PODCAST · news
ENAB TECH PODCAST
by Abate Tsegaye
በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።
Episodes
-
ኢናብ ቴክ - በቴሌብር ጉዳዮችን መፈጸም
በዝግጅቱ ቀዳሚ ክፍል የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ከስክሪናችሁ ኬብል የሚወጣን ጨረር በመመልከት ብቻ ስክሪን ላይ ያለውን ጽሁፍ መለየት ስለመቻሉ፤ እንዲሁም ጉግል ሰርች ህገወጥ ሞኖፖሊ ነው ተብሎ የተፈረደበት ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ መጨረሻ ክፍል፣ በቴሌብር ገንዘብ ማስተላለፍን ጨምሮ አንዳንድ ጉዳዮችን እንዴት እንደምንፈጽም በተግባር እንቃኛለን። ከአድማጮች ጥያቄዎች ውስጥ፥- የኮምፒውተር ቁልፍ አቀማመጡ...
-
ኢናብ ቴክ - ቴሌብርን ለመጀመሪያ ጊዜ መክፈት
ጤና ይስጥልን፣ እንዴት አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በኤፒሶዱ የመጀመሪያ ክፍል በሆነው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት ስካይፕ በተባለው የቪዲዮ መደዋወያ አፕሊኬሽኑ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ሊያቆም ስለመሆኑ እና ጉግል በክሮም ብራውዘሩ ሴቭ የተደረጉ ፓስወርዶችን በአፕዴት ችግር ምክንያት ለ18 ተከታታይ ሰአታት ማሳየት ሳይችል መቅረቱን የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ቀጣይ በሆነ የዝግጅት ክፍል፣ ቴሌብር አፕሊኬሽንን ለመጀመሪያ ጊዜ...
-
ኢናብ ቴክ - ቴሌብርን መተዋወቅ
ሰላም፣ እንዴት አላችሁ? የኢናብ ቴክ ፖድካስት ተከታታዮች፤ በዚህ ክፍል የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ኤንቪዲኤ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ 11 ዋን ድራይቭ የተባለው አገልግሎቱን በሙሉ ስክሪን ማስታወቂያ ለተጠቃሚዎቹ በማድረስ ማስቸገሩን የሚሉትን መረጃዎች እናወራችኋለን። ዛሬ በሚጀምረው የሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ሁላችንም በተለያየ አጋጣሚ ስለምንሰማው እና በርካቶቻችን በተለያየ መጠን እየተጠቀምነው እንደሆነ...
-
ኢናብ ቴክ - አንድ በአንድን ከሩቁ መቆጣጠር እና ሙዚቃውን በስልካችን ላይ መስማት
እንዴት ናችሁ? የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ ዛሬ ደግሞ ይዘነው በመጣነው ኤፒሶድ፣ በቀዳሚው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ጉግል ኩኪስ የተባሉት ቴክኖሎጂ ለማስቀረት ያወጣውን እቅድ ስለመቀልበሱ እና ክራውድ ስትራይክ ድርጅት ፋልኮን የተባለው አንቲቫይረሱ አፕዴት ሲያደርግ በአለማቀፍ ደረጃ ያስከተለው ቀውስ እንዳይደገም ስለሚያደርገው ጥረት የሚመለከቱ መረጃዎችን እናጋራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የመጨረሻ ክፍል፣…
more -
ኢናብ ቴክ - የአንድ በአንድ ቀሪ ሴቲንጎች እና በመደበኛ ከማጫወት ባሻገር ያሉ አጠቃቀሞች
ሰላም ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ስላካተታቸው አዳዲስ ነገሮች እና ያደረጋቸውን ማሻሻያዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ እያስተዋወቅነው ባለው ዋን ባይ ዋን በተባለው የኦዲዮ ማጫወቻ አፕሊኬሽን ቀሪ ሴቲንጎችን እንዴት እንደምናስተካክል፣ ድምጽን እንዴት አፍጥነን እንደምናጫውት፣ ያለንበትን የትራክ ቦታ እንዴት መዝግበን ማስቀመጥ እንችላለን?...
