ታላላቅ መጻሕፍት — Shakespeare: Hamlet episode artwork

EPISODE · Apr 25, 2026 · 45 MIN

ታላላቅ መጻሕፍት — Shakespeare: Hamlet

from ZereSew ዘረ-ሰው Podcast · host ZereSew

“To be, or not to be — that is the question.”ትምህርት 08 | 4 ክፍሎች | አቅራቢ: ሳባ & ኢብሳ & አበባ | ውይይት: ዳዊትና ትግስትWilliam Shakespeare (1564–1616) — ከ Stratford ትንሽ ከተማ የመጣ፣ ዩኒቨርሲቲ ያልገባ ግን ሰውን ከማንም በላይ ያየ ዓይን። ልጁ Hamnet ሞቶ ለአራት ዓመት ዝም ካለ በኋላ Hamlet ን ፈጠረ — አባቱን ያጣ ልዑል “መኖር ወይስ አለመኖር” ብሎ ጠየቀ። “ወደፊት ሂድ — በቀል ምንም አይቀይርም” — ያ ነው Hamlet ያስተማረው።ክፍል 1 — Shakespeare ማን ነበር? (ሳባ)* የ Stratford ልጅ — በ1564 ተወለደ። አባቱ ጓንት ሠሪ — ከክብር ወደ ውርደት ወደቀ — ልጁ ያንን ውድቀት ከቅርብ አየ፣ ኋላ ንጉሦች ሲወድቁ ጻፈ።* ዩኒቨርሲቲ አልገባም — Grammar School ብቻ — ጥበብ ከዲፕሎማ ሳይሆን ከመመልከት ይወለዳል።* Anne Hathaway — ገና 18 ዓመቱ ሳለ አገባ — ሦስት ልጆች ወለዱ — Susanna፣ መንትዮች Hamnet እና Judith።* “የጠፉ ዓመታት” — ከ1587 እስከ 1590 ምንም ሰነድ የለም — ከ Stratford ወጥቶ London ገብቶ ቲያትር ዓለም ውስጥ ታየ።* ከሞት ጋር መኖር — ቸነፈር London ያጭዳል — ቲያትር ቤቶች ይዘጋሉ — ሕይወትና ሞት ጎን ለጎን ነው።* Hamnet ሞተ — በ1596 ልጁ ሞተ — 11 ዓመት — ስለ ሐዘኑ አንድ ቃል አልጻፈም። ከአራት ዓመት በኋላ Hamlet ን ጻፈ — ያ ዝምታ Hamlet ሆኖ ወጣ።* ሰውን ያየበት ዓይን — ያለ ሃይማኖት ስብከት “ሰዎች ለምን ያሉትን ያደርጋሉ?” ብቻ ጠየቀ — ቅናት፣ በቀል፣ ፍቅር፣ ስልጣን — ሁሉንም በቃላት ገለጸ።ክፍል 2 — Elizabethan England (ኢብሳ)* ንግሥት Elizabeth — ልጅ ያልወለደች — “ወራሽ ማን ይሆናል?” ያስጨነቀ ጥያቄ — Hamlet ውስጥ ዙፋን ቅሚያ — ተመልካቾቹ ስለ England ያስቡ ነበር።* ካቶሊክ vs. ፕሮቴስታንት — ስለ ሥልጣን በግልጽ መናገር አይቻልም — ቲያትር ስለ ዴንማርክ ያወራል፣ ተመልካቾቹ ግን ስለ England ያዳምጣሉ — ቲያትር የፖለቲካ ድብቅ ቋንቋ ነው።* ቲያትር ለሁሉም — Globe Theatre ውስጥ ባላባቶች ከላይ፣ ተራ ሰዎች penny ከፍለው ቆመው — Shakespeare ሁለቱንም ማድረስ ነበረበት።* ቲያትር ከግንቡ ውጭ — Puritans “የዲያብሎስ ቤት” ይሉት ነበር — Globe Theatre 1613 ተቃጠለ።* Renaissance — ሰዎች ከመካከለኛው ዘመን ማዕቀፍ ውጭ ማሰብ ጀመሩ — Hamlet ዘመናዊ ሰው ነው፣ ጥያቄ ይጠይቃል ግን ማሰቡ ሲበዛ ድርጊቱ ይዘገያል።* ለምን ያ ዘመን? — Hamlet አሮጌና አዲስ ዓለም ሲጋጩ ብቻ ሊወለድ ይችላል — መካከለኛ ዘመን “ተበቀል” ይላል፣ Renaissance “ለምን?” ይጠይቃል — Hamlet ያ “ለምን?” ስለ ገባው ሊበቀል ያልቻለው።ክፍል 3 — ወደ ተውኔቱ (አበባ)ገጸ ባሕሪያት* ኀምሌት — የምድረ-ዴን ልዑል፣ አሳቢ፣ ፈላስፋ — ድርጊትን ወደ ኋላ የሚስብ* ገላውዴዎስ — ወንድሙን ገድሎ ዙፋን የያዘ — ገዳይ ግን ሕሊና ያለው* ገርትረድ — ኀምሌት እናት — ደካማ ወይ ክፉ? Shakespeare ክፍት ትቶታል* ወፌ-ይላ (Ophelia) — ኀምሌትን ትወዳለች — ፍቅሯ ዋጋ ያስከፍላታል — ቀልቧ ተሰልቦ ሞተች* ጶሎኔዎስ — አፈ-ንጉሥ — “ለራስህ ታማኝ ሁን” ያለ ግን ራሱ ሰላይ* ሆራትዮስ — ብቸኛ እውነተኛ ወዳጅ* ላርቆስ — ወፌ-ይላ ወንድም — ለበቀል ቸኩሎ Claudius ሰይፍ ሆነ* ፎርጠንብሮስ — የ Norway ልዑል — ድርጊት ያለው ሰው — ዙፋኑን አገኘታሪኩ — ገቢር በገቢርገቢር 1 — ጣዕረ መንፈስ ተናገረ — “ደሜን ተበቀላት — ገዳዩ ወንድሜ ገላውዴዎስ ነው” — ኀምሌት ዕብደት ሊስል ወሰነ።