ኢናብ ቴክ - ፖድካስት ምንድን ነው?
from ENAB TECH PODCAST
በዚህ ክፍል፣ ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር ዔንቪዲኤ በቨርዥን 2023.3 ይዟቸው ስለመጣቸው እና ስላሻሻላቸው ነገሮች እንዲሁም ለግለሰብ ተጠቃሚዎች ኢንቴል ለገበያ ያቀረበው ፕሮሰሰር ፍጥነት ሪከርድ መስበሩን የሚሉትን እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ፣ ፖኬት ካስት ስለተባለው አፕሊኬሽን የመጀመሪያ ክፍል ስለፖድካስት ምንነት እናብራራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት የማይክሮሶፍት ወድ አፕሊኬሽን እንዴት እንከፍታለን የሚለውን እናያለን። በሁሉም ኮምፒውተሮች ላይ ያለስክሪን ሪደር ጭምር ወርድን የምንከፍትበትን ዘዴም እንተዋወቃለን። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁ ወይም የቴሌግራም መልእክት በማድረግ ልትልኩልኝ ትችላላችሁ። ኢትዮቴሌኮም በኔትወርኩ ላይ ባደረገው ለውጥ ምክንያት የድምጽ መልእክት መስራት ስላቆመ ለጊዜው የድምጽ መልእክቶች ለመቀበል አልቻልኩም። ሲስተካከል የማስታውቃችሁ ይሆናል። ቴሌግራም ላይ @enabtechpod እና @enabtechbot በመግባት ትችታችሁን ለመላክ እና አድማጮቼን እንዳውቅ ሰርቬይ ልትሞሉልኝ ትችላላችሁ። በዝግጅቱ የተጠቀሰውን ኤንቪዲኤ ቨርዥን 2023.3 እዚህ ያውርዱ።
Embed this episode
No transcript yet.