Skip to content
የመጨረሻዋ እራት  episode artwork

Jan 10, 2022 4 min

የመጨረሻዋ እራት

from Sost kilo Hosted by Leoul Zewelde

የተለያየነው የተገናኘን 'ለት ነው ። እንዲህ እልህ ፍቅራችንን ሳይወርስ በፊት አንዳችን የአንዳችን ደቅ ነበርን ። አሁን በነብስም በስጋም ተለያይተናል ። ሰው ስለይ ጎበዝ እንደሆንኩ እነግራት ነበር ። የትናንት እንጥፍጣፊ ውስጤ አላስቀርም ። ክፉንም ደግ ጠጠር እንደሞላው አቁፋዳ እንዲረሳ አድርጌ ከባህር እሰደዋለው ። አሁንም የሆነው እንደዛ ነው ። ታሪካችን እንደተቋጠረ ቁልቁል ሰምጧል ። ትናንት ሲመሽ እንደሁሌው ጣቶቼን ይዛ አልፀለየችም ። ይልቁን አይኖቼ እስኪከደኑ ጠብቃ የቢጃማዋን መቀነት እየጎተተች ከቤት ወጣች ። አረማመዷ ከመሮጥ ለትንሽ ያዘገመ ነው ። ሻሿ ተፈቶ ከመሬት ሲወድቅ ፤ ፀጉሯ እርቃን ሲወጣ እስከማይሰማት ድረስ ። ዲናዎቹ ሌቱን ሄደችላቸው እንጂ አንዳቸውም ሊይዟት አልመጡም ። ሙራጅ የሽፍታ ሻሞላ ያላደነውን አያርድምናና እነርሱም አራከሷት ። ቢያንስ ቀርድደው እንዲሰቅሏት ብትለምናቸውም ከመሀከላቸው አንድ ሃባ እዛኝ ሳታገኝ ቀረች ። በእንባ የታጠበ ልመናዋ መኖር እንዳገሸገሻት ያሳብቃል ። ሞት ግን የመጣችበትን መንገድ ያህል ራቃት ። አማራጭ እንዳጣች ሲገባት ገለባ ነፍሷን እንደተሸከመች ወደቤት ተመለሰች ። ከጀርባዋ ሲያጅቧት የነበሩ ቁራዎች የጣሪያው ቆርቆሮ ላይ ሲያርፉ ጥፍራቸው ይንሰጠሰጣል ። እንዳልሰማት ዱካዋን በወለሉ እያሟሸች በለሁሳስ አንሶላውን ገልባ ገባች ። እግሯ ይቀዘቅዛል ። ገላዋ ውስጥ የገባው ቁር ከሰውነቷ አልፎ ወደ አልጋው ተጋባ ። ልክ ሽፋሽፍቷ ሲገጥም በተራዬ ተነሳሁ ። የመስኮቱ የግራ መዝጊያ ተበርግዶ ንፋስ ያንሰጠስጠዋል ። የመጋረጃው ዘርፍ ሲውለበለብ የዘለበቱ ጠፍር ከማዕዘኑ ጋር እየተላተመ ይንቋቋል ። ዘላ እንደገባች መልሳ እንዳልዘጋችው ገባኝ ። በድንግዝግዙ ፈዝዤ ደቂቃው ነጎደ ፤ ፅልመቱ ሄዶ አልጎኸም። " ሰዓትህ ደርሷል " ። በውስጤ ያወራሁት ድምፅ አፌን ትቶ በጆሮዬ ወጣ ። ሹክሹክታዬን እንደሰማሁ ከቆምኩበት ወደ ቡፌው ተራምጄ የመሳቢያውን ሰረገላ እንደደገፍኩ ካራ አሰስኩ ። ወዲያውን ፈፀምኳት ። እጄና ክርኔ ላይ የተናጠበው ትኩስ ደም ሳይደርቅ ጨረቃ መግቢያዋን መማሰን ጀምረች ። ፀሐይ ግን ለመውጣት 'ራሱ የወሰነች አትመስልም ። የሰማዩ ውዥንብር የምድሩ ቲያትር ነፀብራቅ ነው ። እጅከፍንጅ የያዘችኝ ቅፅበት በምናልባት ረግታ ለመፍረድ ስታሰላስል ይመስላል ። ሐሙስ ማታ - መዐድ ቀርባ ስትጠብቀኝ የመጨረሻችን ( የመጨረሻዋ ) እራት እንደሆነ ታውቅ ነበር ። ስትስቅ ግን ለዛዋ እንዳለ ነው ። እንደሁሌም ፈገግታዋን ለማገዝ የአይኖቿ ዳር ይሸበሸባል። በአፍንጫዎቿ ጫፍ የአንገቴን ስር ትታከከኛለች ። ምኗም የተረበሸ አትመስልም ። ነገን እንደማትኖር እያወቀች ስለሚፈሰው ደሟ ፅዋ አልቀዳችልኝም ። አታላኛለች ። ረጅሙ ሌት ሟጦ እንደምንም አርብ እስከወጋገኑ ጠባ ። ታጥቦ ያልተወለወለ የሣህን ላብ በመሃረቤ አደራርቄ ጠረጴዛው ላይ አኖርኩ ። የመጀመሪዬን ቁርስ ለብቻዬ እያበሰልኩ ነው ። ህልም የሆነ አዳሬ ረዝሞ እንደማይነጋ ፤ ጭንቀት ሰቅዞ እንዳልያዘኝ አሁን እየተነፈስኩ ነው ። መጥበሻውን አንጋልዬ ዘይት ስጨምር በእሳት የጋለ ልቧ መንቶሻቶሽ ጀመረ ። ይቺ ሴትዘመን ፆሜን ልታስገድፈኝ ነው ።

Episode details come from the podcast's RSS feed.

Embed this episode

Ready to play

የመጨረሻዋ እራት

0:00 4:37

No transcript yet.

Requests help us decide what to transcribe next.

Frequently asked questions

How long is this episode of Sost kilo?

This episode is 4 minutes long.

When was this Sost kilo episode published?

This episode was published on January 10, 2022.

Can I download this Sost kilo episode?

Yes. Use the download control on the episode player to save the publisher-provided media file.