EPISODE · Oct 8, 2025 · 59 MIN
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ፡ ለአፍሪካ ንግድ አዲስ ምዕራፍ
from The Rising South
“የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መመስረት [...]ለአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ ለመነገድ ዕድል ይሰጣል። እስከ አሁን ድረስ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ንግድ 15 በመቶ ብቻ ነው። የአፍሪካ ሀገራት ያለ ቀረጥ እንዲነግዱም ዕድል ይሰጣል።” ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያዉ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዝግጅትን ተከትሎ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀናቸዋል። በዚሁ ዝግጅታችን ፣ ትናንት ሁለተኛ ዓመቱ የደፈነውን የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት መነሻ አድርገን ፣ ስኬት የምዕራብ ዓለም መራሹን ድርድሮችና ለውድቀታቸው ምክንያት የሆኑ ነጥቦች እንዲሁም እያደገ የመጣው የባለብዙ-ዋልታ ዓለም አማራጭ የአሸማጋይነት ሚና በተመለከተ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ መሀመድ ኢብራሂም ምሁራዊ ምልከታዎችን ጠይቀናቸዋል። ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፐሮግራሙን ያዳምጡ
Embed this episode
NOW PLAYING
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ፡ ለአፍሪካ ንግድ አዲስ ምዕራፍ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.