-
ኢናብ ቴክ - የአንድ በአንድ ስፔሻል እና ዊንዶውስ ሴቲንጎች
እንዴት ቆያችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች? በቅድሚያ በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች የዝግጅቱ ክፍል፣ በክራውድ ስትራይክ የአንቲቫይረስ ድርጅት አፕዴት ያስከተለው ቀውስ በመጠኑም ቢሆን መቀጠሉን፣ ሳምሰንግ በስልኮቹ አንድሮይድ ያጋጠመን የደህንነት ክፍተት ባልተለመደ ፍጥነት ፈፕዴት ሊለቅ ስለመሆኑ እንዲሁም ጉግል ክሮም ፋይል ዳውንሎድ ስታደርጉ ለምንድን ነው የምታወርዱት ብሎ መጠየቅ መጀመሩን የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስለዋን…
more -
ኢናብ ቴክ - የአንድ በአንድን ሴቲንጎችን ማስተካከል
ጤና እና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት ተከታታዮች። ኤፒሶዱን በምናስጀምርበት የቴክኖሎጂ መረጃዎች፣ የአንቲቫይረስ አፕዴት በፈጠረው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በመላው አለም የሚገኙ ትላልቅ ኩባንያዎች እና ተቋማት አገልግሎቶቻቸው ተቋርጠው ስለመዋላቸው፣ ዊንዶውስ አዲስ የአፕዴት መንገድ ስለማስጀመሩ እና የአፕል አይኦኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም በቀላሉ ሀክ ማድረግ አለመቻሉን ይህንን የሚሰራ ተቋም ስለማስታወቁ የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ...
-
ኢናብ ቴክ - አንድ በአንድ ላይ ፕለጊኖች መጨመር እና የኦዲዮ ሴቲንጎችን መመልከት
ሰላም እንዴት አደራችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች። በዛሬው ኤፒሶድ ቀድሞ በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 ይዞት ሊመጣ ነው ስለተባለው ስልካችንን እንደኮምፒውተር መጠቀም የሚያስችለን አገልግሎት እና ማይክሮሶፍት ወደ ፍልስጥኤም የሚደውሉ ደንበኞቹን አካውንት እየሰረዘ መሆኑን ስለመዘገቡ የሚሉ መረጃዎችን እንቃኛለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ማስተዋወቅ በጀመርነው የዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን ፕለጊኖችን እንዴት እንደምናካትትበት እና የኦዲዮ...
-
ኢናብ ቴክ - አንድ በአንድ የኦዲዮ ማጫወቻውን መተዋወቅ
እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት የመጨረሻ ኤፒሶድ ይዘን መጥተናል፣ ብያችሁ እንደነበር ይታወሳል። ለፈጠርኩት የመረጃ ክፍተት ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ፖድካስቱ የሚቀጥል መሆኑን የተነገረኝ ስለሆነ እነሆ ቀጣይ ክፍል ይዤ መጥቻለሁ። ዝርዝሩን ከኤፒሶዱ ታገኙታላችሁ። እንደተለመደው፣ በቀዳሚው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ክፍል፣ ጃውስ ባደረገው ማሻሻያ ስለጨመራቸው ነገሮች እና ጃፓን ፍሎፒ የተባለው እጅግ የቆየ ቴክኖሎጂ ከመንግስት...
-
ኢናብ ቴክ - ከስልክ በተግባር ፕሪንት ማድረግ
እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት የመጨረሻ ኤፒሶድ ይዘን መጥተናል። በዚ በመጨረሻ ክፍል ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2024.2 ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና አፖል ኩባንያ በአይኦኤስ የወደፊት ኦፐርቲንግ ሲስተሙ ቨርዥን 18 ከተደራሽነት ጋር ስላካተታቸው ነገሮች መረጃዎችን እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የመጨረሻ ክፍል ከስልካችን በቀትታ ፕሪንት እያደረግን በተግባር...
-
ኢናብ ቴክ - በስልካችን ላይ ሞቢሊቲ ፕሪንትን ማስተካከል
ሰላም፣ ጤና ይስጥልን፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዩቲውብ በስልካቸውም ሆነ በኮምፒውተራቸው ላይ አድ ብሎከሮችን ጭነው ዩቲውብን ለመጠቀም የሚሞክሩ ተጠቃሚዎቹን ቪዲዮዎችን መመልከት እንዳይችሉ አልያም የሚመለከቱትን ነገር እንዳይመች የማድረግ ሙከራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል የሚለውን መረጃ እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል ሞቢሊቲ ፕሪንትን በስልካችን ላይ እንዴት...
-
ኢናብ ቴክ - ፖድካስት እና ፖኬት ካስት
እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ይህ እኔ የማቀርበው ዝግጅትም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ፖድካስት እየተባለ ሲጠራ ሰምታችኋል። በዚህ ዝግጅት ስለ ፖድካስት ምንነት እና ፖድካስትን ለመከታተል እና ለማድመጥ ከሚረዱን የስልክ አፕሊኬሽኖች አንዱ ስለሆነው ፖኬት ካስት የሚስተካከልበትን መንገድ እና አጠቃቀም እናብራራለን። ሙሉ ዝግጅቱን አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት...
