EPISODE · Jan 23, 2026 · 1H
የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ለተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መሥፋፋት
from Sovereignty Sources
''የንፁህ ኢነርጂ ልማት ጉዳዮች ያለ ግል ዘርፉ ተሳትፎ እውን ሊሆኑ አይችሉም። ስለዚህ የመንግስትና የግል ዘርፍ አጋርነት እጅግ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ — መንግስታት፣ የግል ዘርፎች እንደ ቴክኖሎጂና ልማት ሥራዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያውሉ ማነቃቃት ይኖርባቸዋል።'' ሲሉ ቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት ጉዳዮች ለውይይት በሚቀርቡበት የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስሰ ፕሮግራማችን፣ በክፍል አንድ የመንግስትና የግል አጋርነት የተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መስፋፋት እንዲፈጠር የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ በተመለከተ ከቤካ መገርሳ፣ የዘርፉ አማካሪ እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የቀድሞ ቴክኒካል አማካሪ ጋር ቃኝተነዋል። የህግ መሠረት የሌላቸው የውጭ ጣልቃብነቶችን ለማስወገድ አፍሪካ የተቀናጀ ዲፕሎማሲን እንደ መሣሪያ መጠቀም የምትችልበት አግባብን በሚመለከት ኡጋንዳዊው የዓለም አቀፍ ቢዝነስ አክስፐርቱ ዙብሪ ሉጂያና ምልከታቸውን አጋርተውናል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ሙሉ መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ
Embed this episode
Ready to play
የመንግሥት እና የግል ዘርፍ አጋርነት ለተቀላጠፈ የንፁህ ኃይል መሥፋፋት
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.