EPISODE · Dec 24, 2025 · 1H
የሆሊውድ የባህል ወረራ ፦ አፍሪካዊ ማንነቶች ላይ ያነጣጠረው አዲስ የቅኝ ግዛት መልክ
from The Rising South
“የሆሊውድ ተጽእኖ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው፤ ጉዳቱ ያመዝናል ግን ቢሆንም ጠቃሚነቱም ደግሞ የሚካድ አይደለም። [...] ምዕራባውያን በአብዛኛው ፊልሞቻቸው ላይ የበላይነታቸውን ሊያሳዩን ይሞክራሉ፡፡ [...] በተቃራኒው ደግሞ የአፍሪካን ኋላቀርነት እና አስከፊ ገጽታ ለመገንባት ይሞክራሉ፤ ይህም ትውልዱ ራሱን እና ሀገሩን የሚያይበትን መንገድ የተበላሸ እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡” ሲል ደራሲ ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ቢኒያም ወርቁ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል፡፡በዚህኛው ባለሁለት ክፍል የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በመጀመሪያው ክፍል፣ የፊልም እና ቲያትር ባለሙያ ከሆነው ከደራሲ ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ቢኒያም ወርቁ ጋር በመሆን የምእራብያውያን የፊልም እና ሌሎች የጥበብ ስራዎች ቀሪውን ዓለም የሚቃኙበት እና የሚያቀርቡበት መንገድ እንዴት ባለ መልኩ ተጽዕኖ እየፈጠረ እንዳለ ባለሙያዎች ይህን የባህል ወረራ እንዴት ባለ መልኩ መመከት እንደሚችሉ በሰፊው ቃኝተናል፡፡ በኬንያ እና በሴኔጋል መካከል የተፈረመውን ከቪዛ ነጻ እንቅሳቃሴን መሰረት በማድረግ ይህ ለአፍሪካ እና አፍሪካውያን የሚኖረው ትርጉም፣ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው፣ እንዲሁም ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ዓላማ ጋር የሚኖረውን መጣጣም የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ፣ ደራሲ እንዲሁም የቱሪዝም ባለሙያ እና የባህል ጉዳዮች አንቂ ራስ አብይ ጥላሁን ጋር ያደረግነው ቆይታም በሁለተኛው የዝግጅታችን ክፍል ተዳስሷል፡፡ ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
Embed this episode
Ready to play
የሆሊውድ የባህል ወረራ ፦ አፍሪካዊ ማንነቶች ላይ ያነጣጠረው አዲስ የቅኝ ግዛት መልክ
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.
Similar Podcasts
No similar podcasts found.