-
ኢናብ ቴክ - ሞቢሊቲ ፕሪንትን ኮምፒውተር ላይ መጫን እና ማስተካከል
ሰላም የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ከዚህ በፊት በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ዘገባዬ የነገርኳችሁ አንድሮይድ 15 ቤታ ወይም የሙከራ ቨርዥን አካል ሆኖ ይለቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ቶክ ባክ 15.0 ስላካተታቸው ነገሮች መረጃ ይዘናል። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል በሁሉም አይነት ፕሪንተሮች ከስልካችን ፕሪንት ለማድረግ ስለሚያስችለን ሞቢሊቲ ፕሪንት አጫጫን እና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሰራ ሴቲንጎቹን…
more -
ኢናብ ቴክ - ሞቢሊቲ ፕሪንትን ማስተዋወቅ
እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አፕል ኩባንያ በኮምፒውተር እና በስልክ መካከል ደረጃ ላይ የሚገኙትን አይፓድ የተባሉትን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ ያካተቱ ታብሌቶቹን ለገበያ ማቅረቡን፣ ማይክሮሶፍት ወርድ ከተለያዩ ቦታዎች በኮፒ ፔስት ጽሁፍ ስታደራጁ ያጋጥም የነበረውን የቅርጽ መዘበራረቅ የሚያስቀር አፕዴት ስለመልቀቁ እንዲሁም ኦፕን ኤአይ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰሪ ድርጅት ቻት ጂፒቲ በተባለው አገልግሎቱ ከሰው…
more -
ኢናብ ቴክ - ስለሞባይል ፕሪንት ማስተዋወቅ
ሰላም ጤና ይስጥልን፣ እንደምን አላችሁ፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 በ2ኛ ሙከራ ቨርዥኑ አዲስ ስላካተታቸው ነገሮች እንዲሁም ታዋቂው እና ተወዳጁ የሞባይል ቪዲዮ ማጋሪያ እና መመልከቻ ቲክቶክ አፕሊኬሽን በአሜሪካ ሀገር ስላጋጠመው ተግዳሮት ዝርዝር እናወራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልኮቻችን ፕሪንት ስለማድረግ ማብራሪያ እናቀርባለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል…
more -
ኢናብ ቴክ - ፕሪንት አደራረግ
ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ዋነኛ ስክሪን ሪደር የሆነው ጃውስ ፎር ዊንዶውስ በሜይ 2024 አፕዴት በሚል አዲስ በለቀቀው ማሻሻያ ስላደረጋቸው ለውጦች እና ማስተካከያዎች እንዲሁም ሳም ኦልትማን የተባለው የቴክኖሎጂ ባለሀብት የድሆችን የግል መረጃ ለመግዛት ሀምሳ ዶላር እየከፈለ ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት የመጨረሻ ክፍል፣...
-
ኢናብ ቴክ - ማይክሮሶፍት ወርድ
ሰላም? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ኮምፒውተርን ስንጠቀም ለትምህርትም ሆነ ለስራ መሰረታዊ ከሆኑ አፕሊኬሽኖች ውስጥ ዋነኛው የማይክሮሶፍት ኦፊስ ጥቅል ነው። ከዚህ ጥቅል ውስጥ ደግሞ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ አንደኛ ሊባል የሚችለው ማይክሮሶፍት ወርድ ነው። ለኮምፒውተርም ሆነ ለማይክሮሶፍት ወርድ በስክሪን ሪደር ለመጠቀም መጀመሪያቸው ለሆኑ መሰረታዊ የሆኑ አጠቃቀሞችን ያሳያል ብለን ያሰብነውን ሙሉ ቱቶሪያል አቅርበናል። ሙሉውን አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣...
