EPISODE · Dec 15, 2025 · 1H
የፀረ ቅኝ ግዛት ቀን፡ የከሰመው ግን መልኩን ለውጦ የመጣው ቅኝ ግዛት ሲገመገም
from Sovereignty Sources
''አፍሪካ ትናንት በቅኝ ግዛት የደረሰባት ነገር አይዘነጋም፣ ራስ ገዝ እና ሉዓላዊነት በሌለበት ነፃነት አይኖርም። በዚህም ሀገራት የራሳቸውን ነፃነት የማወጅ ሙሉ መብት አላቸው — የአፍሪካ ሆኑ ሌሎች ሀገራት ባለፉ ዘመናት በምዕራባውያን ከደረሰባቸው ተፅዕኖ አንፃር ወደፊት ሌሎች አማራጮችን በጂዮ ፖለቲካው ላይ መቃኘት ይኖርባቸዋል '' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ሁለት አንኳር ጉዳዮችን በምንቃኝበት ፕሮግራማችን፣ በመጀመሪያው ክፍል ዓለም አቀፉ የፀረ ቅኝ ግዛት ቀንን መነሻ በማድረግ ዕለቱን ለውጥ ለማምጣትና መልኩን የቀየረውን ቅኝ ግዛትን በተመለከተ ለመወያየት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህሩ የእዮብዘር ዘውዴን ጋብዘናቸዋል። ስፔስ ሳይንስ ዘርፍ በአፍሪካ ትብብርን፣ ሰላም ግንባታን እንዲሁም አስተማማኝ ልማትን ለመፍጠር ሁነኛ የዲፕሎማሲ መድረክ መሆን በሚችልበት ጉዳይ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የጂኦስፓሻል አስተዳደር ክፍል መሪ አንድሬይ ኖምጉዊሮማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስፔስና ጂኦስፓሻል ተቋም ምክትል ዳይሬክተር ዩሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) ጋር ያደረግነው ቆይታም በፕሮግራሙ ሁለተኛው ክፍል የምንቃኘው ሌላኛው ጉዳያችን ነው። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
Embed this episode
Ready to play
የፀረ ቅኝ ግዛት ቀን፡ የከሰመው ግን መልኩን ለውጦ የመጣው ቅኝ ግዛት ሲገመገም
No transcript for this episode yet
Similar Episodes
No similar episodes found.