EPISODE · Dec 30, 2025 · 1H
''ቅድሚያ ለአሜሪካ የጤና ስምምነት'':- ለአፍሪካ አጋርነት፣ ጉልበት ወይስ ጥገኝነት?
from The Rising South
"[የአፍሪካ] መንግስታት ከሲቪል ማህበረሰብ፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች እና ከሌሎች አካላት ጋር ቢመክሩ ኖሮ፣ ከእነዚህ ቡድኖች ሊመጣ በሚችለው ጫና ምክንያት መንግስታቱ ወደ ስምምነቱ ላይገፉ ይችሉ ነበር። በአሁኑ ወቅት ከኬንያ እያየን ያለነው በጣም የሚደነቅ ነገር ቢኖር ጠንካራ የሲቪል ማህበረሰብ ንቅናቄ መኖሩን ነው፤ ወደ 50 የሚጠጉ ድርጅቶች አሁን ያለውን ስምምነት በመቃወም መቆማቸው የስምምነቱን የተወሰነ ክፍል ለማስቆም አስችሏል።" ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የሚግኙት የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሻኪራ ቹናራ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ልዩ የራይዚንግ ሳውዝ የሁለት ክፍል ዝግጅታችን፣ የአፍሪካን የጤና ሉዓላዊነት እና የፈጠራ አድማስ እንቃኛለን። በመጀመሪያው ክፍል፣ ከዶ/ር ሻኪራ ቹናራ ጋር በመሆን ቅድሚያ ለአሜሪካ የጤና ስምምነት የተሰኙ የጤና ስምምነቶች ያላቸውን አንድምታ በመተንተን፣ ከአፍሪካ የጤና እና የዘረመል መረጃዎች (ጂኖሚክ ዳታ) ትክክለኛ ተጠቃሚ ማን እንደሆነ እንዲሁም በዚህ ስምምነት ምክንያት የአፍሪካ ሀገራት እንዴት ባለ መልኩ ዘላቂ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል የሚያስረዱ ሲሆን፤ በመቀጠል፣ ኢትዮጵያዊው የቴክኖሎጂ ስራ ፈጣሪ ጆኤል ጣልአርጌ አፍሪካውያን የፈጠራ ባለሙያዎች እንዴት የአካባቢውን ሀሳቦች ወደ ተጨባጭ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ መቀየር እንደሚችሉ ያካፍለናል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
NOW PLAYING
''ቅድሚያ ለአሜሪካ የጤና ስምምነት'':- ለአፍሪካ አጋርነት፣ ጉልበት ወይስ ጥገኝነት?
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.