጋርነት እስከ አፍሪካ የጤና ነፃነት

from The Rising South

“ከብሪክስ  አንጻር ሲታይ፣ ኢትዮጵያንና ጥቂት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ያካተተ ዘርፈ-ብዙ ገጽታ አለው። ይህ ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት ራሱ የአፍሪካ-ሩሲያን ግንኙነት ለማጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን፣ ይህም የደቡብ-ደቡብ ትብብር  ዋነኛ ምሰሶ ነው። እንዲሁም ይህ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ነው። ይህ ግንኙነት እየሰፋ የመጣ መስክ ያለው ሲሆን፣ ለሁለቱም ወገኖች ማለትም ለሩሲያ ፌዴሬሽን እና ለአፍሪካ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው።” ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህ የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት በፍጥነት እየተለዋወጠ ባለው የዓለም ሥርዓት ውስጥ የአፍሪካን ድርሻ የሚዳስስ ጠንካራ የሁለት ክፍል ውይይት ይዘንላችሁ ቀርበናል። በክፍል አንድ የፖለቲካ፣ የደህንነት፣ የኢኮኖሚ እና የሰብዓዊ ግንኙነቶችን ትብብር የሚቀርፀውን የሩሲያ–አፍሪካ አጋርነት መድረክ የድርጊት መርሃ ግብር (2023–2026) ከአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር እንመረምራለን። በክፍል ሁለት፡ በአዲስ አበባ (መጋቢት 18–19 ቀን 2018 ዓ.ም) በተካሄደው 62ኛው የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ በመገኘት፣ የአፍሪካን የጤና ስርዓት ከጥገኝነት ለማላቀቅና ራስን ለመቻል የሚደረገውን አስቸኳይ ጥረት ከፕሮፌሰር ጆን ዌሩ፣ የክሊኒካዊ ጉዳዮች ባለሙያ፣ ከዶ/ር ሙባረክ ሸምሱ፣ የህብረተሰብ ጤና ስፔሻሊስት እንዲሁም ከቤተልሄም በቃሉ፣ የ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪ ጋር እንቃኛለን። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ 

Episode metadata supplied by the publisher feed · Published Jun 23, 2026

Embed this episode

NOW PLAYING

ሉዓላዊነት በተግባር፡ ከዓለም አቀፍ አጋርነት እስከ አፍሪካ የጤና ነፃነት

0:00 1:00:00

No transcript for this episode yet

We transcribe on demand. Request one and we'll notify you when it's ready — usually under 10 minutes.

No similar episodes found.

No similar podcasts found.

Frequently Asked Questions

How long is this episode of The Rising South?

This episode is 1 hour and 0 minutes long.

When was this The Rising South episode published?

This episode was published on June 23, 2026.

Can I download this The Rising South episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.
URL copied to clipboard!