-
ኢናብ ቴክ - ፕሪንተርን ከኮምፒውተር ጋር ማስተዋወቅ
እንደምን አላችሁ ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች ዝርዝሩን እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ ፕሪንተራችንን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ስለሚደረገው ፕሪንተርን ከኮምፒውተር ጋር የማስተዋወቅ ሂደትን በተግባር እየሞከርን እንመለከታለን። ለአድማጮች ጥያቄ፣ የማይክሮሶፍት ኤክሴል…
more -
ኢናብ ቴክ - የፕሪንተር አካላዊ መግለጫ
ሰላም ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት በስቶር ውስጥ የሚገኙ አፖችን በሌላ አማራጭ የሚጫኑበትን መንገድ ስለማመቻቸቱ፣ በአሜሪካ የሚገኙ የፖሊስ ተቋማት የጂፒኤስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሌቦችን በመኪና ማሯሯጥ ማቆማቸው ስለመዘገቡ እንዲሁም አፕል በአይፎን ስልኮቹ እና በሌሎቹ መሳሪያዎቹ ጋር በመያያዝ ሲጠፉ ለማግኘት የሚረዳ አገልግሎቱ የንጹሀን ግለሰቦች ቤት በፖሊስ ተሰብሮ እንዲገባ እና ንብረታቸው እንዲበለሻሽ…
more -
ኢናብ ቴክ - የፕሪንተር አይነቶች
እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ኤንቪዲኤ በአዲስ ቨርዥኑ ይዟቸው ከመጣቸው ነገሮች ውስጥ በተለይ በዋና ዋና ጉዳዮች ዘርዘር ያለ ማብራሪያ አቅርበናል። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ ስለፕሪንተር አይነቶች ምንነት እናቀርባለን። ከአድማጮች ከተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች፣ ስለኮምፒውተር ፎርማት አደራረግ ዙሪያ፣ ስለኢትዮቴሌኮም ቴሌብር…
more -
ኢናብ ቴክ - ዩኒግራም ተደራሹ የዊንዶውስ ቴሌግራም ክለያንት (ማጠቃለያ)
እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ዩኒግራም የተባለው የዊንዶውስ ቴሌግራም አፕሊኬሽን ክለያንት ምንነት፣ ከየት ልናገኘው እንደምንችል እና አጫጫኑን በማስተዋወቅ ጀምረን ከጫንነው በኋላ ስለሚመጣው ምርጫዎች ወደ ቴሌግራም አካውንታችን በዩኒግራም አማካይነት ስለምንገባባቸው መንገዶች እንቃኛለን። ከዚያ በማስቀጠል ዩኒግራምን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት በኤንቪዲኤ ዩኒግራም ለመጠቀም የሚረዱ ሴቲንጎችን የትኞቹ እንደሆኑ በተለይ የዩኒግራም አድኦን ክፍሉን ከተመለከትን…
more -
ኢናብ ቴክ - ፕሪንተርን መተዋወቅ
ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ሌላኛው አማራጭ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ዊንዶውስ 32 ቢት ቨርዥን ኦፐሬቲንግ ሲስተም በ2038 ስለሚገጥሙት ችግሮች የሚሉትን መረጃዎች እናካፍላችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ዘመናዊውን የሶት ኮፒ ዘመን ከቀድሞው ሃርድ ኮፒ ዘመን የሚያገናኘውን "ፕሪንተር" የተባለውን መሳሪያ መተዋወቅ እንጀምራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም...
-
ኢናብ ቴክ - በኢትዮቴሌኮም የኤምኤምኤስ መልእክትን መላክ እና መቀበል
ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃ፣ የአንድሮይድ መደበኛ ስክሪን ሪደር የሆነው ጉግል ቶክ ባክ በአዲሱ ቨርዥኑ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ኢትዮቴሌኮም አዲስ ካስጀመራቸው አገልግሎቶች ውስጥ የኤምኤምኤስ መልእክት እንዴት እንደምንልክ እና እንዴት እንደምንቀበል በተግባር እየሞከርን እናሳያችኋለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል አጠቃቀም ቀጣይ ክፍል ስለኤክሴል...
-
ኢናብ ቴክ - ኢትዮቴሌኮም RCS እና MMS አገልግሎቶች
እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት ኦፊስ ቨርዥን 2024 ሊለቀቅ ስለመሆኑ እና የአይፎን አምራች የሆነው ኩባንያ አፕል በአይፎን ስልኮቹ ላይ የሶስተኛ ወገን አፕሊኬሽኖች እንዲጫኑ እንዲፈቅድ ስለመገደዱ የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ኢትዮቴሌኮም አዲስ ካስጀመራቸው አገልግሎቶች ውስጥ RCS እና MMS የተባሉትን ለመጠቀም የምናስተካክላቸውን ሴቲንጎች እንጎበኛለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር...
-
ኢናብ ቴክ - የኢትዮቴሌኮም ተጨማሪ አገልግሎቶችን መተዋወቅ
ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ኤንቪዲኤ በለቀቀው አነስተኛ ማሻሻያ ስላደረጋቸው ለውጦች፣ በዊንዶውስ 11 አንድሮይድ አፕሊኬሽኖችን የሚያስጠቅመው አገልግሎት ሊቋረጥ መሆኑን እና ቲክቶክ በአሜሪካ ሀገር እንዳይሰራ ሊደረግ መሆኑን የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ኢትዮቴሌኮም አዲስ ስላስጀመራቸው ተጨማሪ አገልግሎቶች ምንነት እና አጠቃቀም የሚያብራራ ዝግጅት ይዘናል። በመሰረታዊ...
