EPISODE · Oct 31, 2025 · 1H
የአፍሪካ ጉዞ ከትግል እስከ መታደስ ፡ ታሪክን መመለስና የወደፊቱን መወሰን
from The Rising South
"አፍሪካ ነጻ አይደለችም። በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ፣ በወታደራዊ ወይንም በሌላ በማንኛውም ነገር ቢሆን፤ የአፍሪካ ነፃነት መጀመር ያለበት ከእውቀት [ጥገኝነት] ነፃነት ነው ።" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ 🎧በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ ከአፍሪካ የተረሱ ያለፉ ምዕራፎች ተነስተን ወደፊት ወደ ሚዘራው ዘር እንጓዛለን። በክፍል አንድ፣ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ዳዊት መዝገበ ጋር የአፍሪካን የትግል ጀግኖች በምዕራባዉያኑ ቦታ የማይሰጣቸውና የተረሱት ለምንድን ነው ስንል እንጥይቃለን ፤ በክፍል ሁለት ደግሞ በአዲስ አበባ በተካሄደው የቻይና–አፍሪካ ግብርና ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስብሰባ ላይ ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት መጻኢ ተስፋዎቹ እንወያያለን፣ ለዚህም የተ.መ.ድ የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ)ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ቀጣናዊ ተወካይ አበበ ኃይለ ገብርኤል (ዶ/ር) ፣ የግብርና ሚኒስቴር ዴኤታ ኤፋ ሙለታ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ አዲስ አጋርነት ለአፍሪካ ልማት የኔትዎርክ ማናጀር ፕሮፌሰር ኤሪክ ቻካውያ አነጋግረናቸዋል። "ያፈራናቸውን ዕውቀቶች፣ ያለንን የሀገር በቀል ዕውቀት፣ ከመደበኛ ትምህርት ያገኘነውን ዕውቀት ወስደን በአንድ ላይ ማዋሃድ አለብን፤ ይህም ለችግሮቻችን መፍትሄ ላይ እንድንደርስ ያደርገናል።" ሲሉ የአፍሪካ ህብረት የልማት ኤጀንሲ አዲስ አጋርነት ለአፍሪካ ልማት የኔትዎርክ ማናጀር ፕሮፌሰር ኤሪክ ቻካውያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡፡
Embed this episode
NOW PLAYING
የአፍሪካ ጉዞ ከትግል እስከ መታደስ ፡ ታሪክን መመለስና የወደፊቱን መወሰን
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.