ኢናብ ቴክ ክፍል 45 - ቪፒኤን ምንድን ነው?
from ENAB TECH PODCAST
በዚህ ክፍል፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሺዎ በአዲሱ ቨርዥን ስላሻሻላቸው ነገሮች እና ጉግል ድራይቭ በቀድሞ ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ላይ መስራት ስለማቆሙ የሚሉትን እናነሳሳለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት ስለቪፒኤን ምንነትና ከቪፒኤን አፕሊኬሽኖች ስለአንዱ አስተዋውቃችኋለሁ። በመሰረታዊ ክፍል፣ ስለጃውስ ከርሰሮች ቀሪ አጠቃቀም እንመለከታለን። በአድማጮች አስተያየት፣ ስለማይክሮሶፍት ወርድ፣ ስለኤምፒ3 ዳይሬክት ከት እና ሌሎችም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ፣ የድምጽ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮቼን እንዳውቅ ሰርቬይ ልትሞሉልኝ ትችላላችሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሱትን ጂሺዎ ትልቁን ከዚህ፣ ጂሺዎ ትንሹን ከዚህ ፕሮቶን ቪፒኤንን እዚህ ያውርዱ።
Embed this episode
No transcript yet.