የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካን የዕዳ ጫና ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ይቀይረዋልን? episode artwork

EPISODE · Jun 10, 2025 · 1H

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካን የዕዳ ጫና ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ይቀይረዋልን?

from The Rising South

የአፍሪካ የዕዳ ጫና ከጠቅላላ የአህጉራዊ ምርት ውስጥ ከ 66 በመቶ በላይ ሆኗል ። ለዚህም ደካማ የብድር ስርዓት እና ሙስና ምክያቶቹ ናቸው፡፡ ይህ የጤና ስርዓት ላይ እና ትምህርትን በማደናቀፍ ረገድም አሉታዊ ሚናን እየተጫወተ ነው። በዛሬው የራይዚንግ ሳዉዝ ዝግጅታችን ከኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የጋበዝናቸዉ ዶ/ር ጀማል መሐመድ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ።“ብድር በግድ ውሰዱ ብለው አያስወስዱንም፡፡ [...] ከጀርባ ግን ብድር እንድንጠይቅ የሚገፋፉ ነግሮች አሉ ፡፡ ወርልድ ባንክም አይ ኤም ኤፍም፡፡ [...] በተለይ አፍሪካ አካባቢ ደግሞ ይህንን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተቋማት ስለሌሉ አብዛኛው [ብድር] በካፒታል ፍላይት [ብድሩ በሃገር ስም ቢመጣም] ብሩ ተመልሶ ወደ አዉሮፓ እና አሜሪካ ይሄዳል፡፡ በተመሳሳይ [ዕዳዉን ] እኛ እንከፍላለን ፣ አበዳሪዎች ያተርፋሉ" ብለዋል፡፡የምስራቃዊ ቡድን አቀራረቦችን በተመለከተም ዶ/ር ጀማል መሐመድ:-"የሩሲያ እና የቻይና አቀራረብ በምጣኔ ሃብታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተለይ የሩሲያ አቀራረብ ከዚያ በላይም ሊሄድ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ከነጻነት ትግል ወቅት ጀምሮ ሀገራት ነጻ እንዲሆኑ ሃቀኛ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩት ሩሲያዎች ናቸው፡፡ እስካሁን ያላቸው እሴት ይመስለኛል፡፡ [...] ሌሎቹም አገራት የእነሱን ዓርዓያነት ተክትለው ነበር፡፡ ለአብነት ኩባን መጥቀስ ትችላለህ፡፡ እነ ፊደል ካስትሮ ለኢትዮጵያ እና አንጎላ ድጋፍ ያደረጉት [ለዚያ ነው]” ሲሉ ተናግረዋል።ዶ/ር ጀማል እንደ መፍትሄ ባሉት ሀሳብ:-"አፍሪካውያን እንደመሆናችን መጠን የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በማጠናከር የውጭ ኃይሎች ላይ ጥገኝነትን መቀነስ አለብን። 54 የተለያዩ ኢኮኖሚዎች ያሏት አፍሪካ ታሪፎችን እና የገበያ እንቅፋቶችን በማስወገድ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችን የሚስብ አንድ ወጥ ገበያ መፍጠር ትችላለች" ብለዋል፡፡ስለ አፍሪካ የእዳ ጫና እና ከእዳ መውጫ መንገዶች ለማወወቅ ይህንን የ ራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት ይከታተላሉ።

Episode metadata supplied by the publisher feed · Published Jun 10, 2025

Embed this episode

Ready to play

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት የአፍሪካን የዕዳ ጫና ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬ ይቀይረዋልን?

0:00 1:00:00

No transcript for this episode yet

We transcribe on demand. Request one and we'll notify you when it's ready — usually under 10 minutes.

No similar episodes found.

No similar podcasts found.

Frequently Asked Questions

How long is this episode of The Rising South?

This episode is 1 hour and 0 minutes long.

When was this The Rising South episode published?

This episode was published on June 10, 2025.

Can I download this The Rising South episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.
URL copied to clipboard!