-
ኢናብ ቴክ - ፈጣኑ ቪፒኤን - ፕሮቶን?
እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በአንድሮይድ ስልካችን ላይ የሚጫነውን፣ የምንጎበኛቸው ውብሳይቶች እና የኔትወርክ አቅራቢዎቻችን የሚሰበስቡብንን የግል መረጃ ለመቀነስ፣ ለእኛ እንዳይሸጡ አልያም እንዳይታዩ በአቅራቢዎቻቸው የተከለከሉ ይዘቶችን ለመመልከት፣ የግል መረጃችንን ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፎ እንዳይሰጥ የሚከላከል ጠንካራ ህግ እና ባህል ባላት ሀገር ውስጥ ሆኖ የሚሰራውን እና ይህን ሁሉ ለማድረግ የሚረዳንን ፕሮቶን ቪፒኤን የተባለውን አፕሊኬሽን አጠቃቀም...
-
ኢናብ ቴክ - ከፎርማት በኋላ ኮምፒውተርን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተካከል
ጤና ይስጥልኝ፤ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ጃውስ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው አዳዲስ ነገሮች እና ማሻሻያዎች እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ የመጨረሻውን ክፍል፣ ከፎርማት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኮምፒውተራችንን እንዴት እናስጀምራለን። የሚለውን በማየት ይህንን ቅንብር እናበቃለን።...
-
ኢናብ ቴክ - የማይከፍትን ኮምፒውተር ፎርማት ማድረግ
ሰላም የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 በሙከራ ደረጃ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች፣ የአይፎን ስልክ አምራች የሆነው አፕል ኩባንያ ስልካችሁን በሩዝ አታድርቁ በማለት ማሳሰቡን እና አውዳሲቲ የተባለው የድምጽ ማቀናበሪያ ነጻ ሶፍትዌር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማካተቱን የሚሉትን ዜናዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤...
-
ኢናብ ቴክ - አውዳሲቲ የድምጽ መቅረጫው እና ማቀነባበሪያው
ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ማንኛውንም አይነት ድምጽ ሆነ ንግግር ለመቅረጽ እና ለማቀናበር የሚያገለግለው፣ ያላንዳች የገንዘብ ክፍያ በነጻ መጠቀም የሚያስችለው፣ በሶስት አይነት የኮምፒውተር ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚጫነውን (አውዳሲቲ) የተባለውን አፕሊኬሽን ዐጠቃቀም መግለጫ እና በተግባር ሙከራ ሙሉ ዝግጅት አቅርበንላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577…
more -
ኢናብ ቴክ - የማይከፍትን ኮምፒውተር ለፎርማት ማዘጋጀት
እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2023.3.3 ስላደረጋቸው አነስተኛ ማሻሻያዎች፣ ኋትስአፕ ለሌሎች አፕሊኬሽኖች መልእክት መላላክ የሚያስችል አገልግሎት ሊጀምር ስለመሆኑ እና ጉግል ከሚገድላቸው አገልግሎቶቹ ውስጥ የካሽድ ሪዘልት የሚለው መጨመሩን የሚሉትን ጉዳዮች በቅድሚያ እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ...
-
ኢናብ ቴክ - በሩፈስ ፍላሾችን ኮምፒውተር ፎርማት ለማድረግ ማዘጋጀት
ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ እንደሁልጊዜው፣ በዝግጅታችን መጀመሪያ በሚቀርቡት የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ በለቀቀው አዲስ ቨርዥን ስላደረጋቸው ማሻሻያዎች በዝርዝር እናወራለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ ቱቶሪያል፤ የማይከፍት እና አፕሊኬሽን የማይጭን ኮምፒውተር ካለን ከፍላሽ በመነሳት ፎርማት ማድረግ እንድንችል የሚረዳንን...
-
ኢናብ ቴክ - ዶት ወከር
እንደምን አላችሁ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በስልካችን ኢንተርኔት ሳይኖረንም ቢሆን ሳተላይትን በመጠቀም ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚረዳን እና ያለንበትን ቦታ የሚነግረን የአንድሮይድ አፕሊኬሽን "ዶት ወከር" አጠቃቀም የሚያብራራ ዝግጅት ይኸው ቀርቧል። በሙሉ በአንዴ እንድታደምጡ ተጋብዛችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት...
