EPISODE · Jun 16, 2025 · 30 MIN
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ:- የአዋጁ ይዘት እና ቅጣቶቹ
from The Rising South
በኢትዮጵያ የከተሞች መስፋፋት እና እድገት፣ ከሕዝብ ቁጥር እድገትና ለዉጥ ጋር ተዳምሮ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ላይ የራሱን የሆነ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ግንቦት 26 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፤ በዋለው የ33ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ን በሙሉ ደምጽ አፅድቋል። በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ቆይታችን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር አወቀ አምዛዬ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተውናል፡፡🔇ዶ/ር አወቀ ስለዚህኛው አዋጅ ሲያብራሩ:-“ባለፉት ጊዜያት የወጡ ወጥቶ የነበረው አዋጅ ያስከተለው ችግርና ምንም መተግበር ስላልተቻለ፣ ሀገሪቱ እየተበከለች ስለሆነ ቀስ በቀስ ሺፍት እንዲያደርግ ነው። ሁለተኛ ዛሬውኑ ይታገድ ብሎ አይደለም በነገራችን ላይ የወጣው አዋጅ። ስድስት ወር የሽግግር ጊዜ አለ ገና። በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ከባለ ኢንዱስትሪዎች ጋራ ምክክሮች ይደረጋሉ፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ 💸አዋጁ ቅጣትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ሲገልጹ፡-“ባለሱቁና አምራቹ ይቀጣል በነገራችን ላይ፤ ሁለት ሺህ ብርና ሶስት ሺህ ብር ለግለሰብ ነው። አምራቾች የእነርሱ ቅጣት ከ50 ሺህ ብር በላይ ነው። እስከ ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚደርስ ነው።” በማለት ዶ/ር አወቀ አክለው ተናግረዋል፡፡''ስለ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ረቂቅ አዋጅ ይዘት እና አዋጁን መተላለፍ ስለሚያስከትላቸው ቅጣቶች የበለጠ ለማወቅ ይህንን የራይዚንግ ሳውዝ ፕሮግራም ይከታተሉ፡፡
Embed this episode
NOW PLAYING
የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ:- የአዋጁ ይዘት እና ቅጣቶቹ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.