EPISODE · Dec 1, 2025 · 1H
የግብርና መድህን ሽፋን በኢትዮጵያ
from The Rising South
“የግብርና መድህን በአገራችን ውስጥ የሚፈለገውን ያህል አላደገም፡፡ ከአጠቃላይ ኢንዱስትሪው ከሚሰጠው የመድህን ሽፋን የግብርና ኢንሹራንስ ስናየው ከ 1 በመቶ አይዘልም፡፡ እስካሁን የተሰራው፡፡ እሱም ቢሆን ደግሞ በአብዛኛው ኮሜርሻል ፋርም ጋር የሚያያዝ ነው፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ማህበር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የስትራቴጂ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡ በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ባለ ሁለት ክፍል ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል በኢትዮጵያ ውስጥ የግብርና መድህን ያለበትን ደረጃ እና አገልግሎቱን ተደራሽ በማድረግ ረገድ እያጋጠሙ ስላሉ የተለያዩ ተግዳሮቶች የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ማህበር ም/ፕሬዝደንት እንዲሁም የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር የስትራቴጂ እና ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍቅሩ ፀጋዬ ጋር የተወያየን ሲሆን፤ የሁለተኛውን የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ፕሮጀክት በይፋ የማስጀመር መርሀ-ግብር አስመልክቶ ያዘጋጀነው መሰናዶም ተካትቷል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
NOW PLAYING
የግብርና መድህን ሽፋን በኢትዮጵያ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.