Skip to content
•••ሥትናፍቂኝ episode artwork

Jan 10, 2021 2 min

•••ሥትናፍቂኝ

from Sost kilo Hosted by Leoul Zewelde

ስ ት ና ፍ ቂ ኝ [ ል ዑ ል ፡ ዘ ወ ል ደ ] ስትናፍቂኝ … ባሏ ለዕድሜ ይፍታሕ ወህኒ እንደተወረወረባት ሴት ነው ። መልሳ ላታገኘው ነገር እሁድን እየጠበቀች እንደምትጠይቀው … ስትናፍቂኝ … ሲዖል ተኮራምቶ ገነትን እንደሚያልም ሠይጣን ነው ። ምህረት ሱሚ ሆኖበት በልቡ ማብከሪያ እንደሚለምን ። ጥፍሮቹን ቢከረክም'ም ርህራሄ ተነፍጎት ምናልባትን እንደያዘ… ስትናፍቂኝ … በምናብሽ የሚሄድ አስፋልት ሣይና በዛ ላይ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚጓዝ ከንቱ ደሞ አስቢ ። እየሄደ የሚመስለው ግን አንድ ቦታ ላይ እንደቆመ ። ኃይሉ ሲሟጥ አስፋልቱ በራሱ አቅጣጫ እያንደባለለ እንደሚወስደው … ስትናፍቂኝ … ወደቀኝ እንደሚዞር ሽክርክር ሰዓት ነው ። የግዜ ጠለል ወደኋላ እንደሚነዳው ። ነገ የሚባል ነገርን እንደማያውቅ ። ትላንትን ሲገረብ እንደሚኖር…በዕስብታ …በትውስታ … በትዝታ … ስትናፍቂኝ … ጠምላይ ቅጠሎቿ ረግፈው ምግቧን በምን እንደምታዘጋጅ ግራ እንደገባት ሐረግ ነው ። ፎቶሲንተሲስ ቅንጦት ሆኖባት እግሯ መጠውለግ እንደጀመረ ። ፀሐይ ግልጥ ብላላት ደመንሚን እንደወረሳት … ስትናፍቂኝ … እግር ከወርች በወፍጮ ድንጋይ ተቋጥሮ በቀላይ እንደተጣለ ፍርደኛ ነው ። ቁልቁል ወደወለል እየሰመጠ አየር እንደሚያቡለቀልቅ ። ወደውስጥ መተንፈስ ተዓብ እንደሆነበት … ስትናፍቂኝ … ብሶል ( *ኮምፓስ )ሳይዝ እንደወጣ አሳሽ ነው ። ሁሌም ሰሜኑን እንደሚስት ። አቅጣጫ ሳይኖረው ዝምብሎ እንደሚሮጥ … ስትናፍቂኝ … በማማሰያ ተንጠፍጥፎ ቡሖን እንደሚለቁጥ አብሲት ነው ። ውሃ ሲያቀር ከርሞ የሊጥ ባህር ውስጥ ጭልጥ ብሎ እንደሚስጥም … ስትናፍቂኝ- እንደዛ ነው ። " ስትናፍቂኝ " እያልኩ የፃፍኩት ስናፍቅሽ ላለማለት ነው ። በኔ ማስታወስ ውስጥ መረሳት የሚባልን ኩሸት ማሰብ ሕማም ነው ። በስትናፍቂኝ ውስጥ ትናንፍቀኝ ይሆን ? የሚል ተሥፋ አለ ። አልዋሽሽም ትናፍቂኛለሽ ! ማለቴ እናፍቅሻለው … እየሄድኩ … እንደማንገናኝ እያሰብኩ … በዋልሴ ካራ ውስጤን እያጨድኩ ።

Episode details come from the podcast's RSS feed.

Embed this episode

Ready to play

•••ሥትናፍቂኝ

0:00 2:53

No transcript yet.

Requests help us decide what to transcribe next.

Frequently asked questions

How long is this episode of Sost kilo?

This episode is 2 minutes long.

When was this Sost kilo episode published?

This episode was published on January 10, 2021.

Can I download this Sost kilo episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.