ገቢር 2 — ኀምሌት ዕብደት ሲያስመስል — ሮዘንቅሮስና ገድለ ስምዖን ሰላዮች ሆኑ — ተዘዋዋሪ ቲያትር ተዋናዮችን አገኝቶ ዕቅድ ዘረጋ — “The Mousetrap” ቲያትር አዘጋጅ።ገቢር 3 — “To be, or not to be” — ቲያትሩ ሲቀርብ ገላውዴዎስ በርግጎ ወጣ — ማስረጃው ጸደቀ — ግን ቤተ ጸሎት ውስጥ ሊገድለው ሲችል “ሲጸልይ ከገደልኩት ነፍሱ ትዳናለች” ብሎ ቆመ — ከዚያ መጋረጃ ጀርባ ጶሎኔዎስን ሳያውቅ ገደለ።ገቢር 4 — ኀምሌት ወደ እንግሊዝ ተሰደደ — ማዘዣውን ቀይሮ ሰላዮቹ ፈንታ እንዲገደሉ አደረገ — ተመልሶ ወደ ምድረ-ዴን ገባ — ወፌ-ይላ ቀልቧ ተሰልቦ ሞተች — ላርቆስ ለበቀል ተነሳ — ገላውዴዎስ ሰይፍ በመርዝ እንዲነከር አሳሳበ።ገቢር 5 — ራስ ቅል — “ዮሪቅ ነበር ይህ — ስልጣን፣ ሀብት፣ ዝና — ሁሉ ወደዚህ ይመጣ” — ፍልሚያ — ገርትረድ መርዝ ጠጥታ ሞተች — ላርቆስ ኀምሌትን በመርዝ ሰይፍ ወጋ — ሰይፍ ተቀያይረው ሁለቱም ተበከሉ — ላርቆስ ሚስጥሩን ተናዘዘ — ኀምሌት ገላውዴዎስን ገደለ — “ቀሪው ዝምታ ነው” — ፎርጠንብሮስ ባዶውን ዙፋን ተቀበለ።ዋናው ትምህርት“Move on. Vengeance will change nothing.” — ወደፊት ሂድ፣ በቀል ምንም አይቀይርም።ክፍል 4 — ውይይት (ዳዊትና ትግስት)* ፍትሕ vs. በቀል — ፍትሕ ሥርዓት ይፈልጋል፣ በቀል ስሜት ብቻ ነው — Hamlet ማስረጃ ሰብስቦ ፖለቲካ ተጠቅሞ ማጋለጥ ይችል ነበር — ግን ግል በቀል መረጠ።* ሐዲስ ዓለማየሁ ግንኙነት — “ፍቅር እስከ መቃብር” ተመሳሳይ ጥያቄ — ግለሰብ ራሱ ዳኛ ሲሆን ውጤቱ ጥፋት ነው።* Gertrude — ክፉ ሳትሆን ደካማ — ልጇን ትወዳለች — መርዝ ያለውን ወይን ስትጠጣ ልጇ እንዳይጠጣ ራሷ ጠጣች ብለው የሚተረጉሙ ሊቃውንት አሉ።* ማመንታት — Hamlet ያስብ ይቆያል ግን አያደርግም — ጶሎኔዎስን ሲገድል ደግሞ ያለ ማሰብ ወጋ — ሁለቱም ጽንፎች ጥፋት ናቸው — ሚዛን ያስፈልጋል።* Fortinbras — Hamlet ሲያስብ Fortinbras ይሠራል — Hamlet ሲሞት ዙፋኑን ያገኛል — ያለ ሴራ፣ ያለ በቀል።* ሐዘንን ይዞ ወደ ፊት — ሐዘን ወደ ፊት ሲሄድ ጥንካሬ ነው፣ ወደ ኋላ ሲሄድ ጥፋት ነው — Hamlet ወደ ኋላ ሄደ።ያልተነገሩ ነገሮች* Shakespeare ለሚስቱ “ሁለተኛውን ምርጥ አልጋ” ብሎ ኑዛዜው ውስጥ ትቶላታል — ለምን ሁለተኛውን? ማንም አያውቅም* Hamlet ከዓለም ሥነ ጽሑፍ ረጅም ሚና ነው — 1,475 ገደማ ስንኞች — ከ4 ሰዓት በላይ መድረክ ላይ* Globe Theatre 1613 “Henry the Eighth” ሲቀርብ ተቃጠለ — ሦስት ሺ ሰዎች ነበሩ — አንድ ሰው ብቻ ተጎዳ — ሱሪው ላይ እሳት ቢራ አጠፉት* ጀርመንኛ ትርጉሙ (August Wilhelm Schlegel) ከ Shakespeare ጋር ተወዳዳሪ ነው ይባላል — ጀርመኖች “የእኛ Shakespeare” ይሉታል* Kronborg Castle (Elsinore) ዛሬም አለ — በየዓመቱ Hamlet ይቀርብበታል — Shakespeare ራሱ ዴንማርክ ሄዶ አያውቅምቁልፍ ጥቅሶች“To be, or not to be — that is the question.” — ኀምሌት“The rest is silence.” — “ቀሪው