EPISODE · Nov 27, 2025 · 1H
የአፍሪካ አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፡ የቅኝ ግዛት ዘመኑን በደል ምን ሊክሰው ይችላል ?
from The Rising South
“ገንዘብ እጅግ ጥሩ ያልሆነ የካሳ ዓይነት ይመስለኛል። የአውሮፓ አፍሪካን የመቆጣጠር ጥቅም፣ ከቅኝ ግዛት፣ ከአዲሱ ቅኝ ግዛት እና ከባርነት የተገኘው፣ ዘላቂ ችግር ነው። ስለዚህ፣ የካሳው ጥቅምም እንዲሁ ዘላቂ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ።[…]የቀድሞ ጨቋኞች በአህጉሪቱ ላይ የአንድነት መሠረተ ልማቶችን መገንባት አለባቸው። ይህ ማለት እንደ ካሳ ፣ መላውን አፍሪካ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ አፍሪካ የሚያገናኝ የባቡር ሐዲድ መገንባት አለበት።[...] ይህ አፍሪካ ዛሬ ከምናደርገው በበለጠ መልኩ በውስጥዋ ውጤታማ ንግድ እንድትፈጽም ያስችላታል።” ሲሉ የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ እና አማካሪ ካባላ ጆን ካባላ ጆን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ፣ በመጀመሪያው ክፍል የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝና አማካሪ ከሆኑት ከካባላ ጆን ጋር በመሆን የአፍሪካን አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተገቢነት ተወያይተናል ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዲጂታል ፋይናንስ ለውጥ እና እድገት እንዲሁም አሳታፊነት የኢትዮ-ኢንክሉሲቭ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሆኑት ከአቶ አዋሽ ባቴ፣ እና የአሪፍፔይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረድኤት ጽጌብርሃን ጋር ያደረገነው ቆይታ በሁለተኛው ክፍል ተዳስሷል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
Embed this episode
NOW PLAYING
የአፍሪካ አህጉራዊ የካሳ ጥያቄ ፡ የቅኝ ግዛት ዘመኑን በደል ምን ሊክሰው ይችላል ?
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.