-
ኢናብ ቴክ - በእርግጥም ኮምፒውተርን ፎርማት ማድረግ
ሰላም፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ እንደሁልጊዜው፣ በዝግጅታችን መጀመሪያ በሚቀርቡት የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጂሜይል ቤዚክ ኤችቲኤምኤል የተባለውን የኢሜይል አገልግሎቱን በቀላሉ ለመጠቀም የሚያስችል ክፍል ማቋረጡን፣ ኦፔራ ጂኤክስ የተባለው ብራውዘር ለተማሪዎች ከወላጆቻቸው እና ለሰራተኞች ከአለቆቻቸው የሚሰሩትን ስራ መደበቅ እንዲችሉ የሚያስችል አገልግሎት ይዞ መምጣቱን ስለማስታወቁ እንዲሁም በአለማችን የኢንተርኔት ዝውውር መጠን በሀያ አምስት በመቶ ለሁለተኛ ተከታታይ…
more -
ኢናብ ቴክ - ሻርፕ ኪስ የኮምፒውተር ቁልፍ ማስተካከያው
ሰላም፣ ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በኮምፒውተራችን እየቀሩ ያሉ ቁልፎችን ለማምጣት፣ ያለቦታቸው የተቀመጡትን እኛ ወደምንፈልገው አካባቢ ለመቀየር፣ የተበላሹብንን የኮምፒውተር ቁልፎች እምብዛም በማንጠቀማቸው ቁልፎች በመተካት ከወጪ ለመዳን እና ለመሳሰሉት የኮምፒውተር ቁልፍ ነክ አገልግሎቶች የሚረዳንን ሻርፕ ኪስ የተባለውን የዊንዶውስ አፕሊኬሽን አጠቃቀም አቅርበናል። አድምጡ፣ ተጠቀሙበት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም...
-
ኢናብ ቴክ - ከኮምፒውተር ፎርማት በፊት ልናደርጋቸው የሚገቡ ዝግጅቶች እና ጥንቃቄዎች እንዲሁም የኢዚ ቢሲዲ አጫጯን
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ቀዳሚ በሆኑት በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር ቶክ ባክ በለቀቀው አነስተኛ ማሻሻያ ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች፣ የዊንዶውስ አብሮት የሚመጣው ስክሪን ሪደር "ናሬተር" ዊንዶውስ 11 በሚጫን ጊዜ አልጀምርም ብሎ የማስቸገር ጸባይ ስለማሳየቱ እና ፌስቡክ የጀመረው የማመስጠር ቴክኖሎጂ ለወንጀለኞች ምቹ እንደሆነ በአንጻሩ ለህግ አስከባሪዎች አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱ የሚሉትን መረጃዎች እናወጋችኋለን።...
-
ኢናብ ቴክ - በአንድሮይድ ስልኮች መጽሀፍትን ማንበብ
ጤና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ዲጂታል መጽሀፍትን ለመዝናኛ፣ ለጥናት፣ ለእውቀት እና ለሌሎች ጥቅሞቻቸው ለማንበብ እና ለማድመጥ የሚረዳውን አት ቮይስ አላውድ ሪደር የተባለውን አፕሊኬሽን አጠቃቀም እንደሚከተለው አቅርበንላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ...
-
ኢናብ ቴክ - ኮምፒውተር ፎርማት ለማድረግ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች
በዚህ ክፍል፣ ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በአሉን ለምታከብሩ እንኳን ለገና በአል አደረሳችሁ እያልን፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ጃውስ ስክሪን ሪደር በለቀቀው ማሻሻ ያይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ጉግል በክሮም ብራውዘሩ ኩኪስ የተባለውን የቴክኖሎጂ አይነት ለማስቀረት የሚያስችለውን ሂደት ሀ ብሎ መጀመሩን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ኮምፒውተራችንን ያለአይናማ እርዳታ እንዴት ፎርማት ማድረግ እንችላለን? በሚል የሚቀርብ...