ዝምታ ነው።” — ኀምሌት“To thine own self be true.” — “ለራስህ ታማኝ ሁን።” — ጶሎኔዎስ“ዮሪቅ ነበር ይህ — ስልጣን፣ ሀብት፣ ዝና — ሁሉ ወደዚህ ይመጣ።” — ኀምሌት“Move on. Vengeance will change nothing.” — ፕሮፌሰሩ“Mediocre minds invariably hate genius.” — ፕሮፌሰሩስሞችና ቃላትሰዎች* William Shakespeare (1564–1616) — ጸሐፊ፣ ተዋናይ — “የ Stratford ሊቅ”* Anne Hathaway — የ Shakespeare ሚስት* Hamnet Shakespeare — የ Shakespeare ልጅ — በ11 ዓመቱ ሞተ* ኀምሌት (Hamlet) — የምድረ-ዴን ልዑል* ገላውዴዎስ (Claudius) — ወንድሙን ገድሎ ዙፋን የያዘ ንጉሥ* ገርትረድ (Gertrude) — ንግሥት — ኀምሌት እናት* ወፌ-ይላ (Ophelia) — ኀምሌት ያፈቀራት* ጶሎኔዎስ (Polonius) — አፈ-ንጉሥ* ሆራትዮስ (Horatio) — ኀምሌት ወዳጅ* ላርቆስ (Laertes) — ወፌ-ይላ ወንድም* ፎርጠንብሮስ (Fortinbras) — የ Norway ልዑል* Saxo Grammaticus — “Amleth” ታሪክን የጻፈ ዴንማርካዊ ታሪክ ጸሐፊቦታዎች* Stratford-upon-Avon — Shakespeare የተወለደበት* Globe Theatre — London — ከ Thames ወንዝ ዳር ያለ ክብ ቲያትር ቤት* Elsinore (Kronborg Castle) — ዴንማርክ — Hamlet ታሪኩ የሚካሄድበት ቤተ መንግሥት* Wittenberg — Hamlet ያጠናበት ዩኒቨርሲቲ — Martin Luther ም ያጠናበትቃላትና ፅንሰ ሐሳቦች* Elizabethan England — ንግሥት Elizabeth the First ዘመን (1558–1603)* Renaissance — “ዳግም ልደት” — ከመካከለኛው ዘመን ማዕቀፍ ውጭ ማሰብ* The Mousetrap — ኀምሌት ያዘጋጀው ተውኔት ውስጥ ተውኔት* Revenge tragedy — የበቀል ተውኔት — በ Elizabethan ዘመን ታዋቂ ዘውግ* Soliloquy — ገጸ ባሕሪ ለብቻው የሚያወራበት — “To be, or not to be” ታዋቂው This is a public episode. If you would like to discuss this with other subscribers or get access to bonus episodes, visit www.zeresew.com

Episode metadata supplied by the publisher feed · Published Apr 25, 2026

Embed this episode

NOW PLAYING

ታላላቅ መጻሕፍት — Shakespeare: Hamlet

0:00 45:27

No transcript for this episode yet

We transcribe on demand. Request one and we'll notify you when it's ready — usually under 10 minutes.

No similar episodes found.

No similar podcasts found.

Frequently Asked Questions

How long is this episode of ZereSew ዘረ-ሰው Podcast?

This episode is 45 minutes long.

When was this ZereSew ዘረ-ሰው Podcast episode published?

This episode was published on April 25, 2026.

Can I download this ZereSew ዘረ-ሰው Podcast episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.
URL copied to clipboard!