EPISODE · Nov 18, 2025 · 1H
ኢትዮጵያ '' የምስራቅ አፍሪካ ዓይን '' ፡ ቀጠናውን የማስተሳሰር እና የማስተባበር ሚናዋ ሲገለጥ
from Sovereignty Sources
''በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያሉ ሀገራት የሚጋሯቸው በርካታ ጉዳዮቾ ያሏቸው ሲሆኑ እንደ ማኅበረሰባዊነት፣ ቀጠናዊነት፣ ቋንቋና ባህል ያሉት ተጠቃሾች ናቸው —ኢትዮጵያ በታሪክ በቀጠናው እንዲሁም ከዛም ባለፈ አዎንታዊ ሚናን በመጫወት የምትታወቅ ሀገር ናት ሲሉ '' የውጭ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አክለውም፡ ''በቀጠናው እየጎለበቱ ያሉ በርካታ ልማቶች ይገኛሉ። ቁልፍ የሚባል የለውጥ ሽግግርም እያደረገ ነው። እናም የውደፊቱ ብሩህ እንደሚሆን በእርግጠኝነት እናምናለን - ብለዋል'' ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን በምንዳስስበት የዛሬው ፕሮግራማችን በመጀመሪያው ክፍል በምስራቅ አፍሪካ በተለይም በአፍሪካ ቀንድ የጋራ ፖሊሲዎችና የወደፊት ዕይታዎች ዙሪያ የእርስ በርስ ትስስርና ትብብርን መፍጠርና በቀጠናው የኢትዮጵያን ቁልፍ ሚና በተመለከተ ከውጭ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ጋር በጥልቀት እንዳስሳለን። የአፍሪካ ሀገራት ለዘመናት ከተጫናቸው የውጪ አካላት ቁጥጥር ለመላቀቅ የራሳቸውን ነፃ ፖሊሲዎች መገንባት አለባቸው በሚል ነዋሪነቷን ታንዛንያ ካደረገችው ደራሲና መምህር ሚስ ሼቮን ፎርድ ጋር ያደረግነው ቆይታም በዚሁ ፕሮግራም የምንዳስሰው ሌላኛው ዐቢይ ጉዳያችን ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
ኢትዮጵያ '' የምስራቅ አፍሪካ ዓይን '' ፡ ቀጠናውን የማስተሳሰር እና የማስተባበር ሚናዋ ሲገለጥ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.