-
ኢናብ ቴክ - የኮምፒውተር ፎርማት አደራረግ
በዚህ ክፍል፣ ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዩቲውብ የማስታወቂያ መከላከያ ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ቪድዮዎችን እያዘገየ ማሳየት መጀመሩን፣ ቲክቶክ በአሜሪካ ሞንታና ግዛት ተጥሎበት የነበረው እገዳ በፍርድ ቤት የተነሳለት መሆኑን፣ ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ 10 የደህንነት ማሻሻያዎችን ከ2025 በኋላ በክፍያ ማቅረብ ሊጀምር መሆኑን ማስታወቁን እና ጉግል ተጠቃሚ የሌላቸው አካውንቶችን መሰረዝ መጀመሩን መግለጹን የሚሉትን መረጃዎች…
more -
ኢናብ ቴክ - የጃውስ አጠቃቀም
በዚህ ክፍል ጤና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ተከታታዮች፤ ከስክሪን ሪደሮች ሁሉ ለረጅም ጊዜ በአገልግሎት ላይ የሚገኘው፣ ዝነኛው፣ ባለብዙ ተጠቃሚው፣ ለብዙዎች የመጀመሪያ የሆነውን የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር "ጃውስን" አጠቃቀም ይዘንላችሁ መጥተናል። በተለይ፣ ኮምፒውተር ጀማሪ ለሆኑ በእጅጉ ስለሚጠቅም በስጦታም ሆነ በማስታወቅ ይህንን ዝግጅት እንድትጋቡልን። ኮምፒውተር ለለመዳችሁትም አንዳንድ ቁመነገር አታጡበትም አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም...
-
ኢናብ ቴክ - በፖኬት ካስት ፖድካስቶችን ማድመጥ እና ኤፒሶዶችን ማደራጀት
በዚህ ክፍል፣ እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዊንዶውስ 11 በቨርዥን 23H2 ይዟቸው ስለመጣቸው አዳዲስ ነገሮች፣ ፐርግ የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ማይክሮሶፍትን የዊንዶውስ 10ን እድሜ እንዲያራዝም መጠየቁን እና ማይክሮሶፍት ወርድ 40ኛ አመቱን ማክበሩን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን።። በሞባይል ወርልድ፣ ስለፖኬት ካስት የተዘጋጀው ዝግጅት በመጨረሻው ክፍል፣ ሳብስክራይብ ያደረግናቸውን ፖድካስቶች እንዴት እንደምናደምጥ…
more -
ኢናብ ቴክ - ዊንዶውስ ኤክስፕሎረርን መጠቀም
በዚህ ክፍል ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች። በዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም፣ መሰረታዊ የሆነው፣ ከፊት ለፊት መጥተው የምናዛቸውን የዊንዶውስ ክፍሎች ከጀርባ ሆኖ የሚያስተዳድረው፣ መሰረታዊ የሆኑ የዊንዶውስ ፋይሎችን የማስተዳደር እንደመሰረዝ፣ መገልበጥ እና ማንቀሳቀስ የመሳሰሉትን የምንከውንበት ዊንዶውስ ኤክስፕሎረር የተባለውን ክፍል አጠቃቀም አቅርበንላችኋል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣...
-
ኢናብ ቴክ - ፖኬት ካስት አካውንት አፈጣጠር እና የፖድካስት ሰብስክራይብ አደራረግ
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር ጃውስ በቨርዥን 2024 ይዟቸው ስለመጣቸው አዳዲስ ለየት ያሉ ነገሮች እና ስላሻሻላቸው ጉዳዮች እንዲሁም ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 11 ቨርዥኖች ውስጥ አንዱን ድጋፍ ያቆመበት መሆኑን ማስታወቁን የሚሉን መረጃዎች እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ፣ ፖኬት ካስትን ማስተዋወቃችንን ቀጥለን፣ በአፑ አካውንት እንዴት ክርኤት እንደምናደርግ እና የምናደምጣቸውን…
more -
ኢናብ ቴክ - የዊንዶውስ ምንነት እና መሰረታዊ ክፍሎቹ
በዚህ ክፍል ጤና ይስጥልን፣ ኢናባውያን። ከኮምፒውተር ጋር ተያይዞ ሁሌ ስሙ የሚነሳው ዊንዶውስ የተባለው የኮምፒውተር ክፍል ምንነት እና እና ዋና ክፍሎቹን የሚያስተዋውቅ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot…
more -
ኢናብ ቴክ - ፖድካስት ምንድን ነው?
በዚህ ክፍል፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር ዔንቪዲኤ በቨርዥን 2023.3 ይዟቸው ስለመጣቸው እና ስላሻሻላቸው ነገሮች እንዲሁም ለግለሰብ ተጠቃሚዎች ኢንቴል ለገበያ ያቀረበው ፕሮሰሰር ፍጥነት ሪከርድ መስበሩን የሚሉትን እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ፣ ፖኬት ካስት ስለተባለው አፕሊኬሽን የመጀመሪያ ክፍል ስለፖድካስት ምንነት እናብራራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት የማይክሮሶፍት ወድ…
more -
ኢናብ ቴክ - የኮምፒውተር ኪቦርድ አጠቃቀም
በዛሬው ክፍል ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ እንደምን አላችሁ! ኮምፒውተርን በተለይ በስክሪን ሪደር ለምንጠቀም ተጠቃሚዎች ወሳኝ የሆነው፣ በየእለቱ ኮምፒውተራችንን ስንጠቀም የግድ የሚያስፈልገን የኮምፒውተራችን ክፍል ኪቦርድ" ምንነት፣ ስለሚያካትታቸው ቁልፎች፣ ስለአጠቃቀማቸው እና ተያያዥ ጉዳዮች በተለይ ለኮምፒውተር ጀማሪዎች ያዘጋጀሁትን ፕሮግራም አቅርቤላችኋለሁ። የኮምፒውተር ጀማሪም ባትሆኑ አንዳንድ ቁምነገር እንደማታጡበት ተስፋ አለኝ። አውርዱ እና…
more -
ኢናብ ቴክ - የዩኒግራም መሰረታዊ የአጠቃቀም ዘዴዎች
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አዲስ ክፍል ይዘን ቀርበናል። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 14 ለገበያ ስለመቅረቡ እና ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እንዲሁም አፕል ዋነኛ ተፎካካሪው የሆነውን ጉግልን የመጀመሪያ ምርጫ ሰርች ኢንጅን ለምን እንዳደረገው የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ የቴሌግራም ክላያንት የሆነው ዩኒግራምን መሰረታዊ የአጠቃቀም ዘዴ እንዳስሳለን። በመሰረታዊ...
-
ኢናብ ቴክ - ሶፍትዌር ምንድን ነው?
ሰላም ኢናባውያን፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኮምፒውተር ስርአት ውስጥ አንዱ ክፍል ስለሆነው ስለሶፍትዌር ምንነት፣ አይነቶች እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን በሚመለከት ያዘጋጀሁትን ዝግጅት አቅርቤላችኋለሁ። አዲስ ነገር እንደምታገኙበት ተስፋ አለኝ።
-
ኢናብ ቴክ ወ3ክ4 - የዩኒግራም ጠቃሚ ሴቲንጎች
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ እነሆ ኢናብ ቴክ ፖድካስት አዲስ ክፍል ይዘን ቀርበናል። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ለአይፎን ስልኮች ኦፐሬቲንግ ሲስተም የሆነው አይኦኤስ አዲስ ቨርዥን ስለመልቀቁ እና ስላካተታቸው ነገሮች፣ እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚደረሱ መጻህፍት ብዛት የተነሳ የመጻህፍት አከፋፋዩ ድርጅት በቀን መታተም በሚችሉት የመጻህፍት ብዛት ላይ ገደብ ስለማስቀመጡ የሚሉትን መረጃዎች እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዩኒግራምን ስንጠቀም...
-
ኢናብቴክ - ሃርድዌር ምንድን ነው?
ሰላም ኢናባውያን፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ የኮምፒውተር ስርአት ውስጥ አንዱ ክፍል ስለሆነው ስለሀርድዌር ያዘጋጀሁትን ዝግጅት አቅርቤላችኋለሁ። አዲስ ነገር እንደምታገኙበት ተስፋ አለኝ።
-
ኢናብ ቴክ - ወ3ክ3 - ዩኒግራም እና ዩኒግራም ፕላስ
በዚህ ክፍል፣ ጤና ይስጥልን፣ እነሆ ኢናብ ቴክ ፖድካስት ወቅት 3 ክፍል 3 ቀርቦላችኋል፤ ተጋበዙልን። በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆኑት ጉግል ቶክ ባክ እና ጂሺዎ አዳዲስ ቨርዥኖችን ስለመልቀቃቸው እና ይዘዋቸው ስለመጧቸው ነገሮች እናወራችኋለን።። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዩኒግራምን ከኤንቭዲኤ ጋር ስንጠቀም ስለምናስተካክላቸው ሴቲንጎች እናብራራለን። በመሰረታዊ ክፍል፣ ጃውስንም ሆነ ኤንንቪዲኤን ስንጠቀም የሚያስፈልጉን መሰረታዊ...
We're indexing this podcast's transcripts for the first time — this can take a minute or two. We'll show results as soon as they're ready.
No matches for "" in this podcast's transcripts.
No topics indexed yet for this podcast.
Loading reviews...
ABOUT THIS SHOW
በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።
HOSTED BY
Abate Tsegaye
CATEGORIES
Loading